ዶንኪ ትዩብን ለማዳን ግዜው አሁን ነዉ!! ከጎናችን ናችሁ? #savedonkeytube #livestream #donkeytube #eshetumelese
ዶንኪ ቲዩብ ትልቅ የህልውና አደጋ ላይ ነው! 31 ሰራተኞችን ላለማሰናበትና የጀመርናቸውን በጎ ስራዎች ለመቀጠል የእናንተ ድጋፍ ዛሬውኑ ያስፈልገናል። 'Join' በማለት ወይም አባል በመሆን ሚዲያችንን ከውድቀት ይታደጉ። አብረን እናድን! Join / @donkeytube.eshetumelese በወገን ፈንድ ለመደገፍ https://www.wegenfund.com/causes/donk... #uk #usa #dalasreview #texas #washington #lasvegas #merryland #seatle #california #losangeles #canada #germany #australia ዶንኪ ትዩብን ለማዳን ግዜው አሁን ነዉ!! ከጎናችን ናችሁ? #livestream #donkeytube #eshetumelese ውድና የተከበራችሁ የዶንኪ ትዩብ ቤተሰቦች እንዲሁም በዓለም ዙሪያ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ ላለፉት 7 ዓመታት ዶንኪ ትዩብ (Donkey Tube) በኢትዮጵያ ሚዲያ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ በመክፈት፣ ከሰበር ወሬዎችና ከማህበራዊ ሚዲያ ውዝግቦች ይልቅ ሰብአዊነትን፣ አንድነትንና በጎነትን አስቀድሞ ሲያገለግል ቆይቷል። በእግዚአብሔር ቸርነትና በእናንተ ታማኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የለወጡ ታላላቅ ሥራዎችን አብረን ሠርተናል፦ ድልድይ በመሆን ቀጥተኛ እርዳታ ማገናኘት፦ ድሮ ይደረግ የነበረውን የአሰራር ልምድ በመቀየር፣ ተረጂዎችን ቀጥታ ከረዳቶቻቸው ጋር በባንክ አካውንታቸው በማገናኘት በርካታ ሰዎችን ከሞትና ከታላቅ ችግር አትርፈናል። ታላላቅ የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች፦ የአቡነ አሮን የውኃ ፕሮጀክትን፣ የወለተ ጴጥሮስ ገዳም ትራክተር ግዢን፣ የይምርሃነ ክርስቶስንና የኳታር ሥላሴን እንዲሁም የለንደንን ቤተክርስቲያን ድጋፎች በታማኝነት አስፈጽመናል። ተስፋ የቆረጡትን ማገገም፦ በከባድ የሱስ ሕይወት ውስጥ የነበሩ ወጣቶችን መልሰን እንዲቋቋሙ፣ የአእምሮ ሕመም ታማሚዎችንና ለዓመታት ተስፋ ተቆርጦባቸው የነበሩ ባለታሪኮችን እንዲፈወሱ መንገድ ሆነናል። አሁን ግን ዶንኪ ትዩብ ታይቶ በማይታወቅ ታላቅ የኢኮኖሚ አደጋ ውስጥ ይገኛል። ላለፉት 3 ዓመታት ከጀርባ በሚደረጉ የኢኮኖሚ ተፅዕኖዎች፣ የተፈራረምናቸው ስፖንሰርሺፖች እንዲሰረዙ በመደረጉ እና የሠራናቸውን ቪዲዮዎች ያለፈቃድ ቲክቶክ ላይ በመጫን የዩቲዩብ ገቢያችን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲወርድ ስለተደረገ፣ ተቋሙን መምራት ወደማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። እስካሁን ወጪዎቻችንን ለመቀነስ ብዙ ብንታገልም፣ አሁን ግን የኪራይ፣ የኢንተርኔት፣ የስራ ግብርና የሠራተኞቻችንን ደሞዝ መሸፈን አቅቶናል። ይህ ማለት 101 ሠራተኞቻችንን መበተን፣ የቻናሉን ሥራዎች ማቆም እና በዳታቤዛችን ላይ የተመዘገቡ እርዳታ የሚጠብቁ ከ1,200 በላይ ግለሰቦችን፣ እናቶችንና አብያተ ክርስቲያናትን ተስፋ ማጨለም ይሆናል። እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? እግዚአብሔር በናንተ ልብ አድሮ ዶንኪ ትዩብን ከመዘጋት እንድትታደጉት ጥሪያችንን እናቀርባለን። በዚህ የወገን ፈንድ ዘመቻ የሚሰበሰበው እያንዳንዱ ሳንቲም ቀጥታ የሚውለው፦ ዶንኪ ትዩብን ከባድ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ የጣሉትን የቤት ኪራዮች፣ የሠራተኛ ደሞዝና የግብር ወጪዎችን ለመሸፈን። የቪዲዮዎቻችንን ጥራት ጠብቀን፣ 20 እና 30 ቀናት የሚወስዱ ሰብአዊነት ላይ ያተኮሩ ታላላቅ ሥራዎችን በነፃነት ማምረት እንድንቀጥል። በእርዳታ ወረፋ ላይ ያሉትን ታማሚዎች፣ አቅመ ደካሞችና አብያተ ክርስቲያናትን ለመደገፍ። ፣ እውነታውን ተረድታችሁ ከረፈደ በኋላ ከምንቆጭ ዛሬውኑ ከጎናችን እንድትቆሙ እንማጸናለን። እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን፤ በጎ ሥራችንም ፈጽሞ አይቁም! ✅Follow and Subscribe : Tiktok : / comedian_eshetumelese Donkey Kids : @donkeytubekids Instagram : / comedian.eshetu Facebook : / eshe.melesse Contact us [email protected] 📌የኤዲቲንግ ስልጠና ለመውሰድ +25975516360 ይደውሉ! #donkeytube #comedianeshetu #dinqlijoch #dinklijoch #ethiopia #habesha

እየደረሰብኝ ያለው ጥቃት የምታዩት ብቻ አይደለም !#comedianeshetu #donkeytube #dinklijoch #ethiopia

መስኪ በድጋሜ በሳቅ ገደለችን! | የዛሬው ደግሞ ይለያል! | Meskerem Kebede #marakiweg #lifestyle

ቅድስት አርሴማን ተማፅኛት ልጄን ሙሉ ለሙሉ አዳነችልኝ. #comedianeshetu #ethiopia #dinklijoch #donkeyyoutube

Anchor Media ብሔራዊ ምክክር ወይስ ብሔራዊ ስላቅ? በጎጃም ደጋ ዳሞት ሰሞኑን ምን ሆነ? የአብይ አህመድ ስጋትና ህወሀት፥ የተጋሩ ሰልፍ በአዲስ አበባ

Deep Inside Africa's Most Brutal & Secretive Dictatorship 🇪🇷

He attacks viewers live and harasses women I Rezo reacts

Ethiopia እለተ አርብ ሐምሌ 10/2018 ሰበር መረጃዎች #AnchorMedia #EthiopiaNews #AnchorFanoNews #Fano #ethionation

ዶንኪ ትዩብን ለማዳን ግዜው አሁን ነዉ!! ከጎናችን ናችሁ? #savedonkeytube #livestream #donkeytube #eshetumelese

🛑 NEW || ደመናው አይቀደድም || እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ | Aba Gebrekidan New Sibket 2024

መኪና ምረጥ አለኝ !ዋና ያለው ቤት ተከራየልኝ! የዮሐንስዋ ማርያም ናት ያተረፈችኝ#comedianeshetu #donkeyyoutube #ethiopia #dubai

ፖሊስ መግለጫ ሰጥቷል || ህውሃት ሌላ ማሰፈራሪያ አወጣ || መስቀል አደባባይ ይጠለቀለቃል Live

የፈለገ ዋጋ ብከፍልባትም በመለያየታችን ደስተኛ ነኝ!! #comedianeshetu #donkeyyoutube #yalfal #lovestory #relationship

🔴ሰኞ ሰኞ ለምን ይከብደናል ሚስጢሩ ይህ ነው❓❓ ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው likelikawnt simur alamrew @tsenatslmedia

Answer to Harvesting Giant River Fish is Handmade Traps | Fishing with Chuc Duong and Her Children

Vintage Easter Bunny Garden | Spring Frame TV Art Screensaver with Gold Frame | Easter Frame Art 4K

Ethiopian news ሰበር እርምጃ ተጀመረ የሀምሌ 10 2018 የዕለቱ ዜናዎች

سورة الواقعة ( كاملة ) ❤️ للرزق و البركة في البيت😴 | تلاوة هادئة بصوت مريح | القارئ بلال دربالي قرآن

🔴Live Adoration of the Blessed Sacrament / Adoración al Santísimo en vivo

የዋልድባው ቪድዮ ድራማ ወይስ እውነታ!! ለአባቶች ክብር እውነቱን ልናገር! #comedianeshetu #ethiopia #waldba #egregnaw

