በምርምር የተገኙ የሰብል ዝርያዎችን በሰርቶ ማሳያ ማስተዋወቅና ወደ ምርት ማስገባት ለግብርና ምርታማነትን ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ
ባህርዳር፣ ሰኔ 9፣ 2018 ዓ/ም ( ግብርና ቢሮ ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በምርምር የተገኙ የሰብል ዝርያዎችን በሰርቶ ማሳያ ለማስተዋወቅ ይቻል ዘንድ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰማኝ አስረዴ የምርምር ተቋሙ ቴክኖሎጂን ማፍለቅና ማላመድ፣ ማስተዋወቅ እንዲሁም የመነሻ ዘር ብዜት ማካሄድ ዓለማ አድርጎ እንደሚሰራ ጠቅሰው በክልሉ ከ188 በላይ ዝርያዎች መኖራቸውን ገልፀዋል። እነዚህን ዝርያዎች ማስተዋወቅ ከተቻለ በምርታማነት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተናግረዋል። ወደ ሰርቶ ማሳያ የሚገቡ ዝርያዎችን ለይተን ወደ ተጨባጭ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ያሉት ዶ/ር ሰማኝ አስረዴ የባለሙያዎች ቁርጠኝነት ወሳኝ ስለመሆኑ አንስተዋል። አዳዲስ ዝርያዎችን በሰርቶ ማሳያ ማስተዋወቅና ወደ ምርት ማስገባት የግብርና ምርትማነትን ያሳድጋል ሲሉ የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንደ ምርምር ተቋም የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ብለዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የኤክስቴንሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀኝአዝማች መስፍን በበኩላቸው የግብርና ዘርፉን ከልማዳዊ አሰራር ወደ ዘመናዊ አሰራር ለማሸጋገር ሰርቶ ማሳያ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀው አርሶ አደሩ በተግባር አይቶ የሚማርበት መሆኑንም አንስተዋል። የምርምር ተቋሙ፣ ምርጥ ዘር አባዥ ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች በጋራ ተቀናጅተው አማራጭ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ማቅረብ እንዳለባቸው ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ከምርታማነት፣ ከገበያ ተፈላጊነት፣ በሽታንና ድርቅን ከመቋቋም እንዲሁም ለስርዓተ ምግብ ካለው ፋይዳ አንፃር አማራጭ ዝርያዎች በስፋት ለማቅረብ ያሉ አቅሞችን አሟጦ መጠቀም ይገባል ብለዋል። አቶ ቀኝአዝማች መስፍን አክለውም ተቀናጅተን ስንሰራ ችግሮች ይፈታሉ፣ ውጤት እናስመዘግባለን፣ ቅንጅታዊ አሰራርም ይጎለብታል ሲሉ ተናግረዋል። በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የአየር ንብረት የሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ( CREW ) ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አግደው ሞላ ለመወያያ የሚሆን መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በሌሎች አቅራቢዎችም የውይይት መነሻ ፅሁፍ በማቅረብ ገንቢ ውይይት ተደርጓል። በስልጠናና ምክክር መድረኩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ የግብርና ባለሙያዎች፣ የምርምር፣ የዘር አባዥ ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች ተሳታፊ ሆነዋል። ዘጋቢ:- አንተነህ ሰውአገኝ ድምፅ ምስል ቅንብር ኤዲተር : ጌታቸው ታፈረ

በልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ሁሉንተናዊ ድጋፍ ስለተደረገልን ጥሪትና ሀብት እያፈራን ከተረጅነት እየወጣን ነው - የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች

ዓመቱን በሙሉ ምርት የሚሰጡ አትክልትና ፍራፍሬዎች

የተቀናጀ ግብርና

መስኖ ለወጣቶች - ወደ ገጠር |ወደ ገጠር| ETV |EBC |ETHIOPIAN

የመስኖ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ እርብርብ እየተደረገ ይገኛል

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ( DRDIP-ll ) በመተማ ወረዳ የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሂዷል

ግንዛቤ ለመፍጠር እና ለመጠቀም ሰርቶ ማሳያዎች ሚናቸው የጎላ ነው ተባለ።

የማይቋረጥ ገቢ

ውሀ ፣መሬት እና ወጣቶችን ያገናኘው የበጋ መስኖ በቸሀ ወረዳ | ወደገጠር |EBC | EBCDOTSTREAM

ችግኝ ተክለው የከበሩት ግለሰብ

ፀጋን ወደ ተጨባጭ ልማት የማዋል ጅምሩ የሰመረው የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን

"ኢራን ስትወጋን አልደረሳችሁልንም" ትራምፕ | የኔቲና አሜሪካ መጨረሻ ! _NBC የቀን ዜና @NBCETHIOPIA

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሥርዓተ-ምግብና የግብርና ሥርዓተ-ምግብ ፎረም የምክክር መድረክ አካሄደ

Ethiopia - ወደ ኢትዮጵያ የተጠጋው ከባድ ጦር ከጀርባው ያለው ሴራ ሲገለጥ

How Toilet Bowls Are Made | Amazing Toilet Bowl Manufacturing Process in Pakistan

ግብርና በእውቀትና በሲስተም መመራት አለበት "ቀኝአዝማች መስፍን"

"ዘላቂ ምርታማነትን ለማሳደግ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሁነኛ መፍትሔ ነው" ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ

Schottland – Brasilien Highlights | Gruppe C, FIFA WM 2026 | sportstudio

ግብፅ በደቡብ ሱዳን ተዋረደች ተረክ ሚዛን Salon Terek

