ዳንኤል 10 ~ የፋርስ ንጉስ አለቃ ~ ፓስተር አስፋው በቀለ www.operationezra.com
የፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ነገር ተገለጠለት፤ ነገሩም እውነት ነበረ፥ እርሱም ታላቅ ጦርነት ነው፤ ነገሩንም አስተዋለ፥ በራእዩም ውስጥ ማስተዋል ተሰጠው። 2 ፤ በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። 3 ፤ ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም። 4 ፤ ከመጀመሪያውም ወር በሀያ አራተኛው ቀን ጤግሮስ በተባለው በታላቁ ወንዝ አጠገብ ሳለሁ፥ ዓይኔን አነሣሁ፥ 5 ፤ እነሆም፥ በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ። 6 ፤ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፥ ፊቱም እንደ መብረቅ ምስያ ነበረ፥ ዓይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፥ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፥ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ። 7 ፤ እኔም ዳንኤል ብቻዬን ራእዩን አየሁ፥ ከእኔ ጋር የነበሩ ሰዎች ግን ራእዩን አላዩም፤ ነገር ግን ጽኑ መንቀጥቀጥ ወደቀባቸው፥ ሊሸሸጉም ሸሹ። 8 ፤ እኔም ብቻዬን ቀረሁ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኃይልም አልቀረልኝም፥ ደም ግባቴም ወደ ማሸብሸብ ተለወጠብኝ፥ ኃይልም አጣሁ። 9 ፤ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉንም ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ። 10 ፤ እነሆም፥ አንዲት እጅ ዳሰሰችኝ፥ በጕልበቴና በእጄም አቆመችኝ። 11 ፤ እርሱም። እጅግ የተወደድህ ሰው ዳንኤል ሆይ፥ እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬአለሁና የምነግርህን ቃል አስተውል፥ ቀጥ ብለህም ቁም አለኝ። ይህንም ቃል ባለኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥሁ ቆምሁ። 12 ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ። ዳንኤል ሆይ፥ አትፍራ፤ ልብህ ያስተውል ዘንድ፥ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቶአል፤ እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ። 13 ፤ የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት። 14 ፤ ራእዩም ገና ለብዙ ዘመን ነውና በኋለኛው ዘመን ለሕዝብህ የሚሆነውን አስታውቅህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ። 15 ፤ ይህንም ቃል በተናገረኝ ጊዜ ፊቴን ወደ ምድር አቀረቀርሁ፥ ዲዳም ሆንሁ። 16 ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሬን ዳሰሰኝ፤ የዚያን ጊዜም አፌን ከፍቼ ተናገርሁ በፊቴም ቆሞ የነበረውን። ጌታዬ ሆይ፥ ከራእዩ የተነሣ ሕመሜ መጣብኝ፥ ኃይልም አጣሁ። 17 ፤ ይህ የጌታዬ ባሪያ ከዚህ ከጌታዬ ጋር ይናገር ዘንድ እንዴት ይችላል? አሁንም ኃይል አጣሁ፥ እስትንፋስም አልቀረልኝም አልሁት። 18 ፤ ደግሞ ሰው የሚመስል ዳሰሰኝ፥ አበረታኝም። 19 ፤ እርሱም። እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፥ አትፍራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ በርታ፥ ጽና አለኝ። በተናገረኝም ጊዜ በረታሁና። አበርትተኸኛልና ጌታዬ ይናገር አልሁ። 20 ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ። ወደ አንተ የመጣሁት ስለ ምን እንደ ሆነ፥ ታውቃለህን? አሁንም ከፋርስ አለቃ ጋር እዋጋ ዘንድ እመለሳለሁ፤ እኔም ስወጣ፥ እነሆ፤ የግሪክ አለቃ ይመጣል። 21 ፤ ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።

እንዴት ይረሳል|| Endet Yeresal|| ፓስተር ዳንኤል አምደሚካኤል|| Pastor Daniel Amdemichael|| PCGIC #tibebuworkeye

ትንቢተ ዳንኤል 12 ~ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ሂድ ~ ፓስተር አስፋው በቀለ

ዳንኤል 11 ጸረ ክርስስቶ ~ ፓስተር አስፋው በቀለ www.operationezra.com

የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ | የሉቃስ ወንጌል - ክፍል 1 | ፓስተር አስፋው በቀለ

የትንቢተ ዳንኤል መጽሐፍ ትንታኔ ክፍል 10 - ፓስተር ዶክተር ተስፋ ወርቅነህ

የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ | ትንቢተ ሕዝቅኤል | ፓስተር አስፋው በቀለ

የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ | መኀልየ መኀልይ ዘሰለሞን | ፓስተር አስፋው በቀለ

የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ |ወደ ገላትያ ሰዎች | ክፍል 2| አስፋው በቀለ (ፓ/ር)

" ማቲዎስ፡ ካብ ፍንፉን ተቐባሊ ቀረጽ፡ ናብ ሕሩይ ሃዋርያ ክርስትና "

ራዕይ 1:9 ~ ፍጥሞ ደሴት በግዞት ~ ፓስተር አስፋው በቀለ

በረኸት ሒዝኻ ኽትወጽእ ብፓስተር ዮናታን ኣብርሃም SHALOMNA TV 2026

ትንቢተ ዳንኤል ~ ማጠቃለያ የክለሳ ትምህርት ~ ፓስተር አስፋው በቀለ www.operationezra.com

Jstudio |29 ሰነ| "ሰራዊት ትግራይ መጥቃዕቲ ከፊቱ"~ጌታቸው። ድሮናት ኢትዮጵያ ኣብ ትግራይ~ ህወሓት። ምክትል ደብረጽዮን ንሕብረት ኤውሮጳ ኣጠንቂቑ።

እግዚያብሔር ከደከምክበት ነገር ያወጣሃል! |God will deliver you| Dr Abreham Teklemedn #gospeltruth #habesha #2026

ዳንኤል 9 ~ 70ኛው ሱባኤ ~ ፓስተር አስፋው በቀለ

Pastor Eyasu Tesfaye | ፓስተር ኢያሱ ተስፋዬ | " በዚያን ጊዜ ይከናወንልሃል "

ዳሰሳ፡- ትንቢተ ዳንኤል Daniel

"How and Why do We Serve the LORD" - By Dr. Abraham Teklemariam. 10/7/23 Morning

ስውሩ ገመድ የብዙ አማኝ እስራት ያለው በበታችነት ስሜት ውስጥ ነው መጥፎና አደገኛው ያለማወቅ ነው /Pastor Asfaw Bekele /

