የሰኔ 13 ሥንክሳር#ቅዱስ ገብርኤል ለዳንኤል የተላከበት#አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም #ቃይናን #ማትያን#በወርቅ ሣህን የሚመገበው ዓይኑ ጠፋ

የሰኔ 13 ሥንክሳር አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ አረፈ ። ይህም ቅዱስ በቅዱስ አባ ኢላርዮንና በታላቁ አባ ኤስድሮስ ገዳም በታናሽነቱ መነኰሰ ከአባ ኤጲፋንዮስ ጋራም በገድል በመጠመድ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ የደግነቱ የተጋድሎውና የትሩፋቱ ዜናም በቦታው ሁሉ ተሰማ ። ከዚህም በኋላ ኤጲፋንዮስ በቆጵሮስ ሀገር ኤጲስቆጶስነት ከተሾመ በኋላ እርሱን መርጠው በኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስነት ሾሙት ። ይህ አባት በሹመት በነበረ ጊዜ ሰይጣን በገንዘብ ፍቅርና በዚህ ዓለም ክብር አሳተው ብዙ ገንዘብ ሰብስቦ ለማዕዱ የሚመገብበት የወርቅና የብር ሣህን አሠርቶ ነበርና ለድኖችና ለምስኪኖችም መራራትን ተወ ምንም የእንጀራ ቁራሽ አይሰጣቸውም ነበር ። ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሰማ ጊዜ የቀድሞውን ተጋድሎውንና የዓለም መናኒነቱን ፍቅሩንም አስታውሶ እጅግ አዘነ ከቀድሞ ጀምሮ በመንፈስ ወንድሙና ወዳጁ ነበርና ። ስለዚህም ብፁዕ ኤጲፋንዮስ ከቆጵሮስ ተነሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አባ ዮሐንስ መጣ አባ ዮሐንስን በጥበብ ከስሕተት ያድነው ዘንድም ክብር ይግባውና የጌታችን መቃብር ባለበት ቤተ መቅደስ ለመስገድ እንደመጣ አመካኘ ። በተገናኙም ጊዜ አባ ዮሐንስ አባ ኤጲፋንዮስን ወደ ቤቱ አስገብቶ ማዕድ አዘጋጀለት በማዕድም ላይ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ሣህኖችን አኖረ አባ ኤጲፋንዮስም በልቡ አዘነ ለድኆችና ለምስኪኖች ርኃራኄ እንደሌለውም አየ ። ከዚህም በኋላ ከእርሱ ዘንድ ወጥቶ በኢየሩሳሌም ካሉ ገዳማት በአንዱ አደረ ። ምክንያትም አዘጋጀ ይህም እንዲህ ነው ወደ አባ ዮሐንስ እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ላከ ወንድሜ ሆይከቆጵሮስ አገር ሽማግሌዎችና የሕዝቡ መምህራን ወደ እኔ መጥተዋልና በእነርሱ ፊት ታከብረኝ ዘንድ ከወርቅና ክብርየተሠሩ የማዕድ ዕቃዎችን ይመገቡባቸው ዘንድ እንድትልክልኝ እሻለሁ እርሱም ላከለት ያን ጊዜም አባ ኤጲፋንዮስ ዕቃዎቹን ወስዶ ሸጣቸው ዋጋቸውንም ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወታቸው ። ከዚህም በኋላ በተገናኙ ጊዜ አባ ዮሐንስ አባ ኤጲፋንዮስን የላኩልህን የማዕድ ዕቃዎቼን መልስ አለው እርሱም እሺ አለው እንዲሁም ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ ነገረው አባ ኤጲፋንዮስም እሺ አለው በአንዲት ዕለትም ክብር ይግባውና የጌታችን መቃብር ካለበት ቤተ መቅደስ ሲወጣ አገኘው ያን ጊዜም ያዘውና ገንዘቤን እስከምትሰጠኝ አልለቅህም አለው አባ ኤጲፋንዮስም ክብርይግባውና ወደ ጌታችን ጸለየ በዚያን ጊዜም የአባ ዮሐንስ ዐይኖቹ ታወሩ ። ያን ጊዜም ይቅር ብሎት ዐይኖቹን ይገልጥለት ዘንድ እያለቀሰ ወደ አባ ኤጲፋንዮስ ማለደ እርሱም መጸጸቱን አይቶ አንዲቱን ዐይኑን ገለጠለት እንዲህም አለው ነፍስህን ታስብ ዘንድ አንዲቷ ዐይንህ ዕውርት እንደሆነች ትቶልሃል ። ገሠጸውም እነሆ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቀድሞ ድካምህን ብርታትህንና ተጋድሎህን አስቦ ራራልህ ከስሕተትም አዳነህ አለው ። የማዕድ ዕቃዎችንም እኔ እንደሸጥኳቸውና ስለ አንተ ለድኆችና ለምስኪኖች እንደ መጸወትኳቸው ዕወቅ አንተ በገንዘብ ፍቅር መጠመድህንና የቀድሞውን መልካም ሥራህን መተውህን ብሰማ ነው እንጂ ከቆጵሮስ ወደ ኢየሩሳሌም አልመጣም ነበር ። ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ቅዱስ ዮሐንስ ከእንቅልፍ እንደነቃ ሆነ በርኅራኄም መንገድ ሔደ ያለውንም ጥሪቱን ሁሉ ሰጠ ምንም ምን አላስቀረም ። ልብሶቹንም ለተራቆቱ ሰጠ በሞተ ጊዜ አንድ አላድ ከዚያም በታች ከእርሱ ዘንድ እስከ አልተገኘ ድረስ ሰጠ ። ጌታችንም የመፈወስ ሀብትን ሰጠው ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ ከተቀደሰ ዘይት እየቀባ ፊታቸውንም አዳኝ በሆነ በመስቀል ምልክት እያማተበ ደዌ ያለባቸውን ሁሉ አዳናቸው ። መልካም ተጋድሎውን ፈጽሞ ክብር ይግባውና ጌታችንን አገልግሎ በሰላም አረፈ ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ዕለት ለከበረ መልአክ አዲስ የምሥራች ነጋሪ ለሆነ የመላእክት አለቃ ገብርኤል በዓልን ያደርጉለት ዘንድ መምህራን በግብጽ አገር ለክርስቲያን ወገኖች ሥርዓት ይህ የከበረ መልአክ የእስራአል ልጆች ከሰይጣን እጅ ስለመዳናቸውና ከምርኮም ስለ መመለሳቸው ነቢዩ ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር በሚጸልይና በሚማልድ ጊዜ አስቀድሞ የተገለጠለትና ስለ ድኅነታቸውና ስለ ቤተ መቅደስም መታነፅ የነገረው ነውና ዳግመኛም ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ መምጣትና መገደል ስለ ቤተ መቅደስም መፍረስ ከዚያም በኋላ ስለ ሐሳዊ መሲሕ መምጣት ነገረው ለመድኀን መምጣትም በሱባዔ የወሰናቸው ዘመናት በተፈጸሙ ጊዜ ይህ የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ወደ ቅድስት ድንግል ወደ እመቤታችን ማርያም መጣ ዓለምን ስለ ማዳን የእግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ስለመሆኑ ነገራት ። ስለዚህም የበዓላቶቹን መታሰቢያ እንድናደርግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን አዘዙን ። እኛም ከጠላታችን ሰይጣን እጅ ያድነን ዘንድ ለመንግሥቱም የተዘጋጀን ያደርገን ዘንድ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ስለ እኛ እንዲማልድ እንለምነው ። ልዕልና ችሎታም ገንዘቡ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የዚህም የከበረ መልአክ ረድኤቱ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ቀን የኄኖስ ልጅ የቃይናን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ። ቃይናንም መቶ ሰብዓ ዓመት ኖረ መላልዔልንም ወለደው መላልዔልንም ከወለደው በኋላ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ኖረ ሴቶች ልጆችና ወንዶች ልጆችንም ወለደ ። የቃይናን መላ ዘመኑ ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ነው ከዚያም በኋላ አረፈ በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ቀን የሰማዕቱ አቡላግና የሁለት መቶ ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው ስለ ዕውነትም የተሰደደ የአባታችን የማትያንም መታሰቢያው ነው ። እግዚአብሔር በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። ሰኔ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ወደ ዳንኤል የወረደበት ፪.አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም ፫.አባታችን ቃይናን ከአዳም 4ኛ ትውልድ ፬.አባ ማትያን ጻድቅ ስደተኛው አባት ፩.እግዚአብሔር አብ ወርኀዊ በዓላት ፪.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት ፫.99ኙ ነገደ መላዕክት ፩.ቅዱስ አስከናፍር ፭.13ቱ ግኁሳን አባቶች ፮.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ ፯.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ ። በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ ። አስተማረኝም: ተናገረኝም ። እንዲህም አለ ዳንኤል ሆይ ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ ። ዳን 9÷20_22 ‪@yekidusantarik‬ ‪@EOTCOrthodoxChannel1‬ ‪@swromariyamgedam‬

🔴 ክረምቱ ሳይመጣ ፈጥነህ ና || ለቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ | ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ |Aba Gebrekidan New Sibket 2026
▶︎

🔴 ክረምቱ ሳይመጣ ፈጥነህ ና || ለቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ | ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ |Aba Gebrekidan New Sibket 2026

শক্তিশালী রুকাইয়া আয়াত | জ্বীন, ভূত, যাদু ও বদ নজর থেকে মুক্তি | Powerful Ruqyah Ayat
▶︎

শক্তিশালী রুকাইয়া আয়াত | জ্বীন, ভূত, যাদু ও বদ নজর থেকে মুক্তি | Powerful Ruqyah Ayat

የሰኔ 19  ሥንክሳር#ሐዲስ ጊዎርጊስ ሰማዕት#በአንበሳ ጀርባ የበረረ አባት#አባ ቢሶይ አኖብ  #የጠራ ወርቅ#5 ጭፍሮች ሰማዕታት
▶︎

የሰኔ 19 ሥንክሳር#ሐዲስ ጊዎርጊስ ሰማዕት#በአንበሳ ጀርባ የበረረ አባት#አባ ቢሶይ አኖብ #የጠራ ወርቅ#5 ጭፍሮች ሰማዕታት

የሰኔ 17 ሥንክሳር #አባ ለትጹን #ገሪማ ገረምከነ#አባ ጰላሞን #ቅዱሳን ጻድቃን#እንኳን ሰው እፅዋት የታዘዙለት አባት
▶︎

የሰኔ 17 ሥንክሳር #አባ ለትጹን #ገሪማ ገረምከነ#አባ ጰላሞን #ቅዱሳን ጻድቃን#እንኳን ሰው እፅዋት የታዘዙለት አባት

ለምዕራባዊያን ሴራ ሐሰተኛ አጥማቂያን መሳሪያ አልሆኑም ወይ | መምህር ገብረመድኅን እንየው
▶︎

ለምዕራባዊያን ሴራ ሐሰተኛ አጥማቂያን መሳሪያ አልሆኑም ወይ | መምህር ገብረመድኅን እንየው

የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሙሉ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​@Meba_tv
▶︎

የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሙሉ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​@Meba_tv

የጥቅምት 14 ሥንክሳር@ቅዱስ ሙሴ መርዓዊ @ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ@ ይህንን ያውቁ ኖሯል?@ሁለት ተመሳሳይ ቅዱሳን በአንድ ቀን የሚከበሩ
▶︎

የጥቅምት 14 ሥንክሳር@ቅዱስ ሙሴ መርዓዊ @ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ@ ይህንን ያውቁ ኖሯል?@ሁለት ተመሳሳይ ቅዱሳን በአንድ ቀን የሚከበሩ

👉 በጣም አጭሩ ጸሎት ⭕️ እንዲህ ከጸለያቹ የማይፈታ ችግር የለም | እጅግ ድንቅ ስብከት በፕሮፌሰሩ መነኩሴ አባ ኃይለ ገብርኤል | Orthodox Sibket
▶︎

👉 በጣም አጭሩ ጸሎት ⭕️ እንዲህ ከጸለያቹ የማይፈታ ችግር የለም | እጅግ ድንቅ ስብከት በፕሮፌሰሩ መነኩሴ አባ ኃይለ ገብርኤል | Orthodox Sibket

God Says:"TAKE THIS MESSAGE SERIOUSLY, BECAUSE ONLY YOU ARE SEEING IT"/God Message Now/God Message
▶︎

God Says:"TAKE THIS MESSAGE SERIOUSLY, BECAUSE ONLY YOU ARE SEEING IT"/God Message Now/God Message

የንጉሥ ሰለሞን ቀለበት የት ነው ያለው? አጋንንትን የሚያዝዘው የሰለሞን ቀለበት ሚስጥር!  | Dr. Rodas | Awtar
▶︎

የንጉሥ ሰለሞን ቀለበት የት ነው ያለው? አጋንንትን የሚያዝዘው የሰለሞን ቀለበት ሚስጥር! | Dr. Rodas | Awtar

የድንግል ማርያም ሞት - አስተርዮ ማርያም - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​@Meba_tv
▶︎

የድንግል ማርያም ሞት - አስተርዮ ማርያም - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​@Meba_tv

የኢትዮጵያ መስቀል ከሌሎች እንዴት እንደሚለይ! በአንድ መስቀል ውስጥ 3 ነገሮች! መምህር ዘበነ ለማ
▶︎

የኢትዮጵያ መስቀል ከሌሎች እንዴት እንደሚለይ! በአንድ መስቀል ውስጥ 3 ነገሮች! መምህር ዘበነ ለማ

📍መነኩሴ ከአንድ ገዳም አይወጣም‼️መነኩሴ ከተማ ከተገኘ ምራቅ ይተፋበታል// አባ ገብረኪዳን @menkermedia21
▶︎

📍መነኩሴ ከአንድ ገዳም አይወጣም‼️መነኩሴ ከተማ ከተገኘ ምራቅ ይተፋበታል// አባ ገብረኪዳን @menkermedia21

الرقية الشرعية للشفاءمن السحروالعين والحسد حصن من الشيطان رقية البيت والاولاد بصوت القارئ سعيد حمدان
▶︎

الرقية الشرعية للشفاءمن السحروالعين والحسد حصن من الشيطان رقية البيت والاولاد بصوت القارئ سعيد حمدان

🔴ለእግዚአብሔር የምስጢሩ  ገዳም አበ ምኔት
▶︎

🔴ለእግዚአብሔር የምስጢሩ ገዳም አበ ምኔት

የሰኔ 10 ሥንክሳር#ቅድስት ቤተክርስቲያን #ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ#ዋርስኖፋ እና አውሎጊስ ሰማዕታት#ቅዱስ መስቀል
▶︎

የሰኔ 10 ሥንክሳር#ቅድስት ቤተክርስቲያን #ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ#ዋርስኖፋ እና አውሎጊስ ሰማዕታት#ቅዱስ መስቀል

የማያዳግም መልስ // ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ? // ጥያቄና መልስ ክፍል 02
▶︎

የማያዳግም መልስ // ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ? // ጥያቄና መልስ ክፍል 02

ሰበር ዜና  ሀሙስ ሰኔ 18/2018 የሰአቱ መረጃዎች!|Ethiopian news today|Amhara fono|ethio news 25 June 2026
▶︎

ሰበር ዜና ሀሙስ ሰኔ 18/2018 የሰአቱ መረጃዎች!|Ethiopian news today|Amhara fono|ethio news 25 June 2026

200 DIOS TE DICE HOY: ESCUCHA ESTO ANTES DE DORMIR, MI VOZ TE DARÁ PAZ Y DESCANSO
▶︎

200 DIOS TE DICE HOY: ESCUCHA ESTO ANTES DE DORMIR, MI VOZ TE DARÁ PAZ Y DESCANSO

መጽሐፈ ሲራክ | Samuel Asres| ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Orthodox Tewahido | 12 January 2024
▶︎

መጽሐፈ ሲራክ | Samuel Asres| ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Orthodox Tewahido | 12 January 2024