የኃጢአት ቋት (Pocket of Sin)
የኃጢአት ቋት (Pocket of Sin) ተግባሮቻችን፣ መስተጋብራችን፣ መልካም ስራዎቻችን መንፈሳዊ የሆኑትንም ጨምሮ፣ እንዲሁም ደግሞ ከራሳችን ጋር ባለን ግንኙነት፣ አስተውለን ካልመረመርናቸው አነሳሽ ምክንያቶቻችን የሚያስመሰግኑ ሳይሆኑ ይቀሩና ከነጭራሹ “የኃጢአት ቋት” የኃጢአት መከማቻ ሊሆኑ ይችላሉ። ግለሰቦች ጥሩ መስለው የሚታዩ ተግባራቸውን በገሃድ ሲያከናውኑና ከሌሎችም አበረታች ቃላትንና ወቀሳንም ሊያገኙ ይችላሉ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለመልካም ስራው ይህን አይነት አስተያየቶችን አግኝቶ ነበር። የእርሱን መልካም ስራ ለየት የሚያደርገው በፍጹም ቅንነት፣ ነጻነትና ደግነት ተነሳስቶ ሲሆን የደረሰበትም ወቀሳና ተቃውሞ በቅናት፣ በጥላቻ፣ በንዴት፣ በፍራቻ፣ በትዕቢት እና በጥቅሉ “ከኃጢአት ቋት” ከመንጩ ግፊቶች ነበር። በጊዜው የነበሩት የሃይማኖት መሪዎቹም ከዚህ “የኃጢአት ቋት” ወጥመድ አላመለጡም ነበር። በዘመናችንም የሌሎችን ትኩረት ለማግኝት፣ በራስ መተማመናችንን ላይ ማረጋገጫን ለመፈለግ፣ የብቃትና የመወደድ ጥማቶቻችንን ለማርካት በመፈለግ፣ የመፈለግ ፍላጎታችንን ለማርካት በመፈለግ በጎና ድንቅ ማህበረሰባዊና መንፈሳዊ ስራዎችን ለመስራት የምንነሳሳበት አጋጣሚ አይጠፋም። እነዚህን “የኃጢአት ቋት” አነሳሽ ምክንያቶቻችንን አጥርተንና በምትኩ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹህ ውስጣዊ ተነሳሽነትን እንድናጎለብት ክርስትና እምነታችን ይጋብዘናል። "መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደሆና መርምሩ" በማለት ወንጌላዊው ዮሐንስ ያስተማረው ከዚህ ጋር ይሄዳል (1ኛ ዮሐ 4:1)። ይህ መንፈሳዊ ግጥምም ወደዚህ አቅጣጫ ይመራናል። If discernment is not applied, our actions, including spiritual ones—as well as our interactions and engagements with our inner selves, may be influenced by underlying negative motivations, “Pockets of Sins.” Even positive behaviors can be rooted in subtle, less virtuous impulses. Individuals might publicly promote their deeds, unaware of the underlying factors shaping their motivations. For example, Jesus encountered rejection, violence, mistreatment, and public defamation. The root causes of these responses—such as pride, jealousy, anger, hatred, fear, and insecurity—were underlying influences that contributed to his rejection. Despite being religious leaders tasked with upholding spiritual values, those figures chose to oppose rather than support Jesus and his mission, driven by unconscious biases. Similarly, in modern society, the desire for validation or relevance often motivates seemingly positive actions and outreach efforts. Acts that appear good but are motivated by hidden negative impulses, “pockets of sins” call for thoughtful self-examination and ongoing personal growth. The teaching of St. John the Evangelist fits here when he say "...test the spirits to see whether they are from God..." (1 Jn 4:1) የኃጢአት ቋት (Pocket of Sin) ምንም ሳላስተውል ሕይወትን ስመራ ሁሉም ሰላም መስሎ ቅዱስ የጽድቅ ሥራ ያንን አቀድኩ ያንን አልኩ ብዬም ያንን ተገበርኩ የኃጢአት ቋት ወጥመድ እስረኛ እንደነቡርኩ ከየት እንደመጣ መች አጡትና (ማቴ 13፡52-58) የእህት ወንድሞቹን የቤቱን ገመና የእናቱን ማንነት የጠራቢውን ዝና አውቀውት ሲንቁት ሲሰናከሉበት በኩራትና እብሪት ታስረው በኃጢአት ቋት የነቢዩን ትምህርት የእርሱንም ታምራት አምልጧቸው ቀረ ያ የአምላክ ጉብኝት የዘለዓለም ሕይወት ብርቱ እንደተመኘህ (ማር 10፡21) ሃብትህን ሁሉ ትተህ ተከተለኝ ስልህ ነጻነትህን ጠቆምክ ነውና የሚበጅህ የኃጢአት ቋት ሆኖ የንዋይ ፍቅርህ በፊትህ እስኪታይ ውስጥህን አሳዝኖ ከእኔ ዘንድ አራቀህ ሊይዝህ አፍኖ ለስብከተ ወንጌል ከፊት ተሰልፌ ለመንግሥቱ መስፋት ራሴን አሳትፌ በሥርዓት በሕጉ በወጉም አልፌ መንገዱን ተጓዝኩት ደረቅ ሳልል ጨፌ የኃጢአት ቋት ሆኖ ያነሳሳኝ ታዲያ የታይታው መንፈስ ገዝቶኝ እንደ ባሪያ አዛኝ ልቅሶ ደራሽ ጠያቂ ሕመምተኛ የክፉ ቀን ወዳጅ ተብዬ ቤተኛ መጥፎ ቃል ሳይወጣኝ በአክብሮት አንደኛ የኃጢአት ቋቱ ለካ ሆኖብኝ ጓደኛ መፈለግን ፈልግ ሲለኝ ፋታ ነስቶ ከራሴ አፋለሰኝ ከመንገዴ አውጥቶ

እግዚያብሔር ከደከምክበት ነገር ያወጣሃል! |God will deliver you| Dr Abreham Teklemedn #gospeltruth #habesha #2026

ያገባሁት በ57 አመቴ ነው | አርቲስቱ ታዴ የነገረን አስገራሚ ህይወቱ

አባ ዳዊት ውብሸት፦ የእውነት ነጻነት, Abba Dawit's Song: True Freedom.

#አይሆንም ስል ሆነ #እጅግ ድንቅ አምልኮ ከዘማሪት እየሩስ (ጄሪ) አየለ ጋር#pastor Samuel Wondimu (R I W C Tv Worldwide)

When a Cat Teaches a Baby How to Talk… And It Gets Hilarious 😹👶

የሰላዮች ኃጢአት

All Israeli Panel DESCEND Into CHAOS As Things Get TENSE On Piers Morgan Live!

እረ ጉድ ነው ምን እየተሰማ ነው የ Adonay አዲሷ ፍቅረኛ ዪቲናስ ትሆን | እበቀለዋለው እያለች ነው yutinas and adonay Rilashionship

People Who Messed With The Royal Guard and Regretted It!

ብትሰራም ድሃ የምትሆንበት 3 ስውር ምክንያቶች

I have never eaten such delicious zucchini! Nobody knows this recipe! Only 2 ingredients!

Very Important Advice by Pastor Dawit Bokre

Try Not To Laugh 🤣😂 Best Baby And Dog Funny Moments Ever

Incredible Street Performers – Caught on Camera

አባ ዳዊት ውብሸት፦የማታ ሊጦን፣ Abba Dawit's:- Yemata Liton, Night Prayer

The FULL VIDEO of Trump they didn’t want released

Rowan Atkinson's Brilliant Humor Leaves Celebrities in Tears!

በቤተክርስቲያን ውስጥ የሴቶች እውነተኛ አገልግሎት እና የተሰጣቸው የክብር ስፍራ!

ምሽቱን የደረሰን መረጃ/ሰኔ 19/2018

