Jemal Wello about Haile Kasse_December 21, 2024
ሀይሌ ካሴ (ኳሴ)! በ Jemal ወሎ ሙሉ ህይወቱን ለኳስ የሰጠ፣ ስለ ኳስ የኖረ፣ ስለ ኳስ ሲያወራ ውሎ ኳስን ሲያስባት ያደረ፣ እጅግ ሲበዛ ጥበበኛ! የኳስ ፍቅረኛ! የኳስ ምርኮኛ፣ የሰፈር አምባሳደር የኳስ ሜዳ አድባር! ልጅ አዋቂ ያወደሰው፣ በፍቅር አክብሮ ያነገሰው፣ ባለቅን ልቡ የሰብዕዊነት ጥጉ ሀይሌ ኳሴ! ኳስ ና ሀይሌ አይለያዩም ኳስ ሜዳ ና ሀይሌም አይነጣጠሉም፣ ኳስ ሜዳን ቀን ይውልባታል ሌቱን ያልማታል፣ ራሱ ይጫወትባታል አዳጊ ተጫዋች ይመለምልባታል፣ አስሠልጣኞች 15 ቀን የሚያጠኑትን ተጫዋች ሀይሌ በ 15 ደቂቃ ውስጥ እርግጠኛ በሆነ መልኩ የተጫዋቹን የወደፊት ዕጣ ዛሬ ይተነብያል፣ ሀይሌ አይቶ ያነገሰው ይነግሳል የጣለው የተጫዋችነት ዘመኑ ያጥራል። ለበርካታ የአካባቢው ተጫዋቾች ስኬት የሀይሌ ሚና ቁልፍ ነው ድጋፉም ወሳኝ ነው። የኳስ ሜዳ ልጅ መሆን የሀይሌ ሰፈር ልጅ መባል ወደ ቀጣዩ ዙር የተጫዋች ምርጫ ለማለፍ ቪዛ ነው፣ ዕድሜ ለካሤ ገሠሠ ልጅ እንደ "BMW " እንደ "PUMA" ኳስ ሜዳነት ብራንድ ነው። የሀይሌን አይን የሳበ በ ራዳሩ ስር የወደቀ የሰፈር ልጅ ድጋፍ ና ብርታቱ ተለግሶት ክለብ ማግኘቱ የስኬት ማማንን መርገጡ እርግጥ ነው፣ ለዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስጠሩ ኢትዮጵያ ቡናን ያኮሩ በሌሎች ክለቦችም የነገሱ የበርካታ የሰፈራችን ኮኮቦች ታሪክ ህያው ምስክር ነው። ከሰፈር ወጥቶ የሀገራችን ብቻ ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካ ኮከብ የነበረው የምንግዜውም የምርጦች ምርጥ፣ ሰለሞን ቸርኬም የዚሁ ታሪክ አንዱ አካል ነው!!! ሀይሌ, ኳስ ሜዳን የሚያጣት ይመስል ማልዶ ሜዳ ይመጣል፣ መሽቶ አይን ሲይዝ ይመለሳል፣ ይመሻል ይነጋል! ሰኞ ብሎም እሁድ ይደርሳል ሀይሌ ግን ሁሌም እዛው ነው። በአንድ የበዐል ቀን አቶ ካሴ ገሠሠ ማልደው ይነሳሉ የበግ እግር የሚይዝ ልጅ ሊጠሩም ወደ መኝታ ቤት ጎራ ይላሉ ሀይሌ ወንዶቹን ሁሉ ጠራርጎ ሜዳ ወጥቷል፣ ቤቱ ባዶ ነው አቶ ካሴም ተበሳጭተው መለስ ሲሉ የፔሌ ፎቶ በትልቁ ተለጥፎ ያያሉ ትኩር ብለው ካዩትም ቡሀላ ፈገግ ይላሉ፣ ልጃቸውን የተጠናወተው ሰይጣን ተገኘ! አንት ዲያብሎስ በአመት በዕል እንኳን አንድ ልጅ አታስቀርልኝም? እያሉ እየዛቱ ወጡ ወዲያውኑም አንድ አባት ተጠርተው መጡ፣ መኝታ ቤቱም የፔሌም ምስል ፀበል ተረጨ፣ በማግስቱ ግን ሀይሌ ወንድሞቹን ሰብስቦ ሌላውን የመንደር ልጅ ትሬይኒንግ ሊቀሰቅስ ማልዶ ወጣ! ሀይሌ አስቦና አይቶ ቅፅል ስም ያወጣል፣ አለቀ! ወላጅ ያወጣው ስም ይረሳል ስሙም ንቅሳት ሆኖ ይቀራል! ሰፈር፣ ትምህርት ቤት፣ መስሪያ ቤት ዋና መጠሪያ ይሆናል ባህር ማዶም ስደት ይሻገራል! የላ፣ ቸርኬ፣ ወሎ፣ አስፕሬላ፣ ጌሪ፣ ችኳንታ፣ ሊብሮ፣ ፋዲጋ፣ ጆሮ፣ ሪጅስ፣ ጂረስ __እያለ እያለ እያለ ይቀጥላል!!! የሀይሌ ኳሴ የህይወት ጉዞ የሚያጠነጥነው በኳስ ና በኳስ ዙሪያ ብቻ ቢመስልም ሀይሌ የብስክሌት ና የዋና ችሎታው ጥግ የደረሰ የፉጨት ተስጥኦው ጣራ የነካ አዕዋፋትን ሚያስደምም የሰውን ልጅ ሚያስገርም ነው። በአቧራማው የኳስ ሜዳ መሬት ላይ ሀይሌ ፊቱን አዙሮ ዘጋንባ ብስክሌቱን የኋሊት ሲጋልበው ማየት ድንቅ ነው፣ ተስተካክሎ ተቀምጦ ወደ ፊት እየሄደ ሙሉ በሙሉ ወደ ቀኙ አዘንብሎ መሪ የጨበጠበት እጁን አቧራ አስነክቶ ወደቀ ሲባል ሲመለስ መታዘብ ግን ተዕምር ነው። በአንድ አጋጣሚ ሀይሌ ሲዋኝ ለማየት እኛም ለመዋኘት ግዮን ተገኘን፣ ሀይሌ እንደመጣ ቀያይሮ ሻወር ገባ፣ በወቅቱ ለ All African Games ዝግጅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዋናተኞች ቡድን ለልምምድ እዛው ነበሩ፣ ሀይሌም ከአሰልጣኙ ጋ ይተዋወቁ ኖሮ አንድ ሁለት ተባባሉና ሀይሌ ወደ መወርወሪያ ማማው አመራ ትንሽም ትልቁም ገንዳ ውስጥ ያለ ሁሉ ትኩረቱ ወደ መወርወሪያው ሆነ! ሀይሌም ፈገግ ብሎ ህዝቡን ካየ ቡሀላ ከ 7ሜትር ከፍታ ላይ እየተገለባበጠ ወደ ገንዳው ገባ እዚህ የተወረወረው ሀይሌ ውስጥ ለውስጥ ሄዶ እዛኛው ጫፍ ብቅ ሲል የብሄራዊ ቡድን ዋናተኞችን ጨምሮ የህዝቡ ፉጨት ና ጩኸት ጎል የገባ መሰለ። እስከ ጉልበት በምታሰመጠው ትንሿ ገንዳ ለመዋኘት የሄድነው የሰፈር ልጆች የስሙኒ ፌስታላችንን እንደያዝን ፈጠን ቀረን። ሀይሌን የተጠናወተው ዲያብሎስ ዛሬም አብሮት አለ፣ ስደት ተከትሎትም ሄዷል የኳስ ፍቅር ያናዝዝዋል፣ የኳስ ሜዳ ፍቅርም ያስለፈልፈዋል!!! ረጅም ዕድሜ ለ ሀይሌ ኳሴ!!! ⚽ መርካቶ ስፖርት ⚽ 💚💚💛💛❤️❤️

ESFNA 2024 Seattle Teams

Haile Kasse (ኳሴ) former Ethiopian footballer

From Ethiopia to England: Amen's Football Dream Comes True! @dylan.page. Thank you ❤️

Hulet Kitat "ሁለት ቅጣት" | ሙሉ ፊልም | New ethiopian movie 2025#melonacinema

ሓድሽ ዜና ጀርመን - ካብ ዕለት 1 Juli ዝጅምር ሕጊ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ የሀያልነቱ ታሪክ , (St. gorge) Ethiopia's most successful and historic football club.

ሰበር🔥ኣዛዚ TDF ስልጣን ለቒቑ/ኣሜሪካ ንህወሓት ማዕቀብ ኣንቢራ/ንኣብይ ድማ ከቢድ ፅፍዒት

ጽጹይ ሓበሬታ/ ጥዑም ደሃይ ሓውና ተረኪቡ/ ኣቦ ውላዳ ረኪባቶ/ መርፍእ ንህጻን ዝውጋእ/ ኣጸያፊ ቪድዮ ባእሲ

Mesob with wazi . my guest is @teddyafro yezefenelet former soccer player Haile kassye

''የቅዱስ ጊዮርጊስን ደጋፊ ማየት ናፍቆኛል… ''/ የፈረሰኞቹ ንጉስ ሙሉጌታ ከበደ''

ESFNA በኢትዮጵያውያን ዕይታ ምን ይመስላል።

ባላገሩ የጥበብ ሰው፣ ሰኔ 09, 2018 What's New June 16, 2026

የቀድሞ ተጫዋች ታምራት አበበ (ሎቲ) የእግርኳስ ህይወት ታሪክ_06202025

ማዘን አዲስ ፊልም [ MAZEN New Ethiopia Amharic film 2017

Jun-18 ቅልውላው መሊሱ ገደደ I ጉድ ጃንዳ PP I ጉዳይ ሱዳን ትግራይ ፋኖ I Abiy Lost Trump & Eritrea to Egypt I Iran MoU

1993 U20 World Cup: Ghana 2–1 England – Classic Semi-Final

በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ሀይሌ ካሴ (ኳሴ) የኳስ ሜዳ አብሮ አደጎቹ፣ የጎፈሬ የስፖርት ትጥቅ አምባሳደር በመሆኑ የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት አስተላለፉ።

sport America

Women's 10,000m Final - London 2012 Olympics

