አገሩ የዘነጋችው የካራማራው ጀግና፤ አሊ በርኪ | Ali Berki | Karamara | Ethiopia
የተከበራችሁ ተመልካቾቻችን ሻለቃ ዓሊ በርኬ ለአገራችን ያበረከቱትን ውለታ አስባችሁ አሁን የሚገኙበትን ወቅታዊ የኑሮ ሁኔታ ተመልክታችሁ የአቅማችሁን ድጋፍ ልታደርጉላቸው እንደምትፈልጉ ገልጻችሁልናል። ለዚህ ኢትዮጵያዊ ክብር ወዳድነታችሁ ያለንን አክብሮት እየገለጽን አድራሻችሁን በገጻችን facebook.com/andafta ብታስቀምጡልን ከሻለቃ ዓሊ በርኬ ጋር ልናገናኛችሁ እንደምንችል እናሳውቃለን። እናመሰግናለን!! ~~~~~~~~~~~~••••••••~~~~~~~~~~~~~~~ አገሩ የዘነጋችው የካራማራው ጀግና፤ አሊ በርኪ ሰላም ጤና ይስጥልን ተመልካቾቻችን ተስፋፊው መሃመድ ዚያድ ባሬ የሚባሉት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ላይ ይፋዊ ወረራ የጀመሩት የዛሬ 42 ዓመት በሰኔ ወር 1969 ዓ.ም ነበር፡፡ በወቅቱ ከንጉሳዊ አስተዳደር ውድቀት በኋላ ገና የመንግስትነት ቁመና ላይ ያልደረሰው የደርግ መንግስት በሰሜን ከህወሓት እና ሻዕቢያ፣ በመሃል አገር ከኢህአፓ እንዲሁም በምዕራብ በኩል መጠኑ አነስተኛ ይሁን እንጂ ከኦነግ ጋር ፍልሚያ ላይ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ ብዙም ወታደራዊ አቅሙ ያልጎለበተው የደርግ መንግስት ከሰይድ ባሬ የገጠመውን ወረራ ተከትሎ በመላው አገሪቱ የእናት አገር ጥሪ መልዕክት አስተላለፈ፡፡ በወቅቱ ከ300 ሺህ በላይ ወጣቶች የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ለስልጠና በታጠቅ ጦር ሰፈር ከተሙ፡፡ የሶማሊያ ጦርነት ሲነሳ በብዙሃኑ ዘንድ ቀድሞ የሚታወሰው ደግሞ በእጅ ቦንብና በክላሽንኮቭ ጠብመንጃ ብቻ የጠላትን ጦር መሪዎች ከእነ ታንካቸው ዶግ አመድ ያደርጉ የነበሩት የያኔው 50 ዓለቃ፤ በኋላም የአገሪቱን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ከኮሎኔል መንግስቱ እጅ የተሸለሙትና አሁን በቀን ስራ ህይወታቸውን የሚገፉት ሻለቃ ባሻ ዓሊ በርኬ ናቸው፡፡ ወታደራዊ መንግስት ስልጣኑን ለህወሓት ኢህአዴግ አስረክቦ ከወጣ በኋላ የመጀመሪያው ዙር ሚሊሻ ዘማቾች አባል የነበሩት ሻለቃ ባሻ ዓሊ በርኬም ለስደት ተዳርገው በኬንያ ስደተኞች ካምፕ ተጠልለው ቆይተዋል፡፡ ወደ ኬኒያ በሚሰደዱበት ወቅት ከኢትዮጵያ ድንበር ሲደርሱ አፈር ዘግነው በመሃረብ ቋጥረው ኬኒያ የገቡት ሻለቃ ዓሊ፤ በማያውቁት ምክንያት ለዘጠኝ ዓመታት በቃሊቲና ዓለም በቃኝ እስር ቤቶች ክስ ሳይመሰረትባቸው ማቀዋል፡፡ ከእስር ቤት ከተፈቱ በኋላ ኑሮን በጎዳናና በቀን ስራ የገፉት ሻለቃ ዓሊ በርኬ ‹‹የወቅቱ የአገራችን የቁርጥ ቀን ልጅ›› የሚሉትን ታማኝ በየነን ሲያደንቁት ቃላት ያጥራቸዋል ቢባል ይቀላል፡፡ ለአጼ ቴዎድሮስ፣ ለደጃዝማች በላይ ዘለቀና ለኮሎኔል አብዲሳ አጋ ያላቸው አክብሮት ከፍተኛ የሆነው ፤እኒሁ የጦር ሜዳ ጀግና፤ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም አምባገነን ቢሆንም አገሩን የሚወድ ሰው ነበር ይላሉ፡፡ አቶ መለስና ፓርቲያቸው ህወሓት ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ አፍራሾች ናቸው›› ይላሉ፡፡ አሁን የተፈጠረው ለውጥ የህዝብ ድጋፍ ያስፈልገዋል የሚሉት ሻለቃ ዓሊ በርኬ፤ ትውልድና እድገታቸው ወለጋ ቢሆንም የኦነግን አክራሪ ፖለቲካ በጽኑ የሚያወግዙ ሲሆን፤ በቅርቡ ከኦነግ አመራሮች ጋር የተለዋወጧቸውን ጠንካራ ቃላትም በቃለ ምልልሳችን አንስተውልናል፡፡ የዚያድ ባሬን ወረራ 42ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባልደረባችን ይርጋ አበበ በሻለቃ ዓሊ በርኬ መኖሪያ ቤት ተገኝቶ ያደረገውን ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል ዛሬ እናቀርባለን፡፡

አሊ በርኪ ከጀግና ወታደርነት እስከ ጎዳና አዳሪነት /ቅዳሜ ከሳዓት/

አሊ በርኬ የጠላት ታንኮችን በእጅ ቦንብ ያቃጠለና የማረከ ጀግና፡፡Part 1

Ethiopia - ጠቅላዩ ስለ አርሲ ጥቃት!፣ ጠቅላዩ ስለኦነግና ፋኖ ጥምረት፣ የአዲስ አበባው ድርድር ከሸፈ፣ ስለወታደራዊ ዝግጅቱ ህወሃት፣ የኤርትራ ቁጣ

የመንግስቱ ሀይለማሪያምን ሚስጢር አውጣ ብለው ገረፉኝ - Ketarik Mahder

ሻለቃ ባሻ አሊ በርኪ የካራማራው ጀግና ክፍል 1
![[አበበ አካሉ] "የአርሲ ኦርቶዶክሶችን አስታጥቋቸው አታስፈጇቸው"! | ፖለቲከኛው ስለ አርሲው ግድያ ዝምታቸውን ሰበሩ | ትብብሩ ተፍረከረከ! | Ethiopia](https://i.ytimg.com/vi/zpAZHAKRsgM/hq720.jpg?sqp=-oaymwEbCNAFEJQDSFryq4qpAw0IARUAAIhCGAG4AvcY&rs=AOn4CLDB9QmJNDPDINWF3HTIi3djORUxQA&usqp=CCc)
[አበበ አካሉ] "የአርሲ ኦርቶዶክሶችን አስታጥቋቸው አታስፈጇቸው"! | ፖለቲከኛው ስለ አርሲው ግድያ ዝምታቸውን ሰበሩ | ትብብሩ ተፍረከረከ! | Ethiopia

ኢቲቪ ወቅታዊ- ከፕሮፌሰር ምንዳርአለው ዘውዴ ጋር የተደረገ ቆይታ ክፍል-1 |etv

“በትግራይ የድሮን ድብደባ?”፣ ዐቢይ “ስለአርሲና ፅምዶ”፣ የቤተመንግስቱ ስብሰባ ውሳኔዎች፣ የዘመነ ደብዳቤ “100 አውደ ዉጊያ”፣ የተከፈቱ ውጊያዎች| EF

"አጼ ኃይለሥላሴን የገደላቸው ዳንኤል አስፋው ነው" ሻ/ል ተስፋዬ ርስቴ | በደርግ ዘመን የደኅንነት መ/ቤት የሕግ መምሪያ ኃላፊ

#EBC ፕሮፌሰሩ ገበሬ - ምንዳርአለው ዘውዴ (ፕ/ር )

“ኮ/ል መንግስቱ በህይወት የታደሉት ሚስት ነዉ” ደራሲ ዘነበ ወላ | Ethiopia
![የካራማራ ጀግኖችና አስደናቂ ገድላቸው -በደረጄ ሀይሌና በአዜብ ወርቁ [ARTS TV WORLD]](https://i.ytimg.com/vi/sSuDdzvOAZM/hq720.jpg?sqp=-oaymwEbCNAFEJQDSFryq4qpAw0IARUAAIhCGAG4AvcY&rs=AOn4CLDOnkiWyxtpm2l934VzmxlJmDewhQ&usqp=CCc)
የካራማራ ጀግኖችና አስደናቂ ገድላቸው -በደረጄ ሀይሌና በአዜብ ወርቁ [ARTS TV WORLD]

በጀግንነት የወራሪውን ታንክ የማረከው ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ Etv | Ethiopia | News

ቆይታ ከቀድሞ ዜና አንባቢዎች ማህሌት ከተማ፤ሙዱ አሊ እና መድሀኒት ሀይሉ ጋር በአዲስ ነገር የበዓል ፕሮግራም

ትረካ - አገሪቷን በዝርፊያ ያጠቧት አባት እና ልጅ | አርአያ ተስፋማርያም |#amharicaudiobooks #tireka #ትረካ #amharicbooks #tplf

አክሊሉ ሐብተወልድ እና እስከ መቃብር የዘለቀ የኢትዮጵያ ፍቅራቸው! ቆይታ ከዶ/ር ሰላማዊት ታደሰ ጋር! @endalegetamultimedia

Lualawi ሉዓላዊ-አቶ ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/መሰራች እና ዋና ጸሀፊ የነበሩ 2008 /Archive/ወመዘክር/

“አንድም ጥይት ያለ ኢላማ ተኩሼ አላዉቅም” ሻለቃ ባሻ አሊ በርኪ | Ali Berki | Ethiopia

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር በውስጥ ጽዳት ምንነት አስፈላጊነትና አተገባበር ዙሪያ ያደረጉትን ውይይት

