ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
ይህንን ጸሎት ንስሐ የገባ ሰው ቢጸልየው በቀን አንድ ሺህ ሰው (1,000) ከሲኦል ያወጣል.... አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡ አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡ ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ! ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል። በዚህች ዕለትም የምንኩስናቸው በዓል ይከበራል፡፡ #duet #eotc #ethiopia #tewahedo #ethiopia #history #angel #habesha #love #greenscreen #orthodox

የሚያዚያ ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

የታኅሣሥ ድርሳነ ገብርኤል/Archangel Saint Gabriel

🔴 የሊቀ መልዓኩ የቅዱስ ገብርኤል ድርሳን | የሰኔ 19 ምስባክ- ወንጌል -ስንክሳር | Spiritual Narrative Video @ahadumedia21

ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

መዝሙረ ዳዊት ቅዳሜ - Mezmure Dawit Kidame 131-150

ተነሱ እንፀልይ | እግዚአብሔር ፀጋ መንፈስቅዱስ ያለብሰን ዘንድ የሚፀለይ የማታ ፀሎት | የኦርቶዶክስ ፀሎት Night prayer of Orthodox

ሙሉው ገድለ ጊዮርጊስ

ገድሊ ኣቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን Gedli Abune Filipos zedebre Bizen

ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት - The Birth of Saint Tekle Haymanot

የጥር ድርሳነ ዑራኤል- Archangel St Urael

የዓርብ ገድለ አቡነ ሃብተ ማርያም

የሚያዚያ ገድለ ሰማዕተ ኢየሱስ ቅዱስ ጊዮርጊስ - "The Martyrdom of Saint George" @mebba

ገብርኤል ሀያል📮 ድርሳነ ገብርኤል ⭕️ ሰኔ 19 ስንክሳር ገድል ⭕️ ድርሳን መልክአ ገብርኤል#gabriel#ethiopiaorthodoxtewahdochurch

የሰኔ ጎልጎታ

ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታሪክ Abune Gebre Menfes Kudus

🛑 ተወዳጅ የቅዱስ ገብርኤል መዝሙሮች ስብስብ //Ethiopian Orthodox St gebreal Mezmur #ጽዮን_ማርያም @Hosaenamedia

አጋንንት የሚያርቅ የማታ ጸሎት | የኦርቶዶክስ ፀሎት | Ethiopian Orthodox night prayer

የታኅሣሥ ገድለ ቅድስት አርሴማ

ቅዱስ _ ገብርኤል (( ድርሳን_ ተዓምር _ ወንጌል _ ፀሎት )) KIDUS _ GEBRIEL _ ገብርኤል

