አላህን ፈለኩት ኢየሱስን አገኘሁት ምስክርነት ||ከእስልምና ወደ ክርስትና || Nabeel Qureshi Amharic

I found this video useful, so I translated it to the best of my ability. Use this link to find the first video I translated from. I apologize for the minor mistakes I make.‌‌    • Seeking Allah, Finding Jesus: The Christia...   መልካም ዜና የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን። ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡- “በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።” መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡- “ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥... እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15) ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል። ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።” — (ኢሳይያስ 53፥10) ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና። {የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29) እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው። 1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል። 2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ። የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇    / @dhugaanniboqachiisa   አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇 http://t.me/BibleAndMe Additional: - [email protected]

"እናቴን እገልሻለሁ ብያታለሁ" ፓስተር ፍፁም  #encounter #ደማስቆ #ሰማይ #christiantube #yttracker #Testimony #Fitsum
▶︎

"እናቴን እገልሻለሁ ብያታለሁ" ፓስተር ፍፁም #encounter #ደማስቆ #ሰማይ #christiantube #yttracker #Testimony #Fitsum

(መሰማት ያለበት) የለማ መገርሳ ታሪክ በሀገረ ጣሊያን፦ የአብይ ግፎች በሮም
▶︎

(መሰማት ያለበት) የለማ መገርሳ ታሪክ በሀገረ ጣሊያን፦ የአብይ ግፎች በሮም

የራውዳ ኣስደናቂ የህይወት ምስክርነት፡ "ኢየሱስ ከሁሉ ይበልጣል" Rawda Testimony
▶︎

የራውዳ ኣስደናቂ የህይወት ምስክርነት፡ "ኢየሱስ ከሁሉ ይበልጣል" Rawda Testimony

World's most beautiful Quran recitation of Surah Yasin (Yaseen) سورة يس | Zikrullah TV
▶︎

World's most beautiful Quran recitation of Surah Yasin (Yaseen) سورة يس | Zikrullah TV

"  ማቲዎስ፡ ካብ ፍንፉን ተቐባሊ ቀረጽ፡ ናብ ሕሩይ ሃዋርያ ክርስትና "
▶︎

" ማቲዎስ፡ ካብ ፍንፉን ተቐባሊ ቀረጽ፡ ናብ ሕሩይ ሃዋርያ ክርስትና "

አስገራሚው የሕይወት ታሪክ | ከእስልምና ወደ ክርስትና የመጣው መሐመድ ወደ ክርስትና የመጣባቸው ምክንያቶች| Haleta Tv
▶︎

አስገራሚው የሕይወት ታሪክ | ከእስልምና ወደ ክርስትና የመጣው መሐመድ ወደ ክርስትና የመጣባቸው ምክንያቶች| Haleta Tv

እውነቱ አስደነገጠኝ! የቀድሞው ሙስሊም ናቢል ቁሬሺ ስለ መሐመድ ህይወት የገለጠው ሚስጥር | Nabeel Qureshi Amharic|
▶︎

እውነቱ አስደነገጠኝ! የቀድሞው ሙስሊም ናቢል ቁሬሺ ስለ መሐመድ ህይወት የገለጠው ሚስጥር | Nabeel Qureshi Amharic|

ሰማይን የሚያስለቅስ ምንድን ነው? | ትንቢተ ኢሳይያስ ሙሉ ትረካ በአማርኛ – (FULL Prophet Isaiah - Amharic Audio Bible) #ትረካ
▶︎

ሰማይን የሚያስለቅስ ምንድን ነው? | ትንቢተ ኢሳይያስ ሙሉ ትረካ በአማርኛ – (FULL Prophet Isaiah - Amharic Audio Bible) #ትረካ

ይኼን ቢያውቁ አይከተሉትም |የሙስ*ሊሞች አላህ ፈጣሪ ነውን? መራራ እውነት @abdo_jaro @ABRAHAM_M7_MEDIA PISTIS PODCAST
▶︎

ይኼን ቢያውቁ አይከተሉትም |የሙስ*ሊሞች አላህ ፈጣሪ ነውን? መራራ እውነት @abdo_jaro @ABRAHAM_M7_MEDIA PISTIS PODCAST

ኣዘራራቢ ፍልልያት ዕብራዊ፡ ​​እስራኤላዊን ኣይሁዳዊን ብዓይኒ ምሁራን ታሪኽን  መጽሓፍ ቅዱስን #eritreanmoviie #history #bible
▶︎

ኣዘራራቢ ፍልልያት ዕብራዊ፡ ​​እስራኤላዊን ኣይሁዳዊን ብዓይኒ ምሁራን ታሪኽን መጽሓፍ ቅዱስን #eritreanmoviie #history #bible

በእስል*ምና ተስፋ ቆረ*ጥኩ | ኢየሱስ ባይደርስልኝ ኖሮ ...ፍቅርን በማጣት እሰ*ቃይ ነበር |@Herald_Tube_With_Gadisa
▶︎

በእስል*ምና ተስፋ ቆረ*ጥኩ | ኢየሱስ ባይደርስልኝ ኖሮ ...ፍቅርን በማጣት እሰ*ቃይ ነበር |@Herald_Tube_With_Gadisa

እጄ ላይ ነዉ የሞተችው  ከእስልምና የወጣበትን አስፈሪ ጉድ አጋለጠ ሙሐመድ አበባው  #BERHAN_50 #paradigmshift  #berhantune
▶︎

እጄ ላይ ነዉ የሞተችው ከእስልምና የወጣበትን አስፈሪ ጉድ አጋለጠ ሙሐመድ አበባው #BERHAN_50 #paradigmshift #berhantune

በዕብራውያን 6 መሰረት ድነታችንን ልናጣ እንችላለን ? / የእሁድ መደበኛ ትሮግራም / ክፍል 1
▶︎

በዕብራውያን 6 መሰረት ድነታችንን ልናጣ እንችላለን ? / የእሁድ መደበኛ ትሮግራም / ክፍል 1

‘መሀመድ የ6 ዓመት ልጅ ማግባቱ ለህሊናዬ እስካሁን እረፍት አይሰጠኝም' ||Mohammed abebaw(መሐመድ አበባው) || #Meskelmedia#2025
▶︎

‘መሀመድ የ6 ዓመት ልጅ ማግባቱ ለህሊናዬ እስካሁን እረፍት አይሰጠኝም' ||Mohammed abebaw(መሐመድ አበባው) || #Meskelmedia#2025

ከመቃብር ጉድጓድ የተረፈው ሐዋርያ!! መጋቢ ዳንኤል መኮንን#Encounter’s#SemayTube #Demasko #Christiantube #Daniel Mekonen
▶︎

ከመቃብር ጉድጓድ የተረፈው ሐዋርያ!! መጋቢ ዳንኤል መኮንን#Encounter’s#SemayTube #Demasko #Christiantube #Daniel Mekonen

ኢየሱስ ኢትዮጲያ ብቻ ነው ማያማልደው:: | Dawit Fassil | Preaching By Dawit Fasil
▶︎

ኢየሱስ ኢትዮጲያ ብቻ ነው ማያማልደው:: | Dawit Fassil | Preaching By Dawit Fasil

ኢየሱስ በመስበኬ ብዙ መከራ ደርሶብኛል አባ ተዋህዶ ሃይማኖት Aba Tewhado Haymanot #paradigmshift  #berhantube # #testimony
▶︎

ኢየሱስ በመስበኬ ብዙ መከራ ደርሶብኛል አባ ተዋህዶ ሃይማኖት Aba Tewhado Haymanot #paradigmshift #berhantube # #testimony

ሂና ባትላል የህንዳዊቷ ምስክርነት || ክፍል 01  || Gezai Yohannes
▶︎

ሂና ባትላል የህንዳዊቷ ምስክርነት || ክፍል 01 || Gezai Yohannes

🔴ሱዳን፡ ዶብ ኢትዮጲያ መጥቃዕቲ//ፋኖ፡ 40 ሰራዊት ኣቢ ቀቲሉ//ንትራምፕ፡ ኣምበርኪኽናዮ፡ ኢራን/23/06/2026
▶︎

🔴ሱዳን፡ ዶብ ኢትዮጲያ መጥቃዕቲ//ፋኖ፡ 40 ሰራዊት ኣቢ ቀቲሉ//ንትራምፕ፡ ኣምበርኪኽናዮ፡ ኢራን/23/06/2026

ቸርች አቃ**ጥዬ አውቃለሁ♦️[ክፍል 1️⃣] |ኢየሱስ ባያገኘኝ ኖሮ…ሼህ አብዶ |ከእስ**ልምና ወደ ኢየሱስ |PistisPodcast @ABRAHAM_M7_MEDIA
▶︎

ቸርች አቃ**ጥዬ አውቃለሁ♦️[ክፍል 1️⃣] |ኢየሱስ ባያገኘኝ ኖሮ…ሼህ አብዶ |ከእስ**ልምና ወደ ኢየሱስ |PistisPodcast @ABRAHAM_M7_MEDIA