የእርግዝና ሁለተኛው ሳምንት ምልክቶች | The sign of two week pregnancy

ሁለተኛው ሳምንት ማለት ፅንስ ገና የሚፈጠርበት ሳምንት ነው ማለት ነው። ለማርገዝ እየሞከራችሁ ከሆነ, ለቀጣዩ ጉዞ መዘጋጀት መጀመር ይኖርባችኋል። ይህም የቅድመ ወሊድ ቫይታሚን መውሰድ መጀመር ፣ አልኮል እና ትምባሆ ማቆም እና አንዳንድ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤያችሁን ማስተካከል ይኖርባችኋል። አሁን ላይ የ 2 ሳምንታት ነፍሰ ጡር ነኝ ብላችሁ እያሰባችሁ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ላትሆኑ ትችላላችሁ ። ምክንያቱም እርግዝናችሁ መቆጠር የሚጀምረው ከመጨረሻው የወር አበባችሁ የመጣበት ቀን ጀምሮ ነው። ዶክተራችሁ የእርግዝና ርዝማኔያችሁን እና የምትወልዱበትን ቀን የሚነግራችሁ ከዚህ ቀን ጀምሮ ቆጥሮ ነው። ስለዚህ ከሁለት ሳምንት በፊት ከፀነሳችሁ አሁን ላይ የአራት ሳምንታት ወይም አምስት ሳምንት እርጉዝ ናችሁ ማለት ነው። በአጠቃላይ ምን ለማለት ነው ኦቭዩሌት የምታደርጉበት ቀን እና ሳምንት አንዱ የእርግዝናችሁ አካል ነው ማለት ነው። 📌 ህፃኑ በ 2 ኛ ሳምንት ምን ይመስላል ? በ 2 ሳምንት እርግዝና ውስጥ ምን ይከሰታል ? በዚህ ሳምንት ውስጥ የወር አበባችሁን ጨርሳችኋል። እና ምናልባትም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ውፀት ታደርጋላችሁ ወይም ኦቭዩሌት ታደርጋላችሁ። ስለዚህ በ 2 ሳምንት እርግዝና ወቅት ውስጥ እርጉዝ አይደላችሁም ማለት ነው። ነገር ግን በጣም ቅርብ ናችሁ ለመፀነስ። ስለዚህ ለማርገዝ ፍላጎት ካላችሁ እንቁላል የምትለቁበትን ቀን ለማወቅ ምልክቶቹን በሚገባ ማወቅ ይኖርባችኋል ። ከዚያም በዚህ ቀን ግንኙነት ማድረግ ይኖርባችኋል ማለት ነው። 📌 2 ሳምንት አልትራሳውንድ ምን ይመስላል ? ምናልባት የ 2 ሳምንታት እርግዝና አልትራሳውንድ አይኖረውም። በዚህ ሳምንት ውስጥ አልትራሳውንድ ብትነሱ አልትራሳውንዱ እንቁላል ከ ኦቫሪያችሁ ሲለቀቅ እና በማህፀን ቱቦ ውስጥ የወንዱን ስፐርም ሲጠባበቅ ሊያሳይ ይችላል። ስለዚህም ይህ ለግንኙነት ዋነኛው ቀን ነው ማለት ነው። በዚህ ቀን እና ከዚህ ቀን 3 ወይም 2 ቀን አስቀድማችሁ ግንኙነት ብታደርጉም መፀነስ ትችላላችሁ ማለት ነው። ለምን ስፐርም ሴል በማህፀናችሁ ውስጥ እስከ 5 ቀን መኖር ስለሚችል ነው። 📌 የሁለተኛ እርግዝና ሳምንት ምልክቶች የሁለተኛው እርግዝና ሳምንት ማለት የኦቭዩሌታችሁ ሳምንት ወይም ግንኙነት ማድረግ ያለባችሁ ሳምንት ማለት ነው። ታዲያ በዚህ ሳምንት ምታዩት ምልክቶች የኦቭሌታችሁ ምልክት ናቸው። እነሱም፦ ➣ከብልት የሚወጣ ነጭ "እንቁላል የሚመስል ፈሳሽ በዚህ ጊዜ ከማህፀናችሁ ግድግዳ ወይም በር የሚወጣ በጣም ጥቃቅን እንቁላል መሰል ወይም ንፋጭ የሚመስል ፈሳሽ ይወጣል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ፈሳሹ ስፐርም ሴልን ወደ የማህፀን ቱቦ እንዲዋኝ ስለሚረዳው ነው። ➣ጠረናችሁ በጣም ደስ የሚል ይሆናል የሆርሞን ለውጥ ስለሚኖራችሁ ፍቅረኛችሁን የበለጠ የመሳብ ነገር ይኖራችኋል። በተለይም ደግሞ የወንዱን ፌርሞን ለማስወጣት የሚረዳችሁ ነገር ነው። ➣የጡት ህመም እና መደደር ከእንቁላል መለቀቅ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የሆርሞኖች ለውጥ ጡቶቻችሁ በትንሹ እንዲታመም ያደርጋሉ። ➣ የዳሌ ህመም ኦቫሪያችሁ እንቁላል ሲለቅ በአንደኛው የሆዳችሁ ክፍል ውስጥ ትንሽ መንቀጥቀጥ ሊሰማችሁ ይችላል። ➣ የወሲብ ፍላጎት መጨመር እንቁላል በምትለቁበት ጊዜ ከፍ ያለ የወሲብ ፍላጎት ይኖራችኋል። ➣ የማኅጸን ጫፍ ለውጦች በዚህ ጊዜ የማህፀን ጫፍ ለስላሳ እና ይበልጥ ክፍት እየሆነ ይመጣል። ለማርገዝ እንዲረዳችሁ ከወር አበባ ዑደት ውስጥ ከ10ኛው ቀን እስከ 18ኛው ቀን ድረስ በየሁለት ቀኑ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ነው - ይህም ማለት በሁለተኛው ሳምንት መጨረሻ እስከ ሶስተኛው ሳምንት መጀመሪያ ድረስ ማለት ነው። 📌የእርግዝና ምልክቶች ምን ያህል በፍጥነት መታየት ይጀምራሉ? ለአንዳንድ ሴቶች የእርግዝና ምልክቶች ከተፀነሱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሊጀምሩ ይችላሉ። አካላዊ ምልክቶች ሊሰማችሁ ይችላል, ወይም የሆነ ነገር በሰውነታችሁ ውስጥ ሲያሳይ ትገነዘባላችሁ። ሌሎች ሴቶች ደግሞ አዎንታዊ የእርግዝና ምርመራ ካገኙ በኋላ እንኳን በሰውነታቸው ላይ ምንም ልዩነት ላይሰማቸው ይችላል። ታድያ በሁለተኛው ሳምንት ውስጥ ከፀነሳችሁ የሚታዩ የእርግዝና ምልክቶች አሉ። እነዚህም ➣ ስፖት ማድረግ ማለትም ነጠብጣብ የደም መፍሰስ ከተፀነሳችሁ ከ5 እስከ 10 ቀናት በኋላ ትንሽ ነጠብጣብ ደም ሊፈሳችሁ ይችላል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ፅንሱ እራሱን ወደ ማህፀን ውስጥ በሚተክልበት ጊዜ ነው። ➣በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ይህ የእርግዝና ሆርሞኖች መኖር በእርግዝና ምክንያት እና በእርግዝና ወቅት ከሚጨምረው የደም መጠን ጋር የተያያዘ ነው። ➣የጡት ህመም ወይም ጥቁሩ ክፍል መስፋት የእርግዝና ሆርሞኖች እንደታዩ የሴቷ ጡት ጡት ለማጥባት መዘጋጀት ይጀምራል። ➣ ድካም አጠቃላይ ድካም አንዳንድ ሴቶች የሚጠብቁት የመጀመሪያ ፍንጭ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ሰውነታችሁ ልጁን ለማሳደግ አንድ ቶን ሃይል ስለሚጠቀም ነው። ➣እብጠት እርጉዝ ስትሆኑ ሰውነታችሁ ብዙ ንጥረ ነገሮችን ለህፃኑ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት የምግብ መፍጨት ሂደቱን ይቀንሳል። ይህ ትንሽ ጋዝ እና እብጠት ሊያስከትል ይችላል። 📌 በእርግዝና መጀመሪያ ላይ አንዳንድ ያልተለመዱ ምልክቶች ምንድናቸው? ➣ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ፣ ➣መፍዘዝ፣ ➣ብጉር ወይም ማድያት ➣ በአፋችሁ ውስጥ የብረት ጣዕም እነዚህ እርጉዝ መሆንዎን የሚያሳዩ የመጀመሪያ ምልክቶች ናቸው። አብዛኛው የመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ምልክቶች በሆርሞኖችዎ ላይ የሚከሰቱ ለውጦች ናቸው። 📌 በ 2 ሳምንታት ላይ ከተፀነሳችሁ የእርግዝና , ምልክቶች ወዲያውኑ አይታዩም። የእርግዝና ምርመራ ብታደርጉ እንኳን የምታገኙት አሉታዊ ውጤት ነው።ለምን የHCG ሆርሞን ገና በሰውነታችሁ ውስጥ አልተመረተም። አዎንታዊ ውጤት የምታገኙት በአራተኛው ሳምንት ላይ ነው። የወር አበባችሁ በሚቀርበት ቀን ማለት ነው። ለዚህም ነው የእርግዝና ምርመራ ስታደርጉ ሁልጊዜም የወር አበባችሁ ከቀረ በኋላ መኖር ይኖርበታል የሚባለው። ታድያ በዚህ ዜዘ የምታዩት የእርግዝና ምልክቶች ጉልህ የሆኑ ናቸው። ነገር ግን ሁለተኛው ሳምንታችሁ ላይ አሁንም ገና እርጉዝ አይደላችሁም። ነገር ግን ምን አልባት ፀንሳችሁ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም በዚህ ወቅት ውሃ መጠጣት ፣ ማጨስ ወይም ቡና መጠጣት ያሉ መጥፎ ልማዶችን ማቆም፣ እንደ እና መደበኛ እና መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጥሩ መንገድ ነው። #እርግዝና #pregnancy #youtube

Surah Al Baqarah Full سورة البقره | Relaxing Calming & Heart Touching Quran | Zikrullah TV
▶︎

Surah Al Baqarah Full سورة البقره | Relaxing Calming & Heart Touching Quran | Zikrullah TV

Surah Yasin (Yaseen) سورة يس | Relaxing heart touching voice | Zikrullah TV
▶︎

Surah Yasin (Yaseen) سورة يس | Relaxing heart touching voice | Zikrullah TV

እርግዝናን ለመለየት የሚያስችሉ 11 ተፈጥሮአዊ ምልክቶች
▶︎

እርግዝናን ለመለየት የሚያስችሉ 11 ተፈጥሮአዊ ምልክቶች

CNS Infections | Clinical Medicine
▶︎

CNS Infections | Clinical Medicine

How to Know that you are Pregnant // Early signs of Pregnancy // Earliest time to do Pregnancy test
▶︎

How to Know that you are Pregnant // Early signs of Pregnancy // Earliest time to do Pregnancy test

Santo Rosário da Madrugada | Instituto Hesed - 21/04
▶︎

Santo Rosário da Madrugada | Instituto Hesed - 21/04

የእርግዝና  3ተኛው ሳምንት ምልክቶች  | The sign of 3rd week pregnancy
▶︎

የእርግዝና 3ተኛው ሳምንት ምልክቶች | The sign of 3rd week pregnancy

እርግዝና ሳይፈጠር የወር አበባ ሊቀር የሚችልባቸው ምክኒያቶች/Reasons for missed period in the absence of pregnancy.
▶︎

እርግዝና ሳይፈጠር የወር አበባ ሊቀር የሚችልባቸው ምክኒያቶች/Reasons for missed period in the absence of pregnancy.

ساعة من السكينة مع القرآن❤️😌 | تلاوة هادئة للنوم والاسترخاء🕊️🎧 | Deep Tranquility
▶︎

ساعة من السكينة مع القرآن❤️😌 | تلاوة هادئة للنوم والاسترخاء🕊️🎧 | Deep Tranquility

Quran recitation in a peaceful voice I Alfatiha, Yasin, AlWaqiah, Arrahman, -By Alaa Aqel
▶︎

Quran recitation in a peaceful voice I Alfatiha, Yasin, AlWaqiah, Arrahman, -By Alaa Aqel

Flying: Relaxing Sleep Music for Meditation, Stress Relief & Relaxation by Peder B. Helland
▶︎

Flying: Relaxing Sleep Music for Meditation, Stress Relief & Relaxation by Peder B. Helland

Learn English While You Sleep (comprehensible input) 💤
▶︎

Learn English While You Sleep (comprehensible input) 💤

ትክክለኛ የእርግዝና አቆጣጠር እርግዝና እንዴት ይቆጠራል //How to calculate pregnancy
▶︎

ትክክለኛ የእርግዝና አቆጣጠር እርግዝና እንዴት ይቆጠራል //How to calculate pregnancy

Antineoplastic Agents | Clinical Medicine
▶︎

Antineoplastic Agents | Clinical Medicine

አራተኛው የእርግዝና ሳምንት ምልክቶች | The sign of week 4 pregnancy
▶︎

አራተኛው የእርግዝና ሳምንት ምልክቶች | The sign of week 4 pregnancy

አስቸኩዋይ የእርግዝና ምልክቶች 5 signs of pregnancy I yenafkot lifestyle
▶︎

አስቸኩዋይ የእርግዝና ምልክቶች 5 signs of pregnancy I yenafkot lifestyle

Ethiopia | የአሜባ በሽታ ምልክቶች እና መፍትሄዎች (Amoebiasis)
▶︎

Ethiopia | የአሜባ በሽታ ምልክቶች እና መፍትሄዎች (Amoebiasis)

Santo Rosário | Sexta-feira | 04:00 | 12/06/2026 | Live Ao vivo
▶︎

Santo Rosário | Sexta-feira | 04:00 | 12/06/2026 | Live Ao vivo

የተለመዱ እና ያልተለመዱ የእርግዝና የመጀመሪያ ምልክቶች| some less common and common symptoms of pregnancy?
▶︎

የተለመዱ እና ያልተለመዱ የእርግዝና የመጀመሪያ ምልክቶች| some less common and common symptoms of pregnancy?

12 የእርግዝና ምልክቶች/Symptoms of Pregnancy #health #doctor #youtube
▶︎

12 የእርግዝና ምልክቶች/Symptoms of Pregnancy #health #doctor #youtube