የጥቅምት 27 ሥንክሳር#አቡነ መባዕ ፅዮን#ስቅለት#እንኳን አደረሣችሁ

ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት 27 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ሃያ ሰባት በዚች ቀን ቅዱስ አባት የሀገረ ቃው ኤጲስቆጶስ አባ መቃርስ አረፈ ። ለዚህም ቅዱስ የዝንጉዎችን ምክር ተከትሎ ያልሔደ፣ በኃጢአተኞችም ጎዳና ያልተጓዘ፣ በዘባቾችም መቀመጫ ያልተቀመጠ፣ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ፈቃዱ የሆነ እንጂ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያነብ የሚያስተምር ብፁዕ ነው የሚለው የነቢይ ዳዊት ቃል ተፈጽሞለታል ። ይህ አባ መቃርስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ በመክሊት ነግዶ ዕጥፍ አድርጎ አትርፎአልና እግዚአብሔርም በእጆቹ ያደረጋቸውን ታላላቆች ድንቆች ተአምራት ስንቱን እንናገራለን ። ስለርሱም እንዲህ ተባለ እርሱ በሀገረ ቃው ተሾሞ በወንበር ተቀምጦ ሕዝብን በሚያስተምራቸው ጊዜ ዘወትር ያለቅሳል ። ከደቀ መዛሙርቱም አንዱ እጅግ የሚወደው አማለውና አባቴ ሆይ ሁል ጊዜ ለምን ታለቅሳለህ ንገረኝ አለው እርሱም ስለ መሐላው ፈርቶ ዘይት በብርሌ ውስጥ እንደሚታይ የወገኖቼን ኃጢአታቸውን የከፋች ሥራቸውንም በማይና በምመለከት ጊዜ አለቅሳለሁ ብሎ መለሰለት ። ሁለተኛ ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ተቀምጦ የየአንዳንዱን የሰውን ሥራ መላእክት ሲያቀርቡለት አየው በዚያንም ጊዜ እንዲህ የሚል ቃል ሰማ ኤጲስቆጶስ ሆይ ለምን ቸለል ትላለህ ሕዝቡን አትገሥጻቸውምን አታስተምራቸውምን እርሱም አቤቱ እነርሱ ትምርቴን አይቀበሉም ብሎ መለሰ ። ሁለተኛም እንዲህ አለው ለኤጲስቆጶስ ሕዝቡን ማስተማር ይገባዋል ትምርቱን ካልተቀበሉ ግን ደማቸው በራሳቸው ይሆናል ። ከዚህም በኋላ መናፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስ ወደ ሰበሰበው ጉባኤ ከሊቀ ጳጳሳቱ ዲዮስቆሮስ ጋርይሔድ ዘንድ ጠሩት የተሰበሰቡትም አንዱን ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ የሚሉ ናቸው በደረሰም ጊዜ ስለ ልብሱ አዳፋነት ወደ ንጉሥ አዳራሽ መግባትን ከለከሉት አባ ዲዮስቆሮስም ከእርሱ ጋር እንዲአስገቡት ጳጳስ መሆኑን ነገራቸው ። በገቡም ጊዜ አንዱን ክርስቶስን ሁለት ባሕርይ አድርገው ትስብእቱን ከመለኮቱ እንደለዩት እምነታቸውን ሰሙ ስለዚህም ንጉሡንና ጉባኤውን አወገዙአቸው እሊህ አባቶቻችን አባ ዲዮስቆሮስና አባ መቃርስ ስለ ቀናች ሃይማኖታቸው ነፍሳቸውን ለሞት አሳልፎ ለመስጠት ቆርጠዋልና ንጉሡም ወደ ደሴተ ጋግራ አጋዛቸው ። ከዚያም ከምእመን ነጋዴ ጋር ወደ እስክንድርያ አባ ዲዮስቆሮስን ሰደደው እርሱ ለአባ መቃርስ ትንቢት ተናግሮለት ነበርና እንዲህ ብሎ አንተ ግን በእስክንድርያ አገር የሰማዕትነት አክሊል ትቀበል ዘንድ አለህ ። አባ መቃርስም ወደ እስክንድርያ ሲደርስ በዚያን ጊዜ የመናፍቁ የንጉሥ መርቅያን በውስጡ የከፋች ሃይማኖቱ የተጻፈበት የመልእክት ደብዳቤ ደረሰ መልእክተኛውንም እንዲህ ብሎ አዞታል በእኛ ሃይማኖት አምኖ በዚህ መዝገብ ውስጥ መጀመሪያ የጻፈ በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ይሁን የሚል ነው አብሮታራ የሚባል አንድ ሰው ተቀዳድሞ በውስጡ ሊጽፍ ያንን መጽሐፍ ተቀበለ ቅዱስ አባ መቃርስም እንዲህ አለው ከእስክንድርያ አገር በሔደ ጊዜ ከእኔ በኋላ አንተ በቤተ ክርስቲያን የሠለጠንክ ትሆናለህ ብሎ የነገረህን የአባ ዲዮስቆሮስን ቃሉን አስብ ያን ጊዜ አብሮታራ ያንን ቃል አስታውሶ በዚያ በረከሰ መጽሐፍ ላይ ሳይጽፍ ቀረ ። የንጉሡም መልክተኛ አባ መቃርስ በንጉሥ ሃይማኖት እንደማያምን በአወቀ ጊዜ ተቆጥቶ ከኵላሊቱ ላይ ረገጠው ያን ጊዜም ሙቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ሥጋውንም ምእመናን ወስደው ከነቢይ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት ወደ ወደደው ክርስቶስም የመንግሥት ዘውድን ተቀዳጅቶ ሔደ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋርትኑር ለዘላለሙ አሜን ። አርኬ ሰላም እብል ብንሣንየ ድኅንፃ። መሰንቆ መዝሙር ዘያስተጒሥሕ ድምጻ። ለመፍቀሬ ጽድቅ መቃርስ ዘትጸልእ ግብረ ዓመጽ እደ ገ ደቀሠከ ሶበ አንበርከ በገጻ። ብእሲተ መኣራርን ሓይወት ወነጽሓት እምለምጻ። በዚችም ቀን በዋሻ የሚኖር የጳውሎስና የዮልያኖስ ከእነርሱም ጋር ላሉ ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው በጸሎታቸውም እግዚአብሔር ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ቀን የመድኃኒታችን የሰቅለቱ መታሰቢያ ነው ። አርኬ ሰላም ሰላም ፈታዊ ዘቀደሶ ። ሀገረ ጽጌ የአህዝ ምስለ ጻድቃን በተዋርሶ ተዘከረኒ ክርስቶስ አመ ትመጽእ ለተዋቅሶ። በእንተ መቃርስ ጻድቅ እንተ መጠወ ነፍሶ። ወበበትረ መስቀል ዘይዝሕት ርእሶ። ጥቅምት ፳፯ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ፩.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፪.ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ ፫.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ ፬.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ ወርኀዊ በዓላት ፩.ቅዱስ መቃርስ የመነኮሳት ሁሉ አለቃ ፪.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ፫.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት ንጉሠ ኢትዮዽያ ፬.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት ፭.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸክሟል ፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው ። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ ፥ በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን ። ኢሳ ፭፫፥፬-፯ ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተፀምዱኩ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘእቱየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውክፋ እምእለ አብ ዑቁ ብኩላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሂቅ እምንኡስ ሕፃን ። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ። ጌታ ሆይ ከብልፅግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል ። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን ።

የጥቅምት 30 ሥንክሳር#መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ #ቅዱስ ማርቆስ#በገድል የተጠመደ ባሕታዊ አባ አብርሐም ገዳማዊ
▶︎

የጥቅምት 30 ሥንክሳር#መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ #ቅዱስ ማርቆስ#በገድል የተጠመደ ባሕታዊ አባ አብርሐም ገዳማዊ

የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሙሉ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​@Meba_tv
▶︎

የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሙሉ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​@Meba_tv

🔴ቅዱስ_ሚካኤል  ሰኔ [፲፪]❗ቅዱስ ባሕራን❗ቅድስት አፎሚያ❗ቅዱስ ላሊበላ የኢትዮጵያ ንጉስ.....ማናቸው❓ ሰኔ አስራ ሁለት ለምን ይከበራል❓
▶︎

🔴ቅዱስ_ሚካኤል ሰኔ [፲፪]❗ቅዱስ ባሕራን❗ቅድስት አፎሚያ❗ቅዱስ ላሊበላ የኢትዮጵያ ንጉስ.....ማናቸው❓ ሰኔ አስራ ሁለት ለምን ይከበራል❓

📍መነኩሴ ከአንድ ገዳም አይወጣም‼️መነኩሴ ከተማ ከተገኘ ምራቅ ይተፋበታል// አባ ገብረኪዳን @menkermedia21
▶︎

📍መነኩሴ ከአንድ ገዳም አይወጣም‼️መነኩሴ ከተማ ከተገኘ ምራቅ ይተፋበታል// አባ ገብረኪዳን @menkermedia21

ለምዕራባዊያን ሴራ ሐሰተኛ አጥማቂያን መሳሪያ አልሆኑም ወይ | መምህር ገብረመድኅን እንየው
▶︎

ለምዕራባዊያን ሴራ ሐሰተኛ አጥማቂያን መሳሪያ አልሆኑም ወይ | መምህር ገብረመድኅን እንየው

#ኑ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ /ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 🔴ምክረ አበው @mikreabewmedia
▶︎

#ኑ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ /ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 🔴ምክረ አበው @mikreabewmedia

የአንበሶቹን አፍ የዘጋ የእምነት ኃይል ነብዩ ዳንኤል#biblestories #history
▶︎

የአንበሶቹን አፍ የዘጋ የእምነት ኃይል ነብዩ ዳንኤል#biblestories #history

ናይ ንግሆ  ጸሎት
▶︎

ናይ ንግሆ ጸሎት

God Says:"TAKE THIS MESSAGE SERIOUSLY, BECAUSE ONLY YOU ARE SEEING IT"/God Message Now/God Message
▶︎

God Says:"TAKE THIS MESSAGE SERIOUSLY, BECAUSE ONLY YOU ARE SEEING IT"/God Message Now/God Message

የቆሮንጦስ መልዕክት ሚስጥር - መባዕ ቲቪ (Meba TV)
▶︎

የቆሮንጦስ መልዕክት ሚስጥር - መባዕ ቲቪ (Meba TV)

#ትረኻ_ዕላል ኣባ መቃርስ ምስቲ መልኣኽ እግዚኣብሔር ዝገበሮ ዕላል ኣብቲ ምድረ በዳ//ቤተልሔም 21
▶︎

#ትረኻ_ዕላል ኣባ መቃርስ ምስቲ መልኣኽ እግዚኣብሔር ዝገበሮ ዕላል ኣብቲ ምድረ በዳ//ቤተልሔም 21

የቅዱስ ገብርኤል ልብን ደስ የሚያሰኙ የመዝሙር ስብስቦች #Kidus Gebriel Mezmur collection #eotc #orthodoxmezmur #habesha
▶︎

የቅዱስ ገብርኤል ልብን ደስ የሚያሰኙ የመዝሙር ስብስቦች #Kidus Gebriel Mezmur collection #eotc #orthodoxmezmur #habesha

ዘይተሰምዑ ተኣምራት ኣቡነ ዓብየ እግዚእ (ኣብየዝጊ)— ሙታን ዘተንሥኡን ኣራዊት ዝኣዘዙን ፍሉይ ትግራዋይ ጻድቕ | ሠለስቱ ምእት"✨
▶︎

ዘይተሰምዑ ተኣምራት ኣቡነ ዓብየ እግዚእ (ኣብየዝጊ)— ሙታን ዘተንሥኡን ኣራዊት ዝኣዘዙን ፍሉይ ትግራዋይ ጻድቕ | ሠለስቱ ምእት"✨

አቡነ ኤርምያስ አደንጋጭ ዜና አሰሙ በእንባ የታጀቦ አባቶችን ተማፀኑ ጳጳሱ ቤተክርስቲያን እየፈረሰች ነው አሉ
▶︎

አቡነ ኤርምያስ አደንጋጭ ዜና አሰሙ በእንባ የታጀቦ አባቶችን ተማፀኑ ጳጳሱ ቤተክርስቲያን እየፈረሰች ነው አሉ

| ባለንበት እንቁም|የመላክት አለቃ|የታመንክ የነፍስ ወዳጅ|ገብርኤል|የቅዱስ ገብርኤል መዝሙሮች @Dagmawi_Tube #spot church #orthodox
▶︎

| ባለንበት እንቁም|የመላክት አለቃ|የታመንክ የነፍስ ወዳጅ|ገብርኤል|የቅዱስ ገብርኤል መዝሙሮች @Dagmawi_Tube #spot church #orthodox

የኢትዮጵያ መስቀል ከሌሎች እንዴት እንደሚለይ! በአንድ መስቀል ውስጥ 3 ነገሮች! መምህር ዘበነ ለማ
▶︎

የኢትዮጵያ መስቀል ከሌሎች እንዴት እንደሚለይ! በአንድ መስቀል ውስጥ 3 ነገሮች! መምህር ዘበነ ለማ

ኢትዮጵያ ለምን ተከለከለች? || የተከለከለው የኢትዮጵያ ታሪክ || ታላላቅ ሚስጥሮች ሲጋለጡ || ደራሲ አሸናፊ ፈንቴ
▶︎

ኢትዮጵያ ለምን ተከለከለች? || የተከለከለው የኢትዮጵያ ታሪክ || ታላላቅ ሚስጥሮች ሲጋለጡ || ደራሲ አሸናፊ ፈንቴ

🔴 ክረምቱ ሳይመጣ ፈጥነህ ና || ለቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ | ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ |Aba Gebrekidan New Sibket 2026
▶︎

🔴 ክረምቱ ሳይመጣ ፈጥነህ ና || ለቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ | ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ |Aba Gebrekidan New Sibket 2026

መዝሙረ ዳዊት 31-35| Samuel Asres | ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Ortodox Tewahido |April 3,2022
▶︎

መዝሙረ ዳዊት 31-35| Samuel Asres | ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Ortodox Tewahido |April 3,2022

የቅዱስ ገብርኤል መዝሙሮች ስብስብ - የተመረጡ የቅዱስ ገብርኤል መዝሙሮች|St.Gabriel Ethiopian Orthodox Mezmur Collection 2026
▶︎

የቅዱስ ገብርኤል መዝሙሮች ስብስብ - የተመረጡ የቅዱስ ገብርኤል መዝሙሮች|St.Gabriel Ethiopian Orthodox Mezmur Collection 2026