የጅስሩ ሐሪማ ሙደሪስ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን የቀብር ስነ ስርዓት!
የሐበሻው ነህውይ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ! ሙሉ ስመማቸ ሸይኽ ሙሀመድ አሚን ሸይኽ አወል ይባላሉ። የዘር ሀረጋቸው በሙሉ በመሻይኽ የታጨቀ የተቅዋና ዙህድ ሰንሰለት ነው። የ2 ወንድ እና የ7 ሴት ልጆች አበአትም ነበሩ።ገና በ7 አመታቸው ለፍዞል ቁርአንን የጨረሱ ሲሆን በ25 አመታቸው ሙሉ ቂርአታቸውን በማጠናቀቅ ለተድሪስ ተቀምጠዋል። እነሸይኽ ሚናስ እና ሸይኽ አጋምሳ ከመሸአይኾቻቸው ተርታ ጉልሃኖቹ ነበሩ። የነህውና ፈናፈን አባት የሆኑትን ሸይኽ ሚናስን (ዓረ) አብዝተው ይወዷቸውና ይዘክሯቸው እንደነበር ደረሶቻቸው ይናገራሉ። በ93 ከ6 ወር እድሚያቸው ወደማይቀረው ሃገር ጉዞ የጀመሩት እነ ሸይኽ ጅስር ገና በለጋ እድሚያቸው በ25 አመታቸው ለማቅራት የተቀመጡ ሲሆን በማቅራት ብቻ 68 አመት ከ6 ወር ያህል አመታትን የቆዩ ሲሆን በ7 አመታቸው ቁርአን መጨረሳቸውን ተንተርሰን ቢያንስ በ6 አመታቸው ቁርአን ጀመሩ ብንል በቂርአት ዘመን 19 አመት ያሳለፉ ሲሆን በማቅራት ያሳለፉትን አመት ስንደምረው በመቅራትና በማቅራት በድምሩ 87 አመት ከ6 ወራትን አሳልፈዋል። ረህመቱሏሂ አለይሂ ረህመተን ዋሲአ። ሸይኾቹ ጅስር/ወደይ ሐሪማን ከመቆርቆራቸው በፊት ሌላ ቦታ ያቀሩ ሲሆን በዚህ ሐሪማቸው ከ40 አመት በላይ ፊቅህ እና በዋናነት ነህውን አቅርተዋል። በዚህም ለአንድ ክፍለ ዘመን በቀረበው ቆይታቸው ለቁጥር የሚታክቱ ደረሶችን ያፈሩ ሲሆን በመሻይኽ ደረጃ ብቻ ቁጥራቸው ከ800 በላይ የሚሆኑ ሙደሪሶች የሳቸውን ኢጃዛ ወስደው በመላ ሃገሪቱ ተሰራጭተው በማቅራት ላይ ይገኛሉ። ለናሙና ያህል የዞብሉ ሙደሪስ ሸይኽ ሙሐመድ አወል ዞብል፣ የሰዶማው ሙደሪስ ሸይኽ ሙሐመድ ሃሺም፣ የሃብሩው ሙደሪስ ሸይኽ ኡስማን እና የሊብሶው ሙደሪስ ሸይኽ ሙሐመድ ሁሰይን የኝሁ ትክ የለሽ ሸይኽ ደረሶች ናቸው።በዚህ የ እውቀት አምባ ላይ ብዙ ፈኖች የሚቀሩ ሲሆን ነህው፣ ፊቅህ፣ በላጋ፣ መንጢቅ፣ ኢልመልከላም (አቂደቱል አሽአሪያ) ፣ ተሰውፍ እና ሌሎችም ፈኖች ይቀራሉ። በተለየ መልኩ ግን በነህውና ተያያዥ ፈኖች ሐሪማው ይታወቃል። እነ ሸይኽ ጅስር (ረህመቱሏሂ አለይህ) በ ኢልማቸው ብቻ ሳይሆን በተቅዋቸው፣ በዙህዳቸው፣ በሱና ክትትላቸው፣ ለሃገር ዱአ አድራጊነታቸው፣ በተዋዱአቸውና በሌሎችም መልካም መገለጫዎቻቸው ይታወቁ ነበር። ደረሶቻቸው ስለሳቸው አውርተው አይጠግቡም። (ሲዋክ ተለይቷቸው አያውቅም)። (ለአቅመ አዳምነት ከደረሱ በሐኃላ የአጅነቢይ ድምፅ ሰምተው አያውቁም)። (ዶህዋ ሶላት አልፏቸው አያውቅም) እና መሰል የስብእና ባለቤትነታቸውን ያይን እማኝ የሆኑ ደረሶቻቸው የምስክርነት ቃሎች ናቸው። ሌላው በግሌ በጣም ከሚያስደምመኝ ነገር የአመራርነት ብቃታቸው ነው። እነሸይኽ ወደይ (ዓረ) ደረሶቻቸውን በመከታተል፣ ችግሮቻቸውን በመጋራት፣ አንድነታቸውን እንዲጠብቁ በመምከር በማይበጠስ ገመድ አስተሳስረዋቸው አልፈዋል። ለዚህም ዋናው ማሳያችን ሁሌም በየአመቱ በሸህሩ ረመዳን ሁሉም ደረሶቻቸው ቂርአታቸውን አቁመው፣ ደረሶቻቸውን ረፍት ሰጥተውና ቤተሰቦቻቸውን ተሰናብተው ወደ ጅስር ሃሪማ ይተማሉ። ወሩን ሙሉ እንቅልፍ አልባ የሆነ ስልጠና ወስደው ስድስቶንም ጭምር ሸይኻቸውን አጿጹመው ወደመጡበት ይመለሳሉ። አለይሂ ረህመቱላህ አሁን በቀጥታ ወደ ስርአተ ቀብራቸው እናምራ፦ ሸይኹ (ረዓ) እለተ እሮብ ሶፈር 21/1445 ዓሂ ወደማይቀረው አለም የተጓዙ ሲሆን እለተ ሃሙስ ሶፈር 22/1445 ዓሂ ለ40 አመት ባቀሩበት ወደይ / ጅስር ሐሪማ ስርአተ ቀብራቸው ተፈጽሟል። በመጨረሻም 2 ወንድ ልጆቻቸው አባታቸውን ተክተው ነህውና ፊቅህ እያቀሩ ይገኛሉ። ካስማ አኢስላማዊ ድርጅት በቦታው ተገኝቶ በትንሹም ቢሆን የኝህን ትክ የለሽ ካስማ የሂወት ታሪክ በወፍ በረርም ቢሆን ለቅምሻ ያህል ይችን ታክል አጋርቷችኃል። ወደፊት ሙሉ የሂወት ታሪካቸውን ይዘን እንደምንመጣ ቃል እንገባለን።ረህመቱሏሂ አለይሂ ረህመተን ዋሲአ። ምንጭ፦ ሸይኽ ሙሐመድ ሐሺም (የሰዶማ ሸይኽ) ሸይኽ አኡስማን (የሀብሩ ሸይኽ) ሸይኽ ሙሐመድ ሁሰይን (የሊብሶ ሸይኽ) ዶክተር ኢድሪስ ሙሐመድ (የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር) የካስማ ዘጋቢ ፊልም ጥንቅሮች #ውለታ_እንደዋዛ #ካስማ_ኢስላማዊ_ድርጅት

#የማይቀረው_ጉዞ || የሸይኽ ሙሐመድ አሚን (ሸይኽ ወደይ) ስርዓተ-ቀብር እና የደረሶቻቸው መልዕክት

ጀነራል አበባዉ ታደሰ በሽምግልና ተመለሰ? እዉነታዉ ታወቀ! ሰበር ዜና Ethiopia breaking news

ካስማ || የሙፍቲ ዳውድ (ሐሪማ) የሕይዎት ታሪክ

🔴ሙስሊሟ ለሙስሊሞች ጥሪ አቀረበች ነብዩ መሀመድ ሰነፍ ኮራጅ ነበር

22 June 2026

የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ መርሃግብር

ግብፅ በደቡብ ሱዳን ተዋረደች ተረክ ሚዛን Salon Terek

ከቪዛ እገዳው በኋላስ? ከአምባሳደሩ የጉዞ ክልከላ ጀርባ ያሉ ጉዳዮች|Awramba Times

የሸይኽ ሙሐመድ ጁድ ሩሐማ ሐሪማ ዚያራ

#ወረብ_ዘሰኔ_ማርያም #በመ/ር_አክሊሉ_ሙሉጌታ

Built To Last - Dr. Corey L. Brown

የአሸንጌ ሐሪማ

መፈንቅለ መንግስት ያሰጋኛል? ሰበር ዜና አብይ አህመድ ዘመነ ካሴ breaking news

|| በሸይኽ ያዕቁብ ሙሐመድ || የቁርኣን ተአምራት || ክፍል 1 || #አፍሪካ_ቲቪ

#የሰኔ ማርያም #ወረብ

“ተቃውሞው ጸረ ህወሐት ወይስ ጸረ ትግራይ?” | ትግሉ መስመሩን ስቷል? የአሉላ እና የቴዎድሮስ ሙግት! 06/22/2026

አቶ ሬድዋን ሁሴን ምን ገጠማቸው ? የዐብን መግለጫ || የሕውሓት አደገኛ ውሳኔ #gubalechethiopia

ሸህ መሀመድ አወል የምንጊዜም ምርጥ እንጉርጉሮ መንዙማ Sheh Mohammed Awol Best Menzuma ||ራምሳ ሚዲያ Ramsa Media

ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ (ረ) ሐሪማ || MUFTI HAJI UMER HARIMA || ክፍል 1

