የሱናሚ ጎርፍ || የነሸይኽ ጅስር / ወደይ የቀብር ስነስርአት || تشييع جنازة الشيخ جسر - رحمه الله

የሐበሻው ነህውይ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ! ሙሉ ስመማቸ ሸይኽ ሙሀመድ አሚን ሸይኽ አወል ይባላሉ። የዘር ሀረጋቸው በሙሉ በመሻይኽ የታጨቀ የተቅዋና ዙህድ ሰንሰለት ነው። የ2 ወንድ እና የ7 ሴት ልጆች አበአትም ነበሩ።ገና በ7 አመታቸው ለፍዞል ቁርአንን የጨረሱ ሲሆን በ25 አመታቸው ሙሉ ቂርአታቸውን በማጠናቀቅ ለተድሪስ ተቀምጠዋል። እነሸይኽ ሚናስ እና ሸይኽ አጋምሳ ከመሸአይኾቻቸው ተርታ ጉልሃኖቹ ነበሩ። የነህውና ፈናፈን አባት የሆኑትን ሸይኽ ሚናስን (ዓረ) አብዝተው ይወዷቸውና ይዘክሯቸው እንደነበር ደረሶቻቸው ይናገራሉ። በ93 ከ6 ወር እድሚያቸው ወደማይቀረው ሃገር ጉዞ የጀመሩት እነ ሸይኽ ጅስር ገና በለጋ እድሚያቸው በ25 አመታቸው ለማቅራት የተቀመጡ ሲሆን በማቅራት ብቻ 68 አመት ከ6 ወር ያህል አመታትን የቆዩ ሲሆን በ7 አመታቸው ቁርአን መጨረሳቸውን ተንተርሰን ቢያንስ በ6 አመታቸው ቁርአን ጀመሩ ብንል በቂርአት ዘመን 19 አመት ያሳለፉ ሲሆን በማቅራት ያሳለፉትን አመት ስንደምረው በመቅራትና በማቅራት በድምሩ 87 አመት ከ6 ወራትን አሳልፈዋል። ረህመቱሏሂ አለይሂ ረህመተን ዋሲአ። ሸይኾቹ ጅስር/ወደይ ሐሪማን ከመቆርቆራቸው በፊት ሌላ ቦታ ያቀሩ ሲሆን በዚህ ሐሪማቸው ከ40 አመት በላይ ፊቅህ እና በዋናነት ነህውን አቅርተዋል። በዚህም ለአንድ ክፍለ ዘመን በቀረበው ቆይታቸው ለቁጥር የሚታክቱ ደረሶችን ያፈሩ ሲሆን በመሻይኽ ደረጃ ብቻ ቁጥራቸው ከ800 በላይ የሚሆኑ ሙደሪሶች የሳቸውን ኢጃዛ ወስደው በመላ ሃገሪቱ ተሰራጭተው በማቅራት ላይ ይገኛሉ። ለናሙና ያህል የዞብሉ ሙደሪስ ሸይኽ ሙሐመድ አወል ዞብል፣ የሰዶማው ሙደሪስ ሸይኽ ሙሐመድ ሃሺም፣ የሃብሩው ሙደሪስ ሸይኽ ኡስማን እና የሊብሶው ሙደሪስ ሸይኽ ሙሐመድ ሁሰይን የኝሁ ትክ የለሽ ሸይኽ ደረሶች ናቸው።በዚህ የ እውቀት አምባ ላይ ብዙ ፈኖች የሚቀሩ ሲሆን ነህው፣ ፊቅህ፣ በላጋ፣ መንጢቅ፣ ኢልመልከላም (አቂደቱል አሽአሪያ) ፣ ተሰውፍ እና ሌሎችም ፈኖች ይቀራሉ። በተለየ መልኩ ግን በነህውና ተያያዥ ፈኖች ሐሪማው ይታወቃል። እነ ሸይኽ ጅስር (ረህመቱሏሂ አለይህ) በ ኢልማቸው ብቻ ሳይሆን በተቅዋቸው፣ በዙህዳቸው፣ በሱና ክትትላቸው፣ ለሃገር ዱአ አድራጊነታቸው፣ በተዋዱአቸውና በሌሎችም መልካም መገለጫዎቻቸው ይታወቁ ነበር። ደረሶቻቸው ስለሳቸው አውርተው አይጠግቡም። (ሲዋክ ተለይቷቸው አያውቅም)። (ለአቅመ አዳምነት ከደረሱ በሐኃላ የአጅነቢይ ድምፅ ሰምተው አያውቁም)። (ዶህዋ ሶላት አልፏቸው አያውቅም) እና መሰል የስብእና ባለቤትነታቸውን ያይን እማኝ የሆኑ ደረሶቻቸው የምስክርነት ቃሎች ናቸው። ሌላው በግሌ በጣም ከሚያስደምመኝ ነገር የአመራርነት ብቃታቸው ነው። እነሸይኽ ወደይ (ዓረ) ደረሶቻቸውን በመከታተል፣ ችግሮቻቸውን በመጋራት፣ አንድነታቸውን እንዲጠብቁ በመምከር በማይበጠስ ገመድ አስተሳስረዋቸው አልፈዋል። ለዚህም ዋናው ማሳያችን ሁሌም በየአመቱ በሸህሩ ረመዳን ሁሉም ደረሶቻቸው ቂርአታቸውን አቁመው፣ ደረሶቻቸውን ረፍት ሰጥተውና ቤተሰቦቻቸውን ተሰናብተው ወደ ጅስር ሃሪማ ይተማሉ። ወሩን ሙሉ እንቅልፍ አልባ የሆነ ስልጠና ወስደው ስድስቶንም ጭምር ሸይኻቸውን አጿጹመው ወደመጡበት ይመለሳሉ። አለይሂ ረህመቱላህ አሁን በቀጥታ ወደ ስርአተ ቀብራቸው እናምራ፦ ሸይኹ (ረዓ) እለተ እሮብ ሶፈር 21/1445 ዓሂ ወደማይቀረው አለም የተጓዙ ሲሆን እለተ ሃሙስ ሶፈር 22/1445 ዓሂ ለ40 አመት ባቀሩበት ወደይ / ጅስር ሐሪማ ስርአተ ቀብራቸው ተፈጽሟል። በመጨረሻም 2 ወንድ ልጆቻቸው አባታቸውን ተክተው ነህውና ፊቅህ እያቀሩ ይገኛሉ። ካስማ አኢስላማዊ ድርጅት በቦታው ተገኝቶ በትንሹም ቢሆን የኝህን ትክ የለሽ ካስማ የሂወት ታሪክ በወፍ በረርም ቢሆን ለቅምሻ ያህል ይችን ታክል አጋርቷችኃል። ወደፊት ሙሉ የሂወት ታሪካቸውን ይዘን እንደምንመጣ ቃል እንገባለን።ረህመቱሏሂ አለይሂ ረህመተን ዋሲአ። ምንጭ፦ ሸይኽ ሙሐመድ ሐሺም (የሰዶማ ሸይኽ) ሸይኽ አኡስማን (የሀብሩ ሸይኽ) ሸይኽ ሙሐመድ ሁሰይን (የሊብሶ ሸይኽ) ዶክተር ኢድሪስ ሙሐመድ (የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር) የካስማ ዘጋቢ ፊልም ጥንቅሮች #ውለታ_እንደዋዛ #ካስማ_ኢስላማዊ_ድርጅት

#የማይቀረው_ጉዞ  || የሸይኽ ሙሐመድ አሚን (ሸይኽ ወደይ) ስርዓተ-ቀብር እና የደረሶቻቸው መልዕክት
▶︎

#የማይቀረው_ጉዞ || የሸይኽ ሙሐመድ አሚን (ሸይኽ ወደይ) ስርዓተ-ቀብር እና የደረሶቻቸው መልዕክት

#ካስማ_3 || #KASMA_3 || ከሀሪማዎቻችን || አንጋፋው የጎሎጀርሳ የተፍሲር ሀሪማ ታሪክ||  [ክፍል 3 B]
▶︎

#ካስማ_3 || #KASMA_3 || ከሀሪማዎቻችን || አንጋፋው የጎሎጀርሳ የተፍሲር ሀሪማ ታሪክ|| [ክፍል 3 B]

የ ሀጅ ሙህድን ገታ  የ ቀብር ስነስርዐት እና ቂሷ
▶︎

የ ሀጅ ሙህድን ገታ የ ቀብር ስነስርዐት እና ቂሷ

تلاوة القرآن للدراسة والتركيز 📚🕛 | راحة وطمأنينة | Peaceful Focus Quran | محمد هشام
▶︎

تلاوة القرآن للدراسة والتركيز 📚🕛 | راحة وطمأنينة | Peaceful Focus Quran | محمد هشام

በጣም አስለቃሽ ገሳጭ ምክር||ustaz||ኡስታዝ አቡ አብዲላህ||ምርጥ ሙሀደራ |ሀዲስ በአማርኛ|ሀድስ ትምህርት|hadis amharic|dawa amharic
▶︎

በጣም አስለቃሽ ገሳጭ ምክር||ustaz||ኡስታዝ አቡ አብዲላህ||ምርጥ ሙሀደራ |ሀዲስ በአማርኛ|ሀድስ ትምህርት|hadis amharic|dawa amharic

አረቦችን ያስደመመ ምርጥ ራምሳ መንዙማ
▶︎

አረቦችን ያስደመመ ምርጥ ራምሳ መንዙማ

ኪታብ ሲነበብ ይበተናሉ! | በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን || በይናት || ክፍል 6
▶︎

ኪታብ ሲነበብ ይበተናሉ! | በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን || በይናት || ክፍል 6

سه ساعت آخر عاشورا | هیچکس طاقت دیدن این صحنه را ندارد | استاد عالی
▶︎

سه ساعت آخر عاشورا | هیچکس طاقت دیدن این صحنه را ندارد | استاد عالی

ሰራዊቱ እየሸሸ ነው!USA ህውሀት ላይ እርምጃ ወሰደች!#tplf
▶︎

ሰራዊቱ እየሸሸ ነው!USA ህውሀት ላይ እርምጃ ወሰደች!#tplf

ቶና:- የአርባ ጫማ መስጅድ፤ የቱሪዝም ማዕድ
▶︎

ቶና:- የአርባ ጫማ መስጅድ፤ የቱሪዝም ማዕድ

ካስም#2 ll የ300 አመት እድሜ ጠገቡ የቢላው ሐሪማ እጅግ የሚያስቀና ታሪክ አለው በጥሞና ተከታተሉት
▶︎

ካስም#2 ll የ300 አመት እድሜ ጠገቡ የቢላው ሐሪማ እጅግ የሚያስቀና ታሪክ አለው በጥሞና ተከታተሉት

سورة الكهف | الشيخ عفيف محمد تاج  |  Sh: Afif Moh.Taj | Surat Al Kahaf
▶︎

سورة الكهف | الشيخ عفيف محمد تاج | Sh: Afif Moh.Taj | Surat Al Kahaf

ረመዷን በሐሪማዎችችን || ከሾንኬ መንደር
▶︎

ረመዷን በሐሪማዎችችን || ከሾንኬ መንደር

ሪዝቅን ከሚያመጡ ነገሮች || @ElafTube
▶︎

ሪዝቅን ከሚያመጡ ነገሮች || @ElafTube

#ካስማ_3 || #KASMA_3 || ከሃሪማዎቻችን - የሸይኽ ሚስባህ ሃሪማ [ክፍል  8 B] @danatv6506 @minbertv1
▶︎

#ካስማ_3 || #KASMA_3 || ከሃሪማዎቻችን - የሸይኽ ሚስባህ ሃሪማ [ክፍል 8 B] @danatv6506 @minbertv1

ሁሱን ለማሸነፍ የገባው ቄስ ሸሀዳ ይዞ ወጣ አላሁ አክበርርር❤
▶︎

ሁሱን ለማሸነፍ የገባው ቄስ ሸሀዳ ይዞ ወጣ አላሁ አክበርርር❤

ሸይኽ ሙሐመድ አወል ሐምዛ | ሞት_ ነኪር እና ሙንከር አሳዛኝ ምክር
▶︎

ሸይኽ ሙሐመድ አወል ሐምዛ | ሞት_ ነኪር እና ሙንከር አሳዛኝ ምክር

የመዲናዉ_ሹሙ||ኢስማኢል_አህመድ {ኢሳም||እና||አቡበከር መካ||@Al Faruk Multimedia Production
▶︎

የመዲናዉ_ሹሙ||ኢስማኢል_አህመድ {ኢሳም||እና||አቡበከር መካ||@Al Faruk Multimedia Production

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች እና ከተለያዩ ክልሎች ከተወጣጡ አባቶች ጋር ያደረጉት ውይይት
▶︎

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች እና ከተለያዩ ክልሎች ከተወጣጡ አባቶች ጋር ያደረጉት ውይይት

ትግሉ የኃይማኖት ሳይሆን የፖለቲካ ነበር                                                  ሸህ ኡመር ኢማም (ሸህ ኡመር ኮምቦልቻ)
▶︎

ትግሉ የኃይማኖት ሳይሆን የፖለቲካ ነበር ሸህ ኡመር ኢማም (ሸህ ኡመር ኮምቦልቻ)