"ሥላሴ ፆታ አላቸዉ" የሊቁ የተሳሳተ ስብከት " #ሥላሴ_ወንድ_ሴት? #orthodoxtewahedo #orthodoxchurch #ቤተሠናያተ
"ሥላሴ ፆታ አላቸዉ" የም'ንፍቅና ትምህርት ዘሩበት" ሥርዋጽ ለማለት ባንፈጥን!!! ሥርዋጽ ለማለት ባንፈጥን!!! ሃይ.አበ.28፥30 ላይ ለእግዚአብሔር ዓይን ጆሮ እጅ እግር እንዳለው የተነገረው ሁሉ ለእግዚአብሔር ገንዘቡ ነው። ነገር ግን አይመረመርም። "ወኵሉ ዘተብህለ ከመቦ ለእግዚአብሔር አዕይንት ወአዕዛን አዕዳው ወአእጋር ወኵሉ ዘተጽሕፈ ውስተ መጻሕፍት ቅዱሳት በእንተ እግዚአብሔር እሙን ወጽድቅ ውእቱ ቦቱ ለእግዚአብሔር ኵሉ ዘዘከርነ ወባሕቱ ኢይትረከብ ወኢይትዐወቅ" ይላል። ብዙዎች የተጻፈውን እንኳ ለመረዳት ጥቂት ጥረት ሳታደርጉ ሥርዋጽ ለማለት እየፈጠናችሁ ነው። መጀመሪያ ጽሑፉን መረዳት ይቀድማል። እናንተ የምትሉት ሌላ መጽሐፉ የሚለው ሌላ ሆነ። ከእናንተ ልጀምር። Anthropomorphism የሚባለውን ክሕደት ልክ ናችሁ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታወግዘዋለች። ለእግዚአብሔር የተወሰነ አካል፣ የተከፋፈለ ቅርጽ ያለው አካል የለውም። ለእግዚአብሔር ቅርጽ፣ መከፋፈል፣ ወሰን የሚሉት ቃላት አይነገሩምና። ከላይ ቅዱስ አትናቴዎስም የገለጸው ይህንን ነው። ወባሕቱ ኢይትረከብ ወኢይትዐወቅ-ነገር ግን አይመረመርም የሚለው ኅሊናችን እንደእኛ እንደሰዎች ቅርጽ አበጅቶ ያንን አምላክ ከማለት እንድንቆጠብ ነው። ለእግዚአብሔር እንደሰው የተወሰነ፣ የተከፋፈለ፣ ቅርጽ ያለው አካል የለውም አልን እንጂ አካል የለውም አላልንም። ያ አካሉ ደግሞ ድንቡልቡል ነው አንልም። ያ በምልአት ያለው አካል ወሰን የሌለበት ዓይን፣ እጅ፣ እግር አለው። ሃይማኖተ አበው የሚገልጽልን ይህንን ነው። ዐይኑ ከሆነ ቦታ፣ እጁ ከሆነ ቦታ፣ እግሩ ከሆነ ቦታ ተከፋፍሎ አለ ማለት ግን ክሕደት ይሆናል። ዐይኑ ካለበት ቦታ ሁሉ እጁ እግሩ አለ። አንዱ ሕዋስ ኖሮ ሌላው የሌለበት ቦታ የለም። ይህንን ካልን መከፋፈል፣ ቅርጽ ማውጣት ውስጥ መግባት ነውና። ይህ ደግሞ አእምሯችን የፈጠረው እንጂ ለእግዚአብሔር አይነገርም። ዐይን፣ እጅ፣ እግር፣...ወዘተ እንዳለው እናምናለን። ዐይኑ፣ እጁ፣ እግሩ፣...ግን የተከፋፈለ፣ ቅርጽ ያለው፣ የተወሰነ ነው አንልም። ይህ ከመመርመር በላይ ነው። የቄርሎስና የአትናቴዎስ ሐሳብ አልተለያየም። Anthropomorphism is the idea of giving human traits or physical shapes to God. ቄርሎስ ያወገዘው ይህንን ነው እንጂ እግዚአብሔር እጅ እግር የለውም አላለም። እንደሰው ያለ ቅርጽ የለውም ነው አለ። ይህ ደግሞ መደበኛው የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ነው። ሌላው በፆታ ጉዳይ እኔ የተማርኩት "ለእግዚአብሔር ሴት ወንድ ተብሎ ፆታ አይነገርለትም" የሚል ነው። ፆታ አላቸው የሚሉ መምህራንም ካሉ በማስረጃ ውይይት ማድረግ ነው እንጂ መሰዳደብ አይገባም። ሁሉንም መምህራን ማክበር መልካም ነው። ፆታ የላቸውም የሚልም፣ አላቸው የሚልም በማስረጃ ማቅረብ ቢቻል መልካም ነው። እስከዚያው እኔ የመምህሮቼን ሐሳብ ማለትም ፆታ የላቸውም የሚለውን ይዤ እቀጥላለሁ። ለእግዚአብሔር እጁ፣ እግሩ፣ ዐይኑ እያለ ሲነገር በሁለት መልኩ ይተረጎማል። አንደኛው ረድኤቱን በማየት፣ በመሄድ፣ በመዳሰስ ስለሚገልጽ ረድኤቱን ሲገልጽ ሁለተኛው ደግሞ ወሰን የሌለበት፣ ያልተከፋፈለ ዐይን፣ እጅ፣ እግር እንዳለው ያመለክታል። ለምሳሌ ሐና ቀንዴ ከፍ ከፍ አለ ስትል ቀንድ ያለችው ሥልጣንን፣ ረድኤትን፣ ክብርን ነው እንጂ ቀንድን አይደለም። እግዚአብሔር በክንፉ ጠበቃቸው ሲልም ረድኤቱን ይገልጻል። ለሐና ቀንድ አላት፣ ለእግዚአብሔር ክንፍ አለው ማለት ግን አይደለም። በዚህ ጊዜ በረድኤት ይተረጎማል። ሌላው መሠረታዊ ሐሳብ ለእግዚአብሔር የሰውነት ክፍል አለው ወይ የሚለው አነጋገሩ ራሱ ስሕተት መሆኑን ነው። የሰውነት አካል ለሰው ነው ያለው። ለእግዚአብሔር የሚነገር የእግዚአብሔርነት አካል ነው። የእግዚአብሔርነቱ አካል ግን ረቂቅ፣ ምሉዕ፣ ወሰን የሌለበት፣ ያልተከፋፈለ ዐይን፣ እጅ፣ እግር....አለው። © በትረ ማርያም አበባው ካሣ #ሥላሴ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #EthiopianOrthodox #መንፈሳዊ #Ethiopia #Amharic #OrthodoxTeaching #Christian #Faith #YouTubeEthiopia #መረጃ #ውይይት #ቤተክርስቲያን #DonkeyTube #ዶንኪቲዩብ #እሸቱመለሰ #እግረኛውሚዲያ #ዋልድባ #Waldeba #EthiopianOrthodox #OrthodoxTewahedo #Ethiopia #Amharic #EthiopianNews #Orthodox #መንፈሳዊ #ወቅታዊ #ሊቃውንት

የ እግዚያብሔር አካላት | ዘማርያም | ታላቁ 🛑 Live

ፆታ ያለው አምላክ የለንም!! መምህራኑ በቁጭት ተናገሩ! ዐራት አይና ገብረ ማርያም ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው።

በቁም የሞታችሁ የአማራ ባንዳ ፋራሹና ትራሳችሁ ይመስክር ጭንቀታችሁን አማራ አይጠፍም

(መሰማት ያለበት) የለማ መገርሳ ታሪክ በሀገረ ጣሊያን፦ የአብይ ግፎች በሮም

ኦርቶዶክስ ከ66ቱ ላይ ጨምራለች ይሉና 66ቱን የት እንዳገኙት አያውቁም | ደፋር ጴንጤ ይልሃል ይሄ ነው | መዝሙረ ያሬድ | መምህር ኤፍሬም | አሐቲ ድንግል

የማያዳግም መልስ // ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ? // ጥያቄና መልስ ክፍል 02

የዛሬ ሳቅ ይለያል ህዝቡን ተዝናና

🔴ሙስሊሟ ለሙስሊሞች ጥሪ አቀረበች ነብዩ መሀመድ ሰነፍ ኮራጅ ነበር

🔴 ሕዝቡ በድሏል ! አዲስ ስብከት በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ( deacon yordanos abebe )

🛑 መምህር ግሩም የማያዳግም መልስ ተመልከቱ! #ክህደቱ የቱ ጋር ነው? #ሥላሴ ጾታ አላቸው? #yeselase tsota #ጉባኤ ኤስድሮስ #አባ ገብረማርያምክህደ

5 ቢሊየን ዶላር በሰመሃል መለስ አካውንት ፣ ህግ ወጥ የወርቅ ዝውውር

ይቅርታ ጠይቀዋል // መደረግ ያለበት አሁን!#ethiobeteseb

መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ ጀምሩ! | ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan New Sibket 2026

''እቲ ንጉስ ነቲ ህዝቢ ኣይሰመዖን፣፣ (1 ነገ 12፣15) '' ተግሳጽ ካብ ብጹእ ኣቡነ ናትናኤል ናብ መራሕቲ - (ብሰ/ወ ካሳሁን እምባየ)

ልዩ ምስጢረ ሥላሴ ነገረ ሥጋዌ የተዳሰሰበት ትምህርት ከመምህር ኤፍሬም ምናለ ጋር!

የመምህር ተስፋዬን ስልክ ቁጥርማግኘት ለምፈልጉ እና ላሰባችሀ

እራሳችንን የምናይበት ድንቅ ስብከት❗️❗️አባ ክፍለ ሥላሴ ❗️ግንቦት 13📍@Mataniya23

ጠ/ሚ ዐቢይ ከመጅሊስ መሪዎች ጋር | PM Abiy Meeting with Majlis Leaders

♦️ጥያቄ ለጴንጤ ♦️18 ዓመት ሙሉ ኢየሱስ የት ነበር

