የሰኔ 9 ሥንክሳር #ታላቁ ነቢይ ሳሙኤል ዕረፍቱ #አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ #ሉክያኖስ ሰማዕት#ortodox

የሰኔ 9 ሥንክሳር አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዘጠኝ በዚች ዕለት የታላቁ ነቢይሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ። የዚህ ቅዱስ አባቱ ሕልቃና ይባላል የእናቱም ስሟ ሐና እነርሱም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ወገን ናቸው ። ሐናም መካን ነበረች ክብርይግባውና ወደ እግዚአብሔር እያለቀሰች አዘውትራ ስለ ማለደች ይህን የተባረከ ልጅ ሰጣት በቤቷም ሦስት ዓመት አሳደገችው ። ከዚህም በኋላ ገና ስትፀንሰው እንደተሳለች ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አቀረበችው ካህኑ ኤሊንም በመላላክ የሚያገለግለው ሆነ ። የካህኑ የኤሊ ልጆች ግን ክፉዎች ነበሩ እግዚአብሔርንም አይፈሩም ነበር በቅዱስ መሥዋዕቱም ላይ በደሉ ። ይህ ሕፃን ሳሙኤል ግን በኤሊ ፊት ለእግዚአብሔር ሲያገለግል ኖረ በነዚያ ወራቶችም ቃለ እግዚአብሔር ውድ ነበርየሚታይ ራእይም አልነበረም ። ከዚህም በኋላ በአንዲት ሌሊት እንዲህ ሆነ ኤሊ በመኝታው ተኝቶ ሳለ ዐይኖቹም መፍዘዝ ጀምረው ነበር ማየትም አይችልም ነበር ። የእግዚአብሔርንም መብራት አብርቶ ለማሳደር ገና አላዘጋጁም ነበር ሳሙኤል ግን በቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦት አጠገብ ተኝቶ ነበር እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው እነሆ እኔ አለሁ አለ ። ወደ ኤሊም ፈጥና ሔደ ስለጠራኸኝ እነሆ እኔ መጣሁ አለው ኤሊም አልጠራሁህም ተመልሰኽ እግዚአብሔርም ዳግመኛ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ኤሊ ሔደ ስለጠራኸኝ እነሆ መጣሁ አለው ። ኤሊም አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ አለው ። ሳሙኤልም ከዚህ አስቀድሞ እግዚአብሔርን በራእይ ገና አላወቀውም ነበር ቃለ እግዚአብሔርም አልተገለጠለትም ነበር ። ዳግመኛም እግዚአብሔር ሳሙኤልን ሦስተኛ ጊዜ ጠራው ተነሥቶም ወደ ኤለ, ሔደ ስለጠራኸኝ እንሆ መጣሁ አለው ኤሊም ያንን ልጅ እግዚአብሔር እንደጠራው አሰበ ። ልጄ ተመልሰህ ተኛ የሚጠራህ ካለ እኔ ባርያህ እሰማለሁና ጌታዬ ተናገር በለው አለው ሳሙኤልም ሒዶ በመኝታው ተኛ ። እግዚአብሔርም መጥቶ እንደ መጀመሪያው በፊቱ ቁሞ ጠራው ። ሳሙኤልም እኔ ባሪያህ እሰማሃለሁና ጌታዬ በል ተናገር አለው እግዚአብሔርም ሳሙኤልን የሰማው ሁሉ ሁለቱን ጆሮዎቹን ይይዝ ዘንድ እነሆ እኔ በእስራኤል ላይ የተናገርሁት ቃሌን አደርጋለሁ በዚያችም ቀን በኤሊና በወገኑ ላይ የተናገርኹትን ሁሉ አጸናለሁ እጀምራለሁ እፈጽማለሁም = ልጆቹ የእግዚአብሔርን ቃል አቃልለዋልና እርሱም አልገሠጻቸውምና በልጆቹ ኃጢአት እኔ ወገኑን ለዘላለም እንደምበቀለው ነገርሁት ። ስለዚህም ነገር በዕጣንም ቢሆን በመሥዋዕትም ቢሆን የኤሊ የወገኑ ኃጢአት እስከ ዘላለሙ ድረስ እንዳይሠረይ ራሴ እንዲህ 那叫AD በኤሊ ወገኖችና ልጆች ላይ እግዚአብሔር የተናገረው ሁሉ ተፈጸመ ። ከዚህም በኋላ የቂስ ልጅ ሳኦልን ቀብቶ ለእስራኤል ልጆች ያነግሠው ዘንድ እግዚአብሔርሳሙኤልን አዘዘው እንዲእነግሥላቸው ለምነዋልና ። ሳኦልም የልዑልን ትእዛዝ በተላለፈ ጊዜ ዳግመኛ ለእስራኤል ንጉሥ ሊሆን የዕሴይ ልጅ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ ይህን ነቢይ ሳሙኤልን ዳግመኛ አዘዘው ። ይህም ነቢይ ሳሙኤል በሕይወት በኖረበት ዘመን ሁሉ እስራኤልን አስተዳደራቸው ። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ታላቅ ነቢይ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ዕለት ቅዱስ ሉክያኖስ ከሌሎች አራት ሰማዕታት ጋራ ሰማዕት ሆነ ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ የጣዖት ካህን ነበረ የሰማዕታትንም መከራቸውን በእሳት ሲአቃጥሏቸውና ሕዋሳታቸውን ሲቆራርጧቸው ሲሰቅሏቸው ከእሳት ምድጃ ውስጥም ሲጥሏቸው ምንም ምን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው በእየ ጊዜ ከዚህ ሥራ የተነሣ እደነቀ ክብር ይግባውና በጌታችን አመነ ያገለግላቸው የነበሩ ጣዖታት ከእሳት ቢጥሏቸው ፈጥነው ይቃጠላሉ እንጂ ይህን ሥራ ሊሠሩ እንደማይችሉ ተረድቷልና ። ዳግመኛም እንዲህ አለ ይህን ድንቅ ሥራ የሚሠራ እምላክስ በእውነት እርሱ አምላክ ነው ። ከዚህ በኋላም በንጉሥ ፊት እኔ ክርስቲያን ነኝ ክብር ይግባውና በክርስቶስ እምናለሁ ብሎ በግልጥ ጮኾ ተናገረ ። ንጉሡም ወደርሱ አቅርቦ ጣዖት ማምለክን እንዳይተው መከረው ወደ አምልኮ ጣዖት ይመለስ እንደሆነ ብሎ ብዙ ቃል ኪዳኖችን ገባላት ። እርሱ ግን አልሰማውም ሥቃዩንም አልፈራም ከዚህም በኋላ ንጉሡ ጽኑዕ ሥቃይን ሊአሠቃየው ጀመረ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት መንጋጋውንም በደንጊያ እንዲሰብሩት ታላቅ ግርፋትንም እንዲገርፉት አዘዘ ። ከዚህ በኋላም አራት ክርስቲያን እሥረኞች ቀረቡና ከእርሱ ጋራ አቆሟቸው ንጉሡም ለአማልክት ዕጣን ዕጠኑ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሥቃይን አሠቃያችኋለሁ አላቸው ። እነርሱም ለስሕተቱ አልታዘዙለትም በላያቸውም ተቆጥቶ በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመራቸው ያንጊዜ ዝናብ ዘነበ እሳቱንም አጠፋው ። ቅዱስ ሉክዮስን ግን እንደ አምላክህ እሰቅልሃለሁ ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ እንዲሰቅሉት አዘዘ በረጃጅም ችንካሮችም ሥጋውን ሁሉ ቸነከሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ ። እነዚያን አራቱን ሰዎችም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይድረሰን ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ቀን የዮሐንስና የጳጳስ አርልክሳ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ሰኔ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ ፪.ቅዱስ ሉክያኖስ ሰማዕት ፫.ቅዱስ ዮሐንስ ወርኀዊ በዓላት ፩.አባ በርሱማ ሶርያዊ ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት ፪.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊ ፫ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ ዘ.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን ፯.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት ፭.አባ መልከ ጸዴቅ ዘሚዳ ኢትዮዽያዊ እንግዲህ ምን እላለሁ ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና ። እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ ። ጽድቅንም አደረጉ... ዕብ 11 ÷32 ‪@yekidusantarik‬ ‪@swromariyamgedam‬ ‪@EOTCOrthodoxChannel1‬

የሰኔ 5 ሥንክሳር #ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ #ለባሲተ ክርስቶስ ማርታ#አባ ብሶይና ቢፋሞን#አቡዬ ጻድቁ#ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት
▶︎

የሰኔ 5 ሥንክሳር #ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ #ለባሲተ ክርስቶስ ማርታ#አባ ብሶይና ቢፋሞን#አቡዬ ጻድቁ#ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት

ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሙሉ ክፍል | Samuel Asres| ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Orthodox Tewahido | 19 October 2023
▶︎

ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሙሉ ክፍል | Samuel Asres| ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Orthodox Tewahido | 19 October 2023

ሰይፈ ሥላሴ ጸሎትን እንዴት አንጸልይ? አስደናቂው የሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ጥቅሞች! በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ዙሪያ የተሰጠ ሰፊ ማብራሪያ!
▶︎

ሰይፈ ሥላሴ ጸሎትን እንዴት አንጸልይ? አስደናቂው የሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ጥቅሞች! በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ዙሪያ የተሰጠ ሰፊ ማብራሪያ!

ንኽንዕወት ንእግዚኣብሄር ሃዲእና ንጸበዮ
▶︎

ንኽንዕወት ንእግዚኣብሄር ሃዲእና ንጸበዮ

የጥቅምት 27 ሥንክሳር#አቡነ መባዕ ፅዮን#ስቅለት#እንኳን አደረሣችሁ
▶︎

የጥቅምት 27 ሥንክሳር#አቡነ መባዕ ፅዮን#ስቅለት#እንኳን አደረሣችሁ

መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit- ማክሰኞ (መዝ 31- 60 )
▶︎

መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit- ማክሰኞ (መዝ 31- 60 )

မဟာသမယသုတ်၊ မေတ္တာသုတ်၊ ဓာရဏပရိတ်#စီးပွားတက် #ကံပွင့်လာက်ပွင့် #မနက်တိုင်းဖွင့် #တရားတော်များ
▶︎

မဟာသမယသုတ်၊ မေတ္တာသုတ်၊ ဓာရဏပရိတ်#စီးပွားတက် #ကံပွင့်လာက်ပွင့် #မနက်တိုင်းဖွင့် #တရားတော်များ

የሰኔ 10 ሥንክሳር#ቅድስት ቤተክርስቲያን #ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ#ዋርስኖፋ እና አውሎጊስ ሰማዕታት#ቅዱስ መስቀል
▶︎

የሰኔ 10 ሥንክሳር#ቅድስት ቤተክርስቲያን #ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ#ዋርስኖፋ እና አውሎጊስ ሰማዕታት#ቅዱስ መስቀል

መጽሐፈ ሲራክ | Samuel Asres| ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Orthodox Tewahido | 12 January 2024
▶︎

መጽሐፈ ሲራክ | Samuel Asres| ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Orthodox Tewahido | 12 January 2024

መዝሙረ ዳዊት መፀለይ ጀምሩ! | ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan New Sibket 2026
▶︎

መዝሙረ ዳዊት መፀለይ ጀምሩ! | ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan New Sibket 2026

የሰኔ 4 ሥንክሳር#ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት#ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ#ቅዱስ ሳኑሲ#አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ #ቅዱስ አሞን
▶︎

የሰኔ 4 ሥንክሳር#ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት#ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ#ቅዱስ ሳኑሲ#አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ #ቅዱስ አሞን

አቡነ ተክለሃይማኖት ታሪክ  (ተራኪ ዘላለም ኃይሉ)
▶︎

አቡነ ተክለሃይማኖት ታሪክ (ተራኪ ዘላለም ኃይሉ)

መዝሙረ ዳዊት በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ ታላቁ የጸሎት መጽሐፍ  ሙሉው (Mezmure Dawit) | Book of King David [EDUCATIONAL video]
▶︎

መዝሙረ ዳዊት በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ ታላቁ የጸሎት መጽሐፍ ሙሉው (Mezmure Dawit) | Book of King David [EDUCATIONAL video]

🔴 ክረምቱ ሳይመጣ ፈጥነህ ና || ለቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ | ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ |Aba Gebrekidan New Sibket 2026
▶︎

🔴 ክረምቱ ሳይመጣ ፈጥነህ ና || ለቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ | ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ |Aba Gebrekidan New Sibket 2026

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስዕሏ ስር ይህን አድርጉ ሀሳባችሁ ይሳካል ፣ አባ ገብረኪዳን
▶︎

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስዕሏ ስር ይህን አድርጉ ሀሳባችሁ ይሳካል ፣ አባ ገብረኪዳን

ሰኔ ጎልጎታ sene golgota
▶︎

ሰኔ ጎልጎታ sene golgota

የሉቃስ ወንጌል | Samuel Asres | ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Ortodox Tewahido | November 14,2022
▶︎

የሉቃስ ወንጌል | Samuel Asres | ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Ortodox Tewahido | November 14,2022

የሰላም ለኪ ወይም የጸሎተ ማርያም ምስጢር! የጸሎተ ማርያም ጸሎት 21 ጥቅሞች! የሁሉ ችግር መፍትሔ ጸሎት!
▶︎

የሰላም ለኪ ወይም የጸሎተ ማርያም ምስጢር! የጸሎተ ማርያም ጸሎት 21 ጥቅሞች! የሁሉ ችግር መፍትሔ ጸሎት!

🔴የተፈጠርነው ክርስቶስን ለመምሰል ነው || ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል #ዲያቆን_ቀዳሜጸጋ_ዮሐንስ #kendilPodcast
▶︎

🔴የተፈጠርነው ክርስቶስን ለመምሰል ነው || ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል #ዲያቆን_ቀዳሜጸጋ_ዮሐንስ #kendilPodcast

ሰበር ዜና  ሀሙስ ሰኔ 18/2018 የሰአቱ መረጃዎች!|Ethiopian news today|Amhara fono|ethio news 25 June 2026
▶︎

ሰበር ዜና ሀሙስ ሰኔ 18/2018 የሰአቱ መረጃዎች!|Ethiopian news today|Amhara fono|ethio news 25 June 2026