በምን እንላያቸው? የሞች ጋር የነበረን ጣፋጭ ቆይታ ክፍል 2 #ድንቅ ሀገር Dink Hager
የም ዞን . . . በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ከሚገኙ የዞን መዋቅሮች ውስጥ አንዷ ናት ፡፡ በተፈጥሮ ውበት የታደለች ምድሪቱ የተዘራባትን የምታበቅል ህዝቦቿ ሰው አክባሪ እንግዳ ተቀባይ ናቸው ፡፡ አብዛኛው የዞኑ ሕዝብ በግብርና የሚተዳደር ሲሆን እንደ ገብስ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ያሉና የተለያዩ የአገዳና የመኽር ሰብሎች ፣ ፍራፍሬና አትክልት በሰፊው በማምረት ይተዳደራሉ ፡፡ በሚያስገርም እና በሚያስደንቅ ሁኔታ በዞኑዋ ላይ ልመና የሚባል ነገር ከቶ አይታሰብም ፡፡ ለዚህም ዋና ምክንያቱ ደግሞ ማህበረሰቡ እርስ በእርስ የመረዳዳት፤ የመተሳሰብ ባህልን ሲወርድ ሲዋረስ ከጥንት አባቶቹ በመረከብ አስጠብቆ በመቆቱ ነው ፡፡ ይህ አስደናቂ ስፍራ የም ዞን ሲሆን ዋና ከተማዋ ሳጃ አዲስ አበባ ጅማ በሚወስደው ዋና የአስፋልት በ239 ኪ/ሜ ላይ ይገኛል ፡፡ ድንቅ ሀገርም ይህን አስደናቂ ስፍራ በውስጡ ስላሉ ታሪካዊ ፤ ሰው ሰራሽ ፤ ተፈጥሮአዊ መስእቦች በሰፊው ለውድ ተመልካቾቻችን ለማስዳሰስ ከመዲናችን አዲስ አበባ ተነስተን ወደ የም ዞን ሳጃ ከተማ ገሰገስ ፡፡ የየም ማህበረሰብ በጆሮ ከሰማነው በላይ ሰው ወዳድ እንግዳ ተቀባይ መሆኑን በአካል ተገኝተን አስተዋልን በቆይታችን እንግዳ መሆናችንን እስክንረሳ ድረስ ከህፃን እስከ አዋቂ የተለየ እንክብካቤ ሳይለየን በየገባንባቸው ወረዳዎችና ቀበሌዎች ምርጥ ቆይታን አሳለፍን ፡፡ በየም ዞን ቆይታችን አንጋፋውን በለምለም መስክ ላይ ተንጣሎ የሚገኘውን የአንጋሪ ቤተ መንግስትን ጎበኘን ፡፡ የየም ማህበረሰብ የራሱን የአስተዳደር መዋቅር መሥርቶ በነገስታት ይተዳደር እንደነበረ ታሪክ ያወሳል ፡፡ በዚህም መሰረት የጋማ ሥርወ መንግሥት ፤የጌሜሎ ሥርወ መንግሥት እና የሞዋ ሥርወ መንግሥት ተፈራርቀው ያስተዳድሩት ሲሆን የአንጋሪ ቤተ መንግስትም ከ13 ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የሞዋ ሥርወ መንግሥት መቀመጫ ሆኖ በማገልገሉ እስካለንበት ግዜ ድረስ ቀደምት ውበቱን እንደያዘ የዞኑ መስእብ ሆኖ ተገቢው ጥበቃ እየተደረገለት በክብር ተቀምጧል ፡፡ በዞኑ ቆይታችን በሳጃ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘውን ለአይን ማራኪ መንፈስን አዳሽ ልዩ ውበት ያለው የብርብርሳ ፏፏቴን ጎበኘን አያይዘንም በማህበረሰቡ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን ከሳጃ በ32 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በፎፋ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ከባህር ወለል በላይ 2939 ሜትር ከፍታ ያለው በልዩ ወረዳው ከሚገኙ ተራሮች የቦር ተራራ ትልቁ ስፍራ የሚይዘውን ስፍራ አቀናን ፡፡ ይህ የቦር ተራራ በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ እንዲሰጠው ካደረገው ውስጥ የብሔረሰቡ አባላት በአመት አንድ ግዜ ጥቅምት 17 በአንድነት ወጥተው ከተለያዩ ዕፀዋት መድኃኒት የሚለቅሙበት ስፍራ በመሆኑ ነው በቦር ተራራ ውስጥ ሃገር በቀል እፅዋቶች ብዛት ያላቸው ለመድሃኒትነት የሚያገለግሉ ስራ ስሮች በሰፊው የሚበቅሉበት ነው ፡፡ ማህበረሰቡ ለደን ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን በአመት አንድ ጊዜ ጥቅምት 17 ብቻ ለሚፈልገው አላማ ከመቁረጥ ውጪ ደኖችን አይመነጥርም እፅዋትን አያጠፋም ፡፡ ድንቅ ሀገሮችም በየም ዞን ባሳለፍናቸው ድንቅ ቆይታዎች ይህንና ሌሎችም ታይተው የማይጠገቡ የቱሪዝም ሃብቶችን የማህበረሰቡን የአኗኗር ሁኔታ በስፋት ስንቃኝ ከርመን ለውድ ተመልካቾቻችን ለማስቃኘት በካሜራችን አስቀርተን 2017 ዓ/ም በኢቲቪ ኢንተርቴመንት ለማስቃኘት ወደድን ፡ ፡ ድንቅ ሀገር ህዳር 2017

የሞች ጋር የነበረን ጣፋጭ ቆይታ ክፍል 3 #ድንቅ ሀገር Dink Hager

“በጄትና በድሮን ማጥፋት”፣ “የነጌታቸው አማፂዎችና ኤርትራ"፣ አዲስ አበባና አንቀፅ-39፣ "400 ወታደሮች ከድተዋል"፣ እጅ የሰጡት ላይ እርምጃ| EF

ሳጃ የነበረን ቆይታ WOW ድንቅ ነበር || ሳጃዎች እናመሰግናለን:: || ድንቅ ሃገር

“ተቃውሞው ጸረ ህወሐት ወይስ ጸረ ትግራይ?” | ትግሉ መስመሩን ስቷል? የአሉላ እና የቴዎድሮስ ሙግት! 06/22/2026

ሃገር ፤ እውቀት ፤ ጉልበት: ግሩም ዘነበ (Girum Zenebe) - The Full Experience | Nibab & Chill Grand Opening

የድንቅ ሃገር ትውስታዎች ክፍል 2፡፡II ድንቅ ሃገር II

ትረካ -የተደበቀው የመለስ አሟሟት |የስደተኛው ማስታወሻ|ተስፋዬ ገ/አብ| #amharicaudiobooks #tireka #ትረካ #amharicbooks #tereka

God Says:"TAKE THIS MESSAGE SERIOUSLY, BECAUSE ONLY YOU ARE SEEING IT"/God Message Now/God Message

ካብዞም ኣብዚ ስእሊ ዘለው ተጋደልቲ ፡ ሓደ ኣነ ኢየ ! # New Eritrean Video 2026

ተፈተወ ተፀልአ ምስ ኤርትራውያን ኣሕዋትና ናይ ሓባር ፀላኢ ደምሲስና ኢና | rwyet entertainment

''የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ነበርኩ...'' የልዑል አስፋወሰን አስገራሚ ገጠመኝ | ክፍል 2| #በነገራችንላይ #BenegerachinLay #DerejeHaile

ግንቦትና ግንቦታውያን! ደረጀ ኃይሌ ከአቶ ፋሲካ ሲደልል ጋር - Benegerachin Lay with Fasika Sidelil @Arts Tv World

Anchor Media ''የኢትዮጵያ ህዝብ ስርዓቱ እጅ እጅ ብሎታል፥ ትዕግስቱ አልቋል። የጊዜ ጉዳይ ነው'' መምህርና ፖለቲከኛ አበበ አካሉ

የጉራጌ ምድር ያስቀናል DINK HAGER ድንቅ ሀገር ውድድሩ ገራሚ ነው ክፍል1#

መዝሙረ ዳዊት መፀለይ ጀምሩ! | ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan New Sibket 2026

ተወዳጁ ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል በቁጥጥር ስር ዋለ! | ከመታሰሩ በፊት ያስተላለፈው ትንቢት "ድምፅ በጥርስ" | ዲና+ News

አጥፊያቸውን የሚወዱት ንጉሥ! ንጉሠ ነገሥቱና "ፍቅር እስከ መቃብር"

የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች ከየቤተሰቦቻቸው የተደረገላቸው የሽኝት እና ምርቃት ፕሮግራም፡፡II ድንቅ ሃገር IIDINK HAGER//

Ethiopia - “ዘመቻው ተከፍቶባኛል” ኤርትራ፣ ኢሳያስ ቤት ሀዘን ገባ፣ የደብረፅዮን ውሳኔ ተላለፈ፣ የመቀሌው ጉዞ ተሰረዘ

