የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታሪክ/Story of Blessed Virgin Mary
ለፀሀይ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ በቅድመ አያቶቿ በነቴክትካና ጴጥርቃ ህልም እንደታየችው በለሊት የምታበራ ጨረቃ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ነብያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት "መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸው ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነይ ብለው የተናገሩላት። በሐዲስ ኪዳንም በእመቤታችን ምልጃ ቅዳሴ ማርያምን የደረሰው አባ ሕርያቆስም ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ›› በማለት የድንግል ማርያም ጽንሰትና ልደት እንዴት እንደነበር በድርሰቱ አስፍሮታል፡፡ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት የሁላችን እናት ድንግል ማርያም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሳ ከዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኋላ ግንቦት 1 ቀን ተወልዳለች፡፡ እርስዋም ስትፀነስ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከጥንተ አብሶ ጠብቋታል፤ አበሳው አልነካትም፡፡ ይህንንም ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በኃጢአት በተከበበ፣ መርገም በሞላበት ዓለም ውስጥ ከኃጢአት ከበደል ርቃ (ተለይታ) እንደ ጌዲዮን ጸምር በንጽህና የጠገኘች ንጽህት ዘር መሆኗን ሲያስረዳ ‹‹የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር (ኢሳ 1፡19)፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ የውልደቷ ቦታም በሊባኖስ ተራራ እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል ይኸውም መሐሊ መሐሊ ዘሰሎሞን 4÷7-16 ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ምንም ነውር የለብሽም ። ሙሽሪት ሆይ ከሊባኖስ ነይ ብሎ አስፍሮታል። እናት እና እናቷም በተወለደች በስምንተኛ ቀኗ ስሟን ማርያም ብለው ሰይመዋታል። ማርያም የስሟ ትርጓሜ ብዙ ነው። ከዚህም ውስጥ:- ማርያም ማለት የብዙኃን እናት ማለት ነው ። ማርያም ማለት መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው መንግስተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ናትና ማርያም ማለት ጸጋና ሐብት ማለት ነው። የእመቤታችን ወላጆች ለጊዜው በመምከናቸው በሰው ዘንድ ተንቀው የነበሩ ሲሆን የእርሷ መወለድ ሀብት እና ፀጋ ሆኗቸዋልና። ፍፃሜው ግን አማላጅነቷን አውቀው ቃል ኪዳኗን ለሚመጡ ምእመናን ሁሉ ሀብት እና ጸጋ ሆና ተሰጥታለችና ጸጋ ኦና ሐብት ተባለች። በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ፍጽምት ማለት ነው። እግዚአብሔር በባሕርዩ ፍፁም አምላክ ስለሆነ ለምሥጢረ ሥጋዌ ሰው ይሆንባት ዘንድ በመለኮታዊ ጥበቡ የመረጣት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍፅምት ትሆን ዘንድ ይገባል እና በሥጋም በነፍስም ፍፅምት አደረጋት:: ስለምን ማርያም ብለው አወጡላት ቢሉ እንሆ በዚህ ዓለም ከሚመገቡት ሁሉ ምግብ ለአፍ የሚጥም ለልብ የሚመጥን ማር ነው። በገነትም በሕይወት የተዘጋጁ ፃድቃን ቅዱሳን ያም የሚባል ምግብ አላቸው። ከዚህ ሁሉ የበለጥሽ የከበርሽ ነሽ ሲሉ ስለዚህ ማርያም ብለው ስም አወጡላት። እመቤታችን የተወለደች እለት አባቷ ኢያቄም እና እናቷ ሀና ከመጠን በላይ ተደሰቱ። የተወለዱበት ቦታ ግን በስደት በሊባኖስ ተራራ ላይ በመሆኑ ሀና በድሎት አልታረሰችም። ዘመድ አዝማድ ሊጠይቅ ሲመጣ ሁሉም የአራስ ጥሪ ያለውን ይዞ ሲያመጣ አንዲት ቅን ልቦና የነበራት ነገር ግን እጅግ ደሀ የሆነች ሴት በቤቷ ያለውን ጥራጥሬ አሟጣ ሰብስባ ንፍሮ አድርጋ ይዛላት ሄዳ ነበር። አራስ ጥሪው የችግር ቢሆንም ያላትን በማድረጓ እግዚአብሔር ከሌሎች ይልቅ የእርሷን ስጦታ ወዶላታል። ታድያ እኛም የእመቤታችንን ልደት ለማስታወስ ቤት ውስጥ በተመቻቸው ቦታ ሳይሆን ውጪ ንፍሮ ቀቅለን,ቂጣ ጋግረን,ምንጣፍ አንጥፈን ። ዮም ፍስሀ ኮነ እንሆ ድንግል ተወለደች ለአዳም ዘር ሁሉ ብርሃን ሆነ ያመናችሁ ሁሉ ኑ በድንግል ደስ ይበለን እያልን እናከብራለን። ለአባ ሕርያቆስ : ለቅዱስ ኤፍሬም, ለቅዱስ ያሬድ ,ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን። አሜን

ግሩም ድንቅ ነህ | የፅድቅ በር ነሽ | በሙሐዘ ስብሀት ዳግማዊ ደርቤ@21media27

Anchor Media ጎጃም የከተተው የአብይ አህመድ ሰራዊት ምን ገጠመው? ኢትዮጵያ እየመከረች ሳይሆን እያበደች ነው

ሁላችን ከዚህ በኃላ አባታችን ሆይ ስንጸልይ መርሳት የሌለብን አንድ እውነታ || ድንቅ ትምህርታዊ ስብከት || መቀሲስ ፕ/ር ዘበነ ለማ

Bethel Mitiku @Kingdom Sound Worship Night 2026 “Egziabherin Asebkut” Org Song by Kalkidan Tilahun

ልብን የሚነኩ የኪዳነ ምህረት መዝሙሮች ስብስብ|non-Stop Kidane Mihret Mezmur Collection | Ethiopian Orthodox Tewahedo

ሥርዓተ ቅዳሴ

Belle compilation de chansons à Marie

ናይ አቡነ አረጋዊ መዛሙር | ሓምለ 14 | እኩባት መዝሙራት | Non-Stop Tigringa Orthodox Tewahdo Mezmur 2026

ታቦቱን ከቅዱስ አገልግሎቱ ለይቶ በቅርስነት ለማቅረብ የሚደረግ ዘመቻ! መምህር ዘበነ ለማ

🔴 ሩጫዬን ጨርሻለሁ || እጅግ ድንቅ ትምህርት || ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ || Aba Gebrekidan New Sibket 2026

Shakira, Burna Boy - Dai Dai (Official Video)

صلاة المديح - orthodox christian byzantine chant - ترتيل بيزنطي - the akathist to the theotokos

በየቀኑ የሚደመጡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም መዝሙሮች ስብስብ |orthodox mezmur #ተዋህዶ #መዝሙር #ማርያም

Gregorian Chants - Prayer Holy Spirit - The Sacred Prayer Ambience of the Monks

መስቀል በዓል በጉራጌ ይለያል

Stranger Offers Candy! Police Rob Saves the Baby 🍬🚔 | Rosoo Sing Along & Nursery Rhymes

Ocean Police Help the Sea Animals | Good Habits for Kids | Sheriff Zozo - Kids Songs & Cartoons

የቅዱስ ገብርኤል መዝሙሮች ስብስብ - የተመረጡ የቅዱስ ገብርኤል መዝሙሮች|St.Gabriel Ethiopian Orthodox Mezmur Collection 2026

🅾️ ድርሳነ ሚካኤል ድርሳነ ሩፋኤል ድርሳነ ገብርኤል ድርሳነ ራጉኤል ድርሳነ ሳቁኤል ድርሳነ አፍኒን የማኅበረ መላእክት ድርሳን @arone-vlog #eotc

