ያሬድ ነጉ በመጨረሻም ተሳካለት ታርቀው ተጋቡ (@gizemedia1974)

የተወዳጁ አርቲስት የያሬድ ነጉ ሽምግልና መላክ እና ሽምግልናውም ተፈቅዶት እሺ መባሉ ብዙ ጓደኞቹን አስደስቷል ፡፡ ያሬድ በሕይወቱ ውስጥ አንድ ቀን ይህ ደስታ እንደሚኖር እንጂ በቼ እና በምን ያህል ፍጥነት ውስጥ ይህንን ልዩ የሕይወት ምዕራፍ እንደሚቀላቀል እርግጠኛ አልነበረም፡፡ትላንት በልጅነቱ እጅግ አስቸጋሪ በሚባል የድህነት ወለል ላይ ተነስቶ በልጀ ጉልበቱ አይሰሩ ስራ እየሰራ ቤተሰብ ለመደገፍ ጎንበስ ቀና ይል የነበረው ያ ብርቱ ታዳጊ …እነዛ የመከራ እና የስቃይ ቀናት አልፈውለት ዛሬ እንዲህ አሉ በተባሉ ዝነኞች ተከቦ ወፈ ሰማዮን ሁሉ ጠርቶ ሽምግልና ልኮ ድል ባለ ድግስ ሊያገባ ይሰናዳል ብሎ የሚገምተው አይደለም የሚያስበውም ሰው አልተፈጠረም ነበር፡፡ ግን ደግሞ ሕይወት እንዳሰቧት እንዳለሟት የምትገመት አይደለችም እና …ያሬድ ነጉ ፌስታል …ከረሜላ …ጀብሎ ከመሸጥ ተነስቶ እንሆ ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ ሊደርስ በመቻሉ ሁሌም አምላኩን ያመሰግናል፡፡ያሬድ ነገሩ ትላንት እንደዘ ባሉ መከራ እና ስቃዮች ውስት አልፎ ዛሬ ለደረሰብት ደረጃ ደርሶ ደስታውን እንዲህ ሲያጣጥም …ለተመለከቱ ደግሞ ከቁም ነገር መብቃቱን ያስተዋሉ የሰፈሩ ሰዎች እና ዘመዶቹ ምናለ ወላጆቹ አንዴ ቀና ብለው ይህንን ስኬቱን ባዮለት ይሉ ጀምረዋል፡፡ ያሬድ ነጉ በሕይወት ኑረት መካከል ተወልዶ ያደገባትን መርካቶ ሰፈሩን ትቶ ወደ ኮልፌ አካባቢ ከሄደ በኃላ በልጅነቱ ያገኛት የልጅነት ፍቅሩን አብዝቶ የሚወዳትን የፍቅር አጋሩን በተመለከተ በሰይፎ ኦን ኢቢየስ ላይ ቀርቦ ስለ እርሷ ሲጠየቅ ከእርሷ ጋር እልል ያለ ፍቅር ይዞኛል ሲል ነበር የገለፀው፡፡የቀረበችኝ ሰው በመሆኔ እንጂ አርቲስት በመሆኔ አይደለም …በጣም ስነ ስርዓት ያላት ሰው ነች ብዙ ለውጣኛለች …ሰው እንድሆን አድርጋኛለች በማለት በአደባባይ በይፋ የመሰከረላትን የፍቅር አጋሩን ሊያገባ በሀገሪቱ አሉ የተባሉ ታዋቂ የኪነ ጥበብ ሰዎችን እና የኃይማኖት አባቶችን ያቺን ስነ ስርዓት ያላትን ልጅ ወልደው አሳድገው ለዚህ ወደ አበቋት ቤተሰቦቹ ዘንድ ሽምግልና ልኳቸዋል፡፡ ድምፃዊ ..አረጋኝ ወራሸ …ጸጋዬ እሸቱ ሰይፉ ፋንታሁን ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራን ሌሎች አንፋፋ ሰዎችን በመላክ በኢትዮጵያዊ ባህል እና ወግ መሰረት በትላንትናው ዕለት ሽምግልና ልኮ እንሆ ፈቃድ ተሰጥቶታል፡፡ በሴት ወገን በኩልም ከብፁ አቡነ መቃሪዎስ ጀምሮ እጅግ የተከበሩ የሀገር ሽማግሌለዎችም ተገኝተው ሙሽሪትን እና ሙሸራን መርቀዋቸዋል፡፡ ታዳሚውም በስራው ብዙዎች ይወዱታል ጨዋታ አዋቂነቱና ቅንነቱን የቅርብ ጓደኞቹ ባገኙት አጋጣሚ መሰክሩለታል፡፡ የሰው ልጅ የህይወት ታሪክ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም እንዲያው ለመረጃ ያህል እስኪ ያሬድ ታሪክ እጅግ አጠርባለ መልኩ እንዲህ ነው ብለን በጭልፋ ታህል እንጨልፍላችሁ፡፡ ወላጆቹን በሞት ያጣ ከቤተሰቦቹ ተለይቶ በመርካቶ ተወልዶ መርካቶ ያደገ የአራዳ ልጅ ነው፡፡ ያራዳ ልጅ ማለት ቤተሰቡን ማህበረሰቡንና ሀገሩን የሚወድ ማለት ነው፡፡ መርካቶ ደግሞ አራዳና ተወዳጆችን የምታመርት ሰፈር ስለመሆኗ ሳይታለም የተፈታ ነው ፡፡ ያሬድንም መርካቶ አፍርታ አራዳ አድርጋዋለች፡፡ በዛ ላይ ስራ ወዳድ ሆኗል፡፡ መቼም ስራ መውደዱና የነቃ ህሊና ባለቤት መሆኑን ለአሁኑ ማንነቱ እንደጠቀመው ግልጽ ነው ፡፡ያሬድ ማስቲካ ሲጋራ ከረሜላ ሌሎችም ነገሮችንና ሎተሪ በመሸጥ በማሰቦቹን ማገዝ እና ህይወቱን መግፋት ጀመረ፡፡ አሳዳጊዎቹ ማለትም በአደራ የተቀበሉት እናቱ መውለድ አይችሉም ነበር ነገር ግን በአደራ ወስደው ያሳደጉትን ልጅ … ያሬድ ነጉን፡፡ እንደ አብራክ ከፋያቸው በመቁጠርና በፍጹም የእናትነት ፍቅር አሳድገውታል፡፡ አብዛኞቹ የሀገራችን እናቶች ልጆቻቸውን ለማሳደግና ገመናቸውን ለመሸፈን የአቅማቸውን ይሰሩ ነበር ፡፡ሁለቱ የያሬድ አሳዳጊዎች ማለትም አቶ አበራ ለገሰና ወይዘሮ ሸዋዬ ተመስገን ከያሬድ አባት ጋር የስጋ ዝምድና ያህል ይዋደዱና ይቀራረቡ ስለነበር ያሬድን በምድር የሰጠውሽን በሰማይ እጠይቅሻለሁ ብሎ የያሬድ ወላጅ አባት በህይወት ከማለፋቸው በፊት በአደራ ይሰጡና የያሬድን እህት ደግሞ ለአክስታቸው የተሰጠች ቢሆንም ሁለቱ ግን ተለያይተው መኖር ስላልቻሉ የያሬድ አሳዳጊዎ ጋር ሆና ከያሬድ ጋር መኖር ጀመረች፡፡ አሳዳጊዎች ሁለቱን ልጆች ለማሳደግ ሕይወት ከባድ ሆናባቸው ነበር፡፡ አዳጊ አባት የአምስት መቶ ብር ደሞዝተኛ ሲሆን በመንግስት ድርጅት ውስጥ በጥበቃ ስራ ተሰማርተው ነበር ይህንን ቤተሰብ የሚያስተዳድሩት፡፡ እናት ደግሞ ኑሮን ለመግፋት ህይወትን ለማሸነፍና… የተሻለ ኑሮ ለመኖር ከሰል እየሸጡ አልጋዎችን በሦስት ብር እያከራዩ ከጉርሻቸው የተረፈውን እቁብ እየጣሉ ኑሯቸውን ለማሸነፍ ይሯሯጡ ነበር፡፡ ያሬድ አራተኛ ክፍል እስኪደርስ ድረስ አንድ ዮኒፎርም ለጋራ ከተጓደኛው ጋር ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን ጓደኛ ልብሶ ከሄደ ከሰዓት ያሬድ ወደ ትምህርት ቤት ለብሶት ነበር የሚሄደው፡፡ ያሬድ ነጉ ለራተኛ ክፍል በኋላ ሰፈራቸው በእናት አበበች ጎበና በሚደረገው እርዳታ ተመዝግቦ ብርድ ልብስ አንሶላ ሳሙና ሁለት ደርዘን ደብተርና በዓመት ሁለቴ ዪፎም እየተቻለለትና እየታገዘ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን የካቲት 23 እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ድላችን በተሰኘው ትምህርት ቤት ያጠናቀቀ ሲሆን ከትምህርት መልስ ወደ ስራ ተመልሶ በመርካቶ ጎዳናዎች ላይ ለስራ ወዲያ ወዲህ ይል ነበር፡፡ ነበር በዚህ አይነት መልኩ አቋሙ እስኪጠነክርበት እድሜ ድረስ ተደጋጋሚ ይወትን አሳለፈ ያሬድ ከልጅነቱ ጀምሮ ሙዚቃ መስማት የሚወድ ሲሆን ይኖሩበት የነበረበት ሰፈር የነበረ አንድ ልጅ ሰፈር ውስጥ ባላንድ ክበብ ውስጥ ይዘፍን ስለነበር ያሬድ በእርሱ አማካኝነት ሙዚቃን ተቀላለቀ፡፡ Popular artist Yared Negu has reached a significant milestone in his life: his traditional wedding engagement (Shimglina) has been successfully accepted by his partner’s family. Surrounded by renowned artists, religious leaders, and beloved friends, Yared’s journey from a childhood of extreme poverty in Merkato to the success he enjoys today is a testament to resilience and hard work. Yared grew up in the bustling streets of Merkato, where he supported his family by selling candy, chewing gum, and lottery tickets. Raised with immense love by his adoptive parents, Ato Abera Legesse and W/ro Shewaye Temesgen, he overcame incredible odds—including sharing a school uniform with a friend and relying on community support—to complete his education. His musical journey began in the vibrant culture of Merkato, eventually leading him to become the star he is today. Today, as he prepares to marry the woman who helped him become a better man, his story serves as a beacon of hope for all. #gizemedia1974 ጊዜ ሚዲያ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ያልታዩ፣ ያልተሰሙ እና ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማምጣት ለተመልካች ያደርሳል! ለቻናላችን አዲስ ከሆኑ አሁኑኑ ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑን! ስራችንን ተመልክተው ከወደዱት Like ያድርጉ! ሃሳብ ወይም አስተያየት ካሎት በኮመንት ባሩ ላይ ያስቀምጡልን! የተለያዩ መረጃዎችን ለኢትዮ አዲስ መረጃ ማድረስ ከፈለጉ ወይም በስፍራው ተገኝተን እንድንዘግብልዎ የሚፈልጉት ማህበራዊ ጉዳዮች ካሉ በሀሳብ መስጫ ሳጥናችን ላይ አድራሻዎን ያስቀምጡልን!

🛑 ያልተጠበቀ ዘረፋ ጌድዮን ዳንኤልን አሳዛኝ ነገር ገጠመው የጃኒ ስህተት
▶︎

🛑 ያልተጠበቀ ዘረፋ ጌድዮን ዳንኤልን አሳዛኝ ነገር ገጠመው የጃኒ ስህተት

ያሬድ ነጉ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከሚገኙ ታራሚዎች ጋር | Yared Negu
▶︎

ያሬድ ነጉ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከሚገኙ ታራሚዎች ጋር | Yared Negu

ልደት 🥳 #zebibagirma
▶︎

ልደት 🥳 #zebibagirma

የገዛ ሚስቴ ልታስገድለኝ  7መቶ ሺ ብር ከፈለች |ሞቴን ስትጠብቅ በሕይወት መጣሁ(@gizemedia1974)
▶︎

የገዛ ሚስቴ ልታስገድለኝ 7መቶ ሺ ብር ከፈለች |ሞቴን ስትጠብቅ በሕይወት መጣሁ(@gizemedia1974)

የተወዳጁ ድምፃዊ ያሬድ ነጉ ሽምግልና በታዋቂ ሰዎች እና ጳጳሳት ደመቀ Shimgilina by a famous artist yared negu
▶︎

የተወዳጁ ድምፃዊ ያሬድ ነጉ ሽምግልና በታዋቂ ሰዎች እና ጳጳሳት ደመቀ Shimgilina by a famous artist yared negu

ሚሊዮን ብሮችን የተካደው ግለሰብ |  ከጥንዶቹ አርቲስቶች ጀርባ ያሉ ያልተሰሙ እውነቶች |  ያማሩት የሠርግ ልብሶች ምስጢር
▶︎

ሚሊዮን ብሮችን የተካደው ግለሰብ | ከጥንዶቹ አርቲስቶች ጀርባ ያሉ ያልተሰሙ እውነቶች | ያማሩት የሠርግ ልብሶች ምስጢር

አሁን ያ ሁሉ አልፎ ቤቴ ሆኜ ገንዘብ እሰራለሁ…// እሁድን 1 ላይ በቻናል 1//
▶︎

አሁን ያ ሁሉ አልፎ ቤቴ ሆኜ ገንዘብ እሰራለሁ…// እሁድን 1 ላይ በቻናል 1//

7 ዓመት ሙሉ የፀባችን ምክንያት እንጋባ ማለቴ ነበር! ስለ ባሌ ማንም አስተያየት መስጠት አይችልም! #jamfamily#gizachewashagrie#love
▶︎

7 ዓመት ሙሉ የፀባችን ምክንያት እንጋባ ማለቴ ነበር! ስለ ባሌ ማንም አስተያየት መስጠት አይችልም! #jamfamily#gizachewashagrie#love

አብርሐም ወልዴ እና ቴዲ አፍሮ...የአሁን መረጃዎች DerPressNews June14,2026
▶︎

አብርሐም ወልዴ እና ቴዲ አፍሮ...የአሁን መረጃዎች DerPressNews June14,2026

ልጄን አንድ ላይ አሳደግን! | Liyu and kidus
▶︎

ልጄን አንድ ላይ አሳደግን! | Liyu and kidus

//ከውበት በላይ// "ልጄ እየራበውም ቢሆን እኔ ካልበላሁ ቢሞት አይበላም"🥺 //በእሁድን በኢቢኤስ//
▶︎

//ከውበት በላይ// "ልጄ እየራበውም ቢሆን እኔ ካልበላሁ ቢሞት አይበላም"🥺 //በእሁድን በኢቢኤስ//

📢ህያብ ይቅርታውን ተቀበለች😱//የተንቢ እና ቤተሰቡ ተሰብስቦ ውሳኔ አሳወቁ😱😳
▶︎

📢ህያብ ይቅርታውን ተቀበለች😱//የተንቢ እና ቤተሰቡ ተሰብስቦ ውሳኔ አሳወቁ😱😳

Seifu on EBS: ያሬድ ነጉ ከጎዳና አንስቶ የሚያሳድገው ኢሳያስ | Yared Negu And Isaias
▶︎

Seifu on EBS: ያሬድ ነጉ ከጎዳና አንስቶ የሚያሳድገው ኢሳያስ | Yared Negu And Isaias

የማያልቀው የቤተሰብ ጉድ|ወንድሜን በድግመት አሳብዳው 2 ፍቅረኞች በአንዴ ያዘችበት(@gizemedia1974)
▶︎

የማያልቀው የቤተሰብ ጉድ|ወንድሜን በድግመት አሳብዳው 2 ፍቅረኞች በአንዴ ያዘችበት(@gizemedia1974)

ምን አይነት ፅናት ነው ? ይህ ከቃል በላይ ነው  #story #lovestory #ethiopia #ታሪክ#podcast
▶︎

ምን አይነት ፅናት ነው ? ይህ ከቃል በላይ ነው #story #lovestory #ethiopia #ታሪክ#podcast

ሰኔ 09/2018፥ የአሁን ሰበር መረጃዎች!#EthiopiaNews #breakingnews #DailyMereja #AnchorNews #News June 16/2018
▶︎

ሰኔ 09/2018፥ የአሁን ሰበር መረጃዎች!#EthiopiaNews #breakingnews #DailyMereja #AnchorNews #News June 16/2018

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለውከዚህ ዓለም በሞት ተለየ|ምን ገጠመው(@gizemedia1974)#SemhagnBelew
▶︎

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለውከዚህ ዓለም በሞት ተለየ|ምን ገጠመው(@gizemedia1974)#SemhagnBelew

/ቤት ያፈራው/ ከፍሪጅ ውስጥ ቅቤ ነው ብለው ወሰዱት 😂"
▶︎

/ቤት ያፈራው/ ከፍሪጅ ውስጥ ቅቤ ነው ብለው ወሰዱት 😂"

ያሬድ ነጉ ተሞሸረ/ ሚስቱ ማናት? የት ተዋወቁ?// እውነት  ሀይማኖቱን ቀይሯል?/Yared Negu
▶︎

ያሬድ ነጉ ተሞሸረ/ ሚስቱ ማናት? የት ተዋወቁ?// እውነት ሀይማኖቱን ቀይሯል?/Yared Negu

እኔን አረብ ሀገር ልኮ ከሰራተኛዬ ጋር መማገጥ ጀመረ@gizemedia1974
▶︎

እኔን አረብ ሀገር ልኮ ከሰራተኛዬ ጋር መማገጥ ጀመረ@gizemedia1974