የቱ ነው እውነቱ (ሕያው ክታብ)-Ethio-Jazz x Vintage Rocksteady & Dub Reggae Fusion|Lyrics Video | ELT153 Music
🚀 አዲስና ለየት ያለ የሙዚቃ ውህደት (A Groundbreaking Avant-Garde Fusion) ይህ ስራ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ ከዚህ በፊት ተሞክሮ የማይታወቅ ሙሉ በሙሉ አዲስ እና ልዩ የሙዚቃ ስልት ውህደት (Experimental Fusion) ነው። የ1960ዎቹን አንጋፋ የጃማይካ ሮክስቴዲ (Vintage Rocksteady) እና የከበደውን የደብ ረጌ (Heavy Dub Reggae) የጀርባ ምት፣ ከሀገራችን የኢትዮ-ጃዝ (Ethio-Jazz) ረቂቅ ቅኝት ጋር ያዋሃደ ነው። በምዕራባውያኑ የነሀስ መሳርያዎች (Horns) እና በሀገራችን ባህላዊ መሳርያዎች (የማሲንቆ እና የዋሽንት ጥልቅ ዜማ) መካከል የተፈጠረው አስደናቂ መጣጣም፣ የፈጠረውን ከዚህ በፊት ያልተሰማ አዲስና የተለየ መንፈሳዊ ድባብ ያለው ሙዚቃ ለምትወዱ የሙዚቃ አፍቃሪያን የተዘጋጀ ድንቅ የፈጠራ ስራ! እነሆኝ! 📜 Song Meaning & Analysis ይህ ዘፈን የነፍስን የማንነት ፍለጋ ጉዞ ይተርካል ሰውየው ለአለም ችግር መፍትሄ ፍለጋ በቤተ-ሙከራና በንባብ ቢባዝንም፣ በመጨረሻ ግን የዓለም ህመም ምንጭ ራሱ መሆኑን ይረዳል ("እኔ ነበርኩ እኔ የዓለም ህመም የኔ ችግር" የሚለው ስንኝ የሰው ልጅ ውድቀትና የራስን ማንነት የመመርመር ጥሪ ነው)። ፍጹም እውነትንና መለኪያን ፍለጋ ወደ ጥንታዊ እውቀትና ባህል ይገባል ("የባህሪ ሰቤን ክታብ ገለጥኩ"።) ነገር ግን በምድረበዳው ውስጥ የሚሰማው ድምጽ "ተወው የለም" ቢለውም፣ በውስጡ ያለው የእውነት ጥማት ግን መፈለጉን እንዲቀጥል ያደርገዋል። "ሰማይ ሊያልም በምድር የተኛ፣ ሀገሩን ናፋቂ መጽአተኛ" የሚለው ስንኝ የሰው ልጅ በምድር ላይ ያለውን እንግድነትና ሰማያዊ ናፍቆት ያሳያል። በመጨረሻም ፍለጋው በከንቱ አይቀርም። በጽዮን ተራራ ላይ የነፍሱን ሙሽራና እውነተኛውን መድሃኒት ያገኛል። እውነተኛው "ሕያው ክታብ" (የህይወት መጽሐፍ / ቃል) በፍለጋው አብሮት እንደነበር እና ከፍሬ እንዲደርስ እንዳደረገው በድል አድራጊነትና በምስጋና ይደመድማል። 🎵 የሙዚቃው ስልትና ውህደት (Musical Style) Ethio-Jazz:Minor-key modal chord progressions & 1960s Rocksteady and Heavy Dub Reggae 🎤 የግጥም ግልባጭ (Lyrics) ኧረ የቱ የቱ ( የቱ) የቱ ነው እውነቱ (የቱ) ኧረ የቱ የቱ(የቱ) ኧረ የቱ የቱ ላለም ችግር እኔ መፍትሄ ፍለጋ ፣ ስውተረተር ነበር ሰው ልሆን ስተጋ ። ችግሩን ከስሩ እንድለየው ብዬ ፣ ቤተ ሙከራና መስክ ሆነ ኑሮዬ። እዚና እዛ ስል ፣ ሳነሳና ስጥል ስመረምር ፣ ዉዬ አድሬ ገባኝ ፣ ያለም ህመም ፣ የኔ ችግር ፣ እኔ ነበር እኔ እኔ፣ ያለም ህመም ፣ የኔ ችግር .... ያለም ህመም ቢለይም ፣ ባለመድሃኒቱ በዝቶ፣ እውነቱን ከሃሰት መለየት ፣ቸገረ መለኪያ ጠፍቶ። ኧረ የቱ የቱ ( የቱ ) የቱ ነው እውነቱ (የቱ) ኧረ የቱ የቱ (የቱ) ኧረ የቱ የቱ መለኪያዉን እውቀት ልፈልግ ብዬ ዘልደቴን ልቃኝ ገባሁ ደጁን ጥዬ የታማሚ ነፍሴን ፈውስ እየናፈቅኩ የባህሪ ሰቤን ክታብ ገለጥኩ (ሕያው ቃል ያለኝን አወረድኩ አወጣሁ መለኪያዉን ይዤ ሲሄድ ላየው ወጣሁ የደጁን እየዞርኩ በመለኪያው ለካዉ እንደኔ ያመመው የኔ ቢጤ ነው ያው ። ) ይብቃህ ! በቃ ! የለም አትፈልገው ተወው ! ተወው! ይላል ምድረ በዳው የባህርይኮ ነው! አረ እንዴት ልተወው የሰማሁት ድምጽስ ሚታመን እዉነት ነው ኧረ የቱ የቱ ? (እሱ ሕያው ክታብ ) እሱ ሕያው ክታብ (የቱ ነው እውነቱ) የሆነዉ ካብ እስካብ (እሱ ሕያው ክታብ ) እሱ ሕያው ክታብ (እሱ ግን የቱ ) (እሱ ሕያው ክታብ) እሱ ሕያው ክታብ (እሱ ግን የቱ) የሆነዉ ካብ እስካብ (እሱ ሕያው ክታብ ) ( እሱ ግን የቱ ) ሰማይ ሊያልም በምድር የተኛ ሀገሩን ናፋቂ መጽአተኛ ግድ የለም ! ግድ የለም ይበሉ እፈልገዋለሁ ዘመኔን በሙሉ ግድ የለም ! ግድ የለም እስካየው ልኑር ስፈልገው ልኑር ስጠብቀው ወናፍ ጊዜ ነፍቶኝ በመከራ እንኳ ብነድ ማሰሴን አልተዉም እስከ ትቢያና አመድ ። ............. መድሃኒት ፍለጋ ፣መች ባዝኜ ቀረሁ ? በጽዮን ተራራ ፣ ሙሽራዬን አየሁ ። ባይኖር እሱ አብሮኝ ፣ ማን ነፃ አወጣኝ ? ማን መንገዱን መራኝ ፣ ማን ወንዝ አሻገረኝ ? በቅጠሏ እየፈወሰኝ ፣ እሱ ነው ከፍሬ ያደረሰኝ .. (እኮ ማን...? ) እሱ መድሃኒቱ (ሕያው ክታብ) አብሮኝ ነበር ሲጽፍ "እኔ" ን ካብ እስካብ አብሮኝ ነበር ሲጻፍ እኔን ሆኖ ደርዝ ክታብ (እሱ ግን የቱ) ኧረ የቱ የቱ? (እሱ ሕያው ክታብ ) እሱ ሕያው ክታብ (እሱ ግን የቱ) የሆነዉ ካብ እስካብ (እሱ ሕያው ክታብ ) ( እሱ ግን የቱ) {እሱ ሕያው ክታብ) ( እሱ ግን የቱ ) {እሱ ሕያው ክታብ) ( የቱ ነው የቱ) (ሰማይ ሊያልም በምድር የተኛ) (ሀገሩን ናፋቂ መጽአተኛ ) ግድ የለም ! ግድ የለም ይበሉ እፈልገዋለሁ ዘመኔን በሙሉ... ግድ የለም ! ግድ የለም እስካየው ልኑር ስፈልገው ልኑር ስጠብቀው 🎧 Credits Lyrics & Concept: Ermias Lishan T. Vocal Delivery: Gravelly Baritone Male Lead Music Production & Arrangement: ELT153 (Suno AI Assisted) (Ethio-Jazz, Rocksteady, & Dub Fusion) 🎵 Share & Credit Guidelines: You are welcome to share this video! However, if you use this audio or lyrics in your own content: You must credit the original creator (Ermias Lishan T. | ELT153 Music) . You must provide a link back to this official YouTube video. No monetization or commercial use of this track is allowed without official written consent. © 2026 ELT153 Music|Ermias Lishan T. All rights reserved. #EthioJazz #RocksteadyReggae #EthiopianMusic #YetuNewEwnetu #HiyawKitab #DubReggae #Masinqo #Washint #SpiritualReggae

Chiroye (ጭሮዬ ) 🎵

እውቀት የህይወት ጥላ | The Shadow of Being |Ethiopian Rocksteady (Official Audio) Ermias Lishan| ELT153

አንጃ — ጉድ (Anja - Gud) | Amharic Dancehall Riddim & Dubplate Vibe |Ermias Lishan T.| ELT153

ጎንደር ተጠናቋል || የብልጽግና ፍጻሜ ፊሽካው ተነፋ || አስቸኳይ ስብሰባ ተደረገ || "ኤርትራም ጦር አለበት" ብልጽግና

Authentic Tigrinya Instrumental Music V-11

የቫስኮ ዳ ጋማ ሙሉ ታሪክ | The Entire History Of Vasco Da Gama

Your Music Videos AREN'T Getting Recommended? Do THIS Immediately

በዚህ ቪዲዮ ካልሳቁ ሽልማት አለዎት! | Meskerem Kebede #marakiweg #lifestyle

Summer Afternoon – 1 Hour Persian Jazz Fusion | عصر تابستان

Sona Jobarteh - Jarabi

ረስታ (Nebula of Love) | Roots Reggae - Dub Style | Ermias Lishan | ELT153

ምነው ባየሁ (Minew Bayehu) | Ethio - Roots Reggae & Rocksteady fusion | Ermias Lishan | ELT153-Music

01 Aster Aweke Gela Gela

የእኛ ምርጥ ትዝታዎች 🎶 Best 90s Ethiopian Instrumental Oldies | Vol. 58

Ethiopian Non Stop Remix (1 Hour) ft. Teddy Afro, Hachalu Hundessa & More | By Samy Beatz

ወይ ነዶ! (Wey Nedo) | Ethio - Rocksteady & Reggae Fusion|Washint Melody| Ermias Lishan | ELT153 Music

1 Hour Persian Jazz – “Gole Sangam” (گل سنگم) | Lo-Fi Jazz - We Are Jazz

መማለም (Mummified World) | Ethiopian Rocksteady | Ermias Lishan | ELT153 Music|2026

Legend Reggae Songs That Live| Bob Marley, Jimmy Cliff & More|Golden Era Reggae(inspired & AI Cover)

