የታኅሣሥ ድርሳነ ገብርኤል/Archangel Saint Gabriel
ታኅሣሥ 19-የራማውን ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነበት ታላቅ በዓል ነው፡፡ መልአከ ሞት መስከረም 19 ቀን መጥቶ "ጊዜ ዕረፍትህ ደርሷል" ቢላቸው "የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብር አይሆንም" ብለው መልአከ ሞትን ለ3 ወራት ከበራቸው ላይ ያቆሙት አቡነ ስነ ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ተንቤን ውስጥ የሚገኘውን አስደናቂውን የውቅን ገብርኤል ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ የሠሩት አቡነ ዳንኤል ዘተንቤን ዕረፍታቸው ነው፡፡ +ገና ሲወለዱ ከሰውነታቸው ህቡዕ የሆኑ የእግዚአብሔር የምሥጢር ስሞች በሰውነታቸው ላይ ይዘው (ተጽፎውባቸው) የተወለዱ አቡነ አባለ ክርስቶስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ዳግመኛም በዚህች ዕለት በሚቀድስበት ጊዜ ፊቱ እሳት ሆኖ ይታይ የነበረውና በጸሎቱ እሳት ከሰማይ አውርዶ ከሃዲያንን ያቃጥል የነበረው አቡነ ዮሐንስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ስነ ኢየሱስ፡- መልአከ ሞት መስከረም 19 ቀን መጥቶ "ጊዜ ዕረፍትህ ደርሷል" ቢላቸው "የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብር አይሆንም" ብለው መልአከ ሞትን ለ3 ወራት ከበራቸው ላይ ያቆሙት አቡነ ስነ ኢየሱስ በደመና ተጭነው በመዘዋወር በሀገራችን ወንጌልን ሰብከዋል፡፡ገዳማቸው ታች አርማጭሆ ከሳንጃ ከተማ በእግር የ3 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ጻድቁ ከሽዋ ምድር ተነሥተው ወደ ታች አርማጭሆ በመሄድ በበረሃ ውስጥ በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ በዚያም የሰማዕቱ የቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድን ገዳም ገድመዋል፡፡ አቡነ ስነ ኢየሱስ ብዙ መናንያን አርድእትን ያፈሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ አስገራሚ ተአምራትን በማድረግም ይታወቃሉ።የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብር አይሆንም ብለው መልአከ ሞትን ለ3 ወራት ከበራቸው ላይ ካቆሙትና በዓሉን ካከበሩ በኃላ በዚኽች ዕለት ታሕሳስ 19 ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን፡፡ + + #eotc #ethiopia #tewahedo #habesha #duet #love #greenscreen #onthisday #orthodox @mebba #stgabriel

শক্তিশালী রুকাইয়া আয়াত | জ্বীন-যাদু ও বদ নজর থেকে মুক্তির কুরআনের আয়াত | Powerful Ruqyah Verses

የቅዱስ ገብርኤል 🔵የተመረጡ✍️ መዝሙሮች ስብስብ 🔴[St. Gebriel Mezmur Collection🔴

የጥር ድርሳነ ዑራኤል- Archangel St Urael

የሰኞ ድርሳነ መድኃኔ ዓለም

የካቲት 12 የሚከበሩ ቅዱሳን የቅዱስ ሚካኤል በዓል የሚከበርበት አምስት ምክንያቶች የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን

🅾️ ድርሳነ ሚካኤል ድርሳነ ሩፋኤል ድርሳነ ገብርኤል ድርሳነ ራጉኤል ድርሳነ ሳቁኤል ድርሳነ አፍኒን የማኅበረ መላእክት ድርሳን @arone-vlog #eotc

ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት - The Birth of Saint Tekle Haymanot

ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

የሌሊት ፀሎት//Yelelit Teslot // Night time prayer #fastingprayer #christianprayer #breakthroughprayer

ቅዱስ ሚካኤል//"saint michael"

ድርሳነ ገብርኤል ዘወርሃ ሰኔ - Dirsane Gebriel Sene

ገብርኤል ሀያል📮 ድርሳነ ገብርኤል ⭕️ ሰኔ 19 ስንክሳር ገድል ⭕️ ድርሳን መልክአ ገብርኤል#gabriel#ethiopiaorthodoxtewahdochurch

🔥 ከመኝታ በፊት በዚህ ወር ይህንን ፀልዩ | የተወሰደባችሁን በረከት አሁኑነ አስመልሱ Midnight praying #ebstv #habesha

Built To Last - Dr. Corey L. Brown

የሚያዚያ ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

የመጋቢት ድርሳነ መስቀል

📕ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ✝️ ሰኔ 19📖 ገድል#ድርሳን#ስንክሳር kidus gebreal @zikr_mediaዝክር ሚዲያ#eotc

መልክአ ገብርኤል - Melka Gebriel

#ሰኔ ቅዱስ ሚካኤል (Saint Mikael ) @mikreabewmedia

