ወንድ ልጃቹ በመገረዙ ቢያዝንስ?? እኔ ሁለቱንም ሞክሬዋለሁ/ ቦኒ Bonnie M| Ethiopian in Europe | ዘመን የለሽ
#ግርዛት #ልጆቹን_ለቀቅ_አበቦቹን_ጠበቅ ይህንን ጽሁፍ የጻፍኩት ከተማርኩት, ከተረዳሁት, አንብቤ ብቻ ሳይሆን አጥንቼም, ካወቅኩት ነው! በተለይ ነፍሰጡር በነበርኩበት ወራት የልጄን ጾታ አላውቅ ስለነበር በሁሉም ዙርያ ማንበብና ከዶክተሬ ጋር መወያየት ነበረብኝ! ስለግርዛት ያነሳሁ ቀን..ያኔ ጉዴን አወቅኩ:: 👉🏾የግርዛት ታሪካዊና ሀይማኖታዊ አመጣጥና ጽንሰሃሳቦች በእርግጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ በመነሳት ድርጊቱ በአይሁድ ዘንድ እንደተጀመረ ቢታሰብም የወንድ ልጅ ግርዛት በጥንታዊ ግብጻውያን መጀመሩን ቀደምት የታሪክ ድርሳናት ይጠቁማሉ። ከነዚህም ውስጥ ስድስተኛው ሥርወ-መንግሥት(the sixth density) ከ 2345 እስከ 211 ክርስቶስ ልደት በፊት) የተፈለፈሉት ድንጋዮችና የመቃብር ላይ ሥዕሎች የግርዛት ጥንታዊ ሰነድ ነው ተብሎ ይታሰባል:: በተጨማሪም ከሳክራሕ (በ 2400- ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 1940 ገደማ) ኡሀ(uha) የተሰኘ ግብጻዊ ጸሀፊ የአደባባይ ጅምላ ግርዛት ላይ እንደተሳተፈና ወንዶችም ህመሙን በጽናት መቋቋም እንደቻሉና ይህም የጥንካሬ ምልክት መሆኑን የሚያመላክት ጥቅስ ጠቅሷል! ይህንን ልማድ ከግብፃች የተዋሱት የራሳቸዉ ታሪክ "ሀ"ብለው በመጻፍላይ የነበሩት አይሁዶች ድርጊቱን በመውረስና በማስፋፋት በመፅሀፍ ቅዱስ ጭምር የመፅደቅ እና ያለ መፅደቅ መስፈርት እስከመሆን አደረሱት። በአይሁድ በእስልምናና ክርስትና ሀይማኖቶች እንደ ፅንሰ-ሃሳብ ግርዛት(የወንድም የሴትም) የሚጀመረው ግለሰቦችን እና ህብረተሰቡን "ንጹህ" ለማድረግ የጾታ ስሜትንና የጾታ ፍላጎትን ለመቀነስ ነው:: የሰዎች ወሲባዊነት በእነዚህ ማህበረሰቦች ውስጥ ቆሻሻ ወይም ሀጥያተኝነት ተደርጎ ይታያል:: በዚህ ምክንያት ደስታን የሚሰጡ ክፍሎች ማስወገድ አንድን ሰው በገነት "ለማንጻት" ግልጽ መንገድ ነበር::ስለዚህ ግርዘት በምድራዊ ሕይወት እንደ መስዋዕትነቱ ለዘላለማዊ ሕይወት እንደቅድስናና መለኪያ ሆነ:: በተጨማሪም እንደ የአቅመ ጋብቻ መግቢያ ምልክትነት: ለወሲብ ህይወቱ መረጋጋትና ለፍሬያማ ፅንስ የጾታ ፍላጎትን ለመቀነስና ትኩረትን ወደ ትዳር አጋር ብቻ ለመሰብሰብ; ምቹ ንጽህናን መጠበቂያ ሁኔታ የማይኖር ከሆነ, (የ3ቱም ሀይማኖት መሰረታቸው በቂ ውሀ በማይገኝበት በረሀ ላይ ስለነበር), የተገረዙ አይሁድ ጎረቤቶቻቸውን ካይተገረዙት ክርስትያን ጎረቤቶቻቸውለመለየት, ራስን በራስ ማርካትን ለመግታትና "ትርፍ" ደስታን ለማጥፋት.ሲሆን በተጨማሪም በእስልምናና በአይሁድ እምነት ተከታዬች ዘንድ -ከእንስሳነት በአረብ (ከውሻ ) የመለየት ምልክት ወንድ ልጅ የእናቱን አካል የነካበት አካል የብልቱ ጫፍ (ሽለፈቱ) መወገድ ስላለበት ሸለፈት ያለው ብልት ከሴት ውጪያዊ ብልት ወይም "የእግር መሀል ከንፈር" ጋር ተመሳሳይነት ስላለውና ሸለፈቱን(ሴትነቱን) በማስወገድ ወንድነትን ማላበስ:: ሸለፈቱ የወንድ የዘር ፈሳሽ ወደ ሴቷ በቀጥታ እንዳይደርስ ይከላከላል, እናም የአገሪቱን ህዝብ ቁጥር ለመጨመር (ሸለፈቱ) ማወገድ እንደ መፍትሄ መታየት:: "የሰይጣን ጫፍ" ስለሆነ ተቆርጦ ብቻም ሳይሆን ደሙ በ "ራቢ" (አይሁድ ቄስ) ካልተመጠጠ ስለማይጸዳ:: Metzitzah b’peh) ህመምን የመቋቋም ችሎታንና ወንድነትን ለማምጣት የሚሉ መሰረተ ሀሳቦችን ያካትታሉ!! አይሁድና ግርዛት በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ, አብርሃምንበ 99 አመቱ እራሱን, ቤተሰቦቹን እና አገልጋዮቹንም ጨምሮ በሥጋቸው ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እንዲያስር እግዚአብሔር አዘዘው! (ይህም ግብጻዊው uha’ም እንደጠቀሰው ተመሳሳይ የጅምላ ግርዛት አደረገ ) በየአይሁድ ምሁራን እንደሚጠቁመው በዕብራይስጥ, “ቃል ኪዳን" ማሰር የሚለው የግሪክ ቃል "መቁረጥ" ማለት ነው:: የአብርሃምን ቃል ኪዳንንም ተመልከት. ያልተገረዙትም ከሕዝቦቻቸው ለየ. [ዘፍ 17: 10-14] ሙሴ ከልጆቹን አልገረዘም ነበር ግን [ኢያሱ 5 4-7]. የሙሴ ሚስት ሲፓራ እግዚአብሔር ሙሴን እንደሚገድል ባስፈራራት ጊዜ ልጃቻቸውን ገረዘች! በዘመኑ የነበሩም አይሁዳውያን ካልተገረዙ ፍሊስጤምን ለመቆጣጠር የሚደራጀውን የእያሱን የጦር ውትድርና መቀላቀል አይችሉም ነበር, በዚህም ምክንያት ሁሉም የአይሁድ ታዳጊዎች ለመገረዝ ይፈልጉ ነበር:: ይህ የአይሁድ ባህል ግርዛትን ከትውልድ ትውልድ እንዲያስተላልፍ አድርጎል "Metzitzah b’peh" ከልጁ የተገረዘ ብልት ውስጥ በቄሱ የሚደረግ ደምን መምጠጥ ስርአት ሲሆን.. ህጻናቱን ለብዙ ኸርፕ ኢንፌክሽን በማጋለጡ ድርጊቱ ተከልክሎል:: (***እባካችሁ ስለጎንደር ፈላሻዎች መረጃ ያላችሁ ይህ ድርጊት በኢትዮጵያ በቤተ እስራኤላውያን ዘንድ ይህ ድርጊት ስለመፈጸሙ የምታውቁት ነገር ካለ አሳውቁኝ! እስልምናና ግርዛት በ 5 ኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ሄሮዶተስ በተለያዩ ከፊል ሙስሊም ሴማዎያን መካከል የነበረውን ልማድ አስተዋለ. ጆሴፈስ ደግሞ በአንደኛው መቶ ዘመን አረቦች መካከል ልማድ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል. እንደዚህም ሆኖ ነብዩ መሀመድ (pbuh) የሴቶችን እንጂ የወንዶችን ግርዛትን መፍቀድ አስመልክቶ ምንም አላለም ድርጊቱ ግን መሐመድ ለሴቶች መገረዝ የፈቀደባቸው አንዳንድ ትረካዎች መኖራቸውንና, የወንዶች ግርዛት ተግባር ልማዳዊነትም እንደ fitrah በሀዲት አል ቡኻሪ ላይ ተገልጾል ግን በርካታ የእስልምና ጥናት ምሁራን እነዚህ ዘገባዎች ደካማና ትክክለኛነት የጎደላቸው መሆናቸውን ያምናሉ. ይሁን እንጂ ከንፅህና ጋር በተያያዘ ምክንያት እስካሁን በሙስሊሙ ማህበረሰብ 98% ይተገበራል:: ግርዛት በክርስትና ክርስቲያኖች በመጀመሪያው መቶ ዘመን ግርዛትን በተመለከተ ጠንካራ ተቃውሞ አስነሱ. ይህም "መገረዝ" የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሌላ ትርጉም ያለው መሆኑ ነው. ዘዳ 10:16 ላይና ትንቢተ ኤርምያስ 4:4 "የልባችሁንም ሸለፈት ግረዙ " የሚል በመቀመጡና በጉዳዩም ዙርያ በኢየሩሳሌም በሚገኘው ምክር ቤት መክረው ግርዛትን እንደክርስትና ሀይማኖት መስፈርቶች አልተቀበሉትም:: ሐዋ. 15 ላይም የአሕዛብ ሐዋርያ የነበረው ቅዱስ ጳውሎስ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዳይገረዙ አስተምሯል. (የሐዋርያት ሥራ 21:25)ቀደም ሲል የሴቶችን የሴት ልጅ አባላተ ወሊድን የመቆረጥ ልማድ አስመልክቶ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቲቶ "ስለ መገረዝ ቡድኖች" መጠንቀቅ እንዳለበትም ጽፋል . (ቲቶ 1: 10-16) በነዚህም ምክንያቶች ግርዛት የሀይማኖትዊ ስሩን ስለለቀቀና አስፈላጊነቱ ስላልታመነበት ከክርስቶስ ልደት በኃላ ወደ ሮም ኤምፓየር አውሮፓና እስያ የተበታተኑ ክርስትያኖች, ከዚህ ተግባር ተቆጥበዋል! ቢሆንም ጥቂት ለማይባሉ Jewish orthodox እምነት ባለባቸው ሀገራትና ማህበረተሰብ, ተግባሩ ተጠናክሮ ቀጥሎል!! ግርዛት በአሜሪካ ታሪክ የአሜሪካ የሕክምና ማኅበር እ.ኤ.አ. በ 1928 በወሊድ ጊዜ ሁሉም ወንድ ህፃናት መገረዝ እንዲችሉ በመጽሔቱ ውስጥ አርታኢን አሳትሞ ነበር. ለዚህም በዋነኝነት የተነሳው መደበኛ የመገረዝ ቅድመ-ውሳኔው የማስተርቤሽን abomination (የሴጋን) -የራስን በራስ ማርካት ቀውስ ለመከላከላ ነው! በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ላይ ብዙ ወታደሮች በጦር ሠራዊት ዶክተሮች በግዳጅ ተገረዙ. ሁለተኛው የጦር አውሮፓውያን ተመላሾች ሲመለሱ መገረዝ ንጽሕናን ለመጠበቅ በጣም ቀላልና በሽታን ለመከላከል አስፈላጊና ትክክለኛ ነው ብለው እንዲያምኑ ተደርጓል. በጊዜውም አዲስ ቤተሰቦችም አዲስ የተወለዱ ወንድ ልጆቻቸውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከሆስፒታሎች በቀጥታ ሲገረዙ አልተቃወሙም, እውነታው ግን ምንም አማራጭ አልነበራቸውም. ሆስፒታሎች ይህን ቀዶ ጥገና ለማከናወን የማንንም ሰው ፈቃድ አይጠይቁም ነበር:: በ 1970 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከ 90% በላይ ከሆኑት ወንዶች ልጆች የተገረዙ ሲሆን. በ 1971 የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ የግርዘትን የሕክምና ጽሑፎችን ከመረመረ በኋላ ግርዛት አላስፈላጊና ጉዳቱ ከጥቅሙ እንደሚያመዝን ከዘገቡ በኃላ. የግርዘት ፍጥነት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ጀመረ. አሁን በነጩ ማህበረሰብ በጣም ዝቅተኛ ቢሆንም በጥቁር አሜሪካውያን መካከል ለውጥ ብዙም ለውጥ አላሳየም ቢሆንም በ2010, 63.5 አሜሪካውያን ተገርዘዋል:: 👉🏾የተገረዘ ብልትና ወሲብ ሴቶች ያልተገረዘ ብልት ከተገረዘዉ ብልት ይልቅ በወሲብ ግዜ አመቺና ተመራድጭ እነደሆነ ገልጸናል። ለምን ሲባል ያልተገረዘ ብልት መሃሉ ላይ ዘንግ ስለሌዉና ሸለፈቱም ወደ ላይና ታች እየተሸራተተ, በወሲብ ግዜ በሴቷ ላይ በፍሪክሽን የሚከስተን ህመም ይቀንሳል። በተለመዱ የግርዛት ስህተቶች ከሚከሰቱት የቆዳ ማጠር, መንሻፈፍ ከሚያስከትሉት ሀሳብ ይድናል የብልቱ ስስ ጫፍ በሸለፈት ስለሚሸፈን ከመድረቅና በፓንትና ሱሪ ከመፈቅፈቅና ይከላከለዋል, ይህም ብልቱ numb ደረቅ እንዳይሆንና ሴንሲቲቪቲውንም እንደያዘ እንዲቆይ ያግዘዋል:: ለወንዱ ደሞ የብልቱ ጫፍ በስስ ቆዳ መሸፈኑ ሴቷ ሳትረካ ቀድሞ እንዳይረካ ያግዘዋል። Ladies Inbox me! I’ll explain to you!

አሁን ያ ሁሉ አልፎ ቤቴ ሆኜ ገንዘብ እሰራለሁ…// እሁድን 1 ላይ በቻናል 1//

Ethiopia :- ወንድ ለምን ይገረዛል ? | መቼ ይገረዛል | ስርዓተ ግዝረት | girizat | ግረዛት | ዮናስ ቲዩብ | yonas tube

ERISAT: ኣብ ሃገራዊ ባይቶ ንጉጅለ 15 ብኽድዓት ዝኸሰስዎም 4 ሰባት | ብ/ጀነራል ተኸስተ ሃይለ | 3ይን መወዳእታን ክፋል

Mekoya - የጋዳፊ ቤተሰቦች የት ደረሱ? በእሸቴ አሰፋ Eshete Assefa @ShegerFM1021Radio

በእውቀቱ ስዩም - አንጻር | Antsar - Bewketu Seyoum (ትረካ - Dina Book)

Inside Ethiopia's unique Tribe where I became a QUEEN! (Dorze) 🇪🇹

ለቤከን ወዳጆች in my messy kitchen

14 June 2026

ዘሕዝን መልእኽቲ ካብ ከባቢ ኣስመራን ደንማርክን!!

EMN - ንስኻ ብኣርባዕተ ነገራት ተሓታቲ ኢኻ - ሰሎምን ኣብርሃም - ፈራዳይ ሾውEritrean Media Network

Why Aliens Would NEVER Invade Africa

ገባታይ ባህጊ ብልፅግናን ከይዲ ፖለቲካዊ ድርድርን #ብራኸ_እዋናዊ #ኣብርሃ_ተክሉ ምስ ክንፈ ገብረዮውሃንስ

የባሌ ልደት እንዴት አለፈ…. እድሜውን ገምቱ?

85 Incredible Moments Caught on CCTV Camera

EMS | የአንዳርጋቸው ጽጌ ምላሽ ለብርሀኑ ጁላ

فاهم 36 | سلسلة تذوق العبادات - (1) الصلاة | مع د. أحمد العربي

1ይ ዕለታዊ ዜና ስፖርት ሰንበት 14 ሰነ 2026፦ ልዑል ትጽቢት ኣብ ዝተገብረሉ ግጥም ብራዚልን ሞሮኮን ቬኒ ብልጽቲ ሸቶ ቡዋዲ ድሙቕ ኮኾብ...!

በመተት ስራየና ትዳሬ ተበጠበጠ ስታሳዝን የደባይ ጉድ ኢክራም ለይላ

"ኣቦና ኣውነ ሰላማ ከቢድ መስዋእቲ ዮም ከፊሎም! " ቃለ መሕትት ምስ ኣባላት ምንቅስቓስ ማሕበር መእመናን ሃለቃ ከላሊ ሕሉፍ ኣይተ ብርሃኑ ኣርኣያ

