በሕማማት ዐሥር(10) ፈጽሞ የተከለከሉ ነገሮች

✥✥✥ በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ እና የማይፈጽሙ ሥርዓቶች ✥✥✥ ፩.ስግደት:- በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል:: ፪. ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ✥ ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው ✥ በምሽቱ ሰዓት 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው:: በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ:: ፫.ጾም:- በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች/ አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል:: ፬.አለመሳሳም:- አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም:: ፭. ማማተብ : - በሰሞነ ሕማማት አባቶች ካህናት መስቀል አያሳልሙም ምዕመናን አናማትብም በጠቅላላ በሰሞነ ሕማማት የመስቀል አገልግሎት በቤተክርስቲያናችን የመስቀል አገልግሎት አይሰጥ ምክንያቱም መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለምም ገላ. 3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29 ሞትን በመስቀል ላይ ሞቶ ሽሮት ትንሳኤ ገልጦ ለሚያምኑት ጠላት ዲያቢሎስን የሚሳፍሩበትን መሰቀል ምልክት ሰጣቸው እንዳለ ልብ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንሳኤ ጊዜ እንሳለማዋለን ጠላትን እናርቀበታለን ። ፮.አክፍሎት:- እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው:: ፯.ጉልባን:- ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው:: ፰.ጥብጠባ:- ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው:: ይህም የጌታ ምሳሌ ነው:: ፱.ቄጠማ:- ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን:: እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም:: የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት . የሰሙነ ሕማማት ሥርዓት በፍትሐ ነገስት ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 578 በዚህ በስድስቱ ቀኖች (በሰሙነ ሕማማት) ከቂጣ ከጨው ከውኃ ብቻ በቀር አይብሉባቸው፡፡ በሊህ ቀኖች ከወይን ከሥጋ ተለዩ የኀዘን ቀኖች ናቸውና የደስታ ቀኖች አይደሉም፡፡ ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፡፡ የሚችል እስከ ሌሊቱ ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው ሰውየውም ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻለው ግን የቅዳሜን ጾም ይጹም፡፡ ቁጥር 590 ካህን ሰሙነ ሕማማትን ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል አስቀድሞ ቢያውል ይሻር፡፡ ከሕማማት ቀጥላ ከምትሆን ከቅዳሜ ስዑር በቀር እሑድንና ቅዳሜን የጾመ ካህን ቢኖር ይሻር፡፡ ቁጥር፡ 593 ከካህናት ወገን ማንም ቢሆን በአርባ ጾም በዓርብና በረቡዕም ጾም ወይን መጠጣት አይገባውም ወደ መዋት (ውሽባ ቤት) አይግባ፡፡ በዐቢይ ጾም ወራት ሰው ከሚስቱ ጋር አይተኛ፡፡ ቁጥር 597 ሴቶችም ጌጣቸውን ይተው፡፡ ሁሉም ለእያንዳንዱ በአርባ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል ድኅነታችንና የኃጢአታችን ሥርየት በእነርሱ ነውና፡፡ ይኸውም ሥራ አንዱስ እንኳ በአርባ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ ሕግ የወጣ ነው፡፡ ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን ኃጢአት የሚሠራት ሰው ወዮለት፡፡ በአርባ ጾም በተድላ በደስታ ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን ወዴት አለ? ቁጥር 599 በተባሕትዎ በትሕትና አርባ ቀን ጾምን ይጹሙ፡፡ ከጥሉላት መከልከል ይገባል፡፡ አያግቡም፡፡ ቁጥር 600 በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሣት ክህነት መስጠት ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም፡፡ በእነዚህም ቀኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጅ፡፡ በሰሙነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሐዋርያት ሥራ ወንጌላት የሙታን ፍትሐት በሆሣዕና በዓል ቀን ይነበብ እንጅ፡፡ ቁጥር 601 በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት አይባልም (አይጸለይም)፡፡ ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል ፍትሐት ይፈታል፡፡ ከመሳለም በቀር ጸሎተ ዕጣንም ይጸለያል፡፡ በዕለተ እሑድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም፡፡ ዳግመኛም በውስጧ በአርባ ጾም ከተድላ ከደስታ ወገን ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ መጋባት ክህነት መስጠት ክርስትና ማንሣት ከሹመትም ወገን ስለሚሞቱት ከመጸለይ በቀር ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና ይደረግለታል፡፡ የተከለከሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ካሉ ፩. እጅ ተጨባብጦ ሰላምታ መባባል መሳሳም ፪. ሩካቤ ሥጋ ማድረግ ፫. መስቀል ማሳለም እና መሳለም ፬. ክርስትና ማስነሣት ፭. ለሙታን ፍትሐት ማድረግ ፮. ክህነት መስጠት ፯. የላመ የጣመ ምግብ መመገብ ፰. መሳቅ መጫዎት መጨፈር ፱. አብዝቶ ጠግቦ መመገብ ፲. መስከር ወዘተ ናቸው። @wdasemaryam ✥ ደሳለኝ ዳኜ✥    / @bisratnegarikidusgebrel  

ታቦት ላይ ርግብ ማስቀመጥ አምልኮ ጣዖት ወይስ ሃይማኖታዊ ነው ????
ታቦት ላይ ርግብ ማስቀመጥ ይቻላል ???
▶︎

ታቦት ላይ ርግብ ማስቀመጥ አምልኮ ጣዖት ወይስ ሃይማኖታዊ ነው ???? ታቦት ላይ ርግብ ማስቀመጥ ይቻላል ???

#ደቀይ_ተጠንቀቑ! እዞም 5ተ ነገራት ንኣበ ንስሓ ኣይትንገሩ//ብጹዕ ኣቡነ ናትናኤል@ዕሴትሚድያ-1327መንፈሳዊ
▶︎

#ደቀይ_ተጠንቀቑ! እዞም 5ተ ነገራት ንኣበ ንስሓ ኣይትንገሩ//ብጹዕ ኣቡነ ናትናኤል@ዕሴትሚድያ-1327መንፈሳዊ

ህንፃዎችን አመድ ያደረገው የቬንዝዌላ ርዕደ መሬት! "በሆርሙዝ ሳታስፈቅዱኝ እንዳታልፉ" የኢራን ጦር! የእስራኤሉ ወታደር ተገደለ ወይስ ሞተ? #venezuela
▶︎

ህንፃዎችን አመድ ያደረገው የቬንዝዌላ ርዕደ መሬት! "በሆርሙዝ ሳታስፈቅዱኝ እንዳታልፉ" የኢራን ጦር! የእስራኤሉ ወታደር ተገደለ ወይስ ሞተ? #venezuela

Marokko – Haiti Highlights | Gruppe C, FIFA WM 2026 | sportstudio
▶︎

Marokko – Haiti Highlights | Gruppe C, FIFA WM 2026 | sportstudio

ስለ አርሲ ሦስቱ አባቶች አቡነ ይስሐቅ አቡነ ሉቃስ አቡነ ጴጥሮስ ምን አሉ ?
▶︎

ስለ አርሲ ሦስቱ አባቶች አቡነ ይስሐቅ አቡነ ሉቃስ አቡነ ጴጥሮስ ምን አሉ ?

ቅዳሴ ምንድን ነው?ስንት ሆኖ ይቀደሳል?ምሳሌዎቹ?የፍሬ ቅዳሴ አይነቶች ? በማስቀደስ የሚገኙ ጥቅሞች?
▶︎

ቅዳሴ ምንድን ነው?ስንት ሆኖ ይቀደሳል?ምሳሌዎቹ?የፍሬ ቅዳሴ አይነቶች ? በማስቀደስ የሚገኙ ጥቅሞች?

🎊 Surprise Ajaa'ibaa godhe caaltuu 🎊
▶︎

🎊 Surprise Ajaa'ibaa godhe caaltuu 🎊

The Man Asked If I Was Still Looking for My Son—Then He Said, “I’m the Kid in..." - Calm Dad Stories
▶︎

The Man Asked If I Was Still Looking for My Son—Then He Said, “I’m the Kid in..." - Calm Dad Stories

10 June 2026
▶︎

10 June 2026

ንአበ ነፍስና ክንገሩ ዘይብሎም ነገራት....? ብመምህር ኣስመላሽ ገብረ ሕይወት
▶︎

ንአበ ነፍስና ክንገሩ ዘይብሎም ነገራት....? ብመምህር ኣስመላሽ ገብረ ሕይወት

Press conference by Alice Weidel and Tino Chrupalla! - AfD parliamentary group in the Bundestag
▶︎

Press conference by Alice Weidel and Tino Chrupalla! - AfD parliamentary group in the Bundestag

ሰይፈ ሥላሌ መፀለይ እንዴተ ነው ? #መምህር_ተስፋዬ #የህይወት_ገጠመኝ @kesishenokweldemariam2240
▶︎

ሰይፈ ሥላሌ መፀለይ እንዴተ ነው ? #መምህር_ተስፋዬ #የህይወት_ገጠመኝ @kesishenokweldemariam2240

Ethiopia - የቁጭት ቀብር ተፈፀመ | አንቀፅ 39 ሊሰረዝ…?
▶︎

Ethiopia - የቁጭት ቀብር ተፈፀመ | አንቀፅ 39 ሊሰረዝ…?

ቃየን ከየት አምጥቶ ሚስት አገባ? |  መጽሐፍ ቅዱስ 66ቱ ብቻ ለሚሉ ጥያቄ  | መምህር ዘበነ ለማ
▶︎

ቃየን ከየት አምጥቶ ሚስት አገባ? | መጽሐፍ ቅዱስ 66ቱ ብቻ ለሚሉ ጥያቄ | መምህር ዘበነ ለማ

⭕️ኤርትራዊ ዝኾንካ ከይተሕልፎ ኤርትራዊያን ኣብ ከቢድ ፀገም ይርከቡ | ሾሊኹ ዝወፀ መልአኽቲ ጀነራል ምግበይ ሃይለ
▶︎

⭕️ኤርትራዊ ዝኾንካ ከይተሕልፎ ኤርትራዊያን ኣብ ከቢድ ፀገም ይርከቡ | ሾሊኹ ዝወፀ መልአኽቲ ጀነራል ምግበይ ሃይለ

ፍቅረኛ አለህ ወይ አለችው🫣የድሮ ልብስ ነው የለበሺው አላት😂
▶︎

ፍቅረኛ አለህ ወይ አለችው🫣የድሮ ልብስ ነው የለበሺው አላት😂

✓ የአንድ ዓመት አመርቂ ውጤት/ዛሬውኑ ጀምሩት
▶︎

✓ የአንድ ዓመት አመርቂ ውጤት/ዛሬውኑ ጀምሩት

God Says:"TAKE THIS MESSAGE SERIOUSLY, BECAUSE ONLY YOU ARE SEEING IT"/God Message Now/God Message
▶︎

God Says:"TAKE THIS MESSAGE SERIOUSLY, BECAUSE ONLY YOU ARE SEEING IT"/God Message Now/God Message

Strengthen Germany first! - Markus Frohnmaier - AfD Parliamentary Group in the German Bundestag
▶︎

Strengthen Germany first! - Markus Frohnmaier - AfD Parliamentary Group in the German Bundestag

የሆሳዕና ቅዳሴ አገባብ ሥርዓት/አርኅው ኆኅተ መኳንንት/ቅዳሴ ጎጎርጎረዮስ/ጸልዩ በእንተ አበዊነ ጳጳሳት
▶︎

የሆሳዕና ቅዳሴ አገባብ ሥርዓት/አርኅው ኆኅተ መኳንንት/ቅዳሴ ጎጎርጎረዮስ/ጸልዩ በእንተ አበዊነ ጳጳሳት