አስቴር: የእግዚአብሔር ማዳን //እንዳሻው ነጋሽ// Esther: the saving acts of God// Endashaw Negash
የአስቴር መጽሐፍ የእግዚአብሔር ስም ያልተጠቀሰበት ነገር ግን ሥራው በኋይል የተገለጠበት መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ ታሪክ የተፈጸመው በመጀመሪያው ዙር ከምርኮ ተመላሾች እና በሁለተኛው ዙር ከምርኮ ተመላሾች መካከል ነው። የታሪኩ ማእከላዊ ትኩረት የእግዚአብሔር ማዳን ነው። መርዶክያስ ለሐማን አክብሮት ባለመስጠቱ (ባለመስገዱ) አዳር በተባለው በአሥራ ሁለተኛ ወር፣ በአሥራ ሦስተኛ ቀን የአይሁድን ሕዝብ ሁሉ ለማጥፋት ደብዳቤ ተጽፎ ቢበተንም እግዚአብሔር ጣልቃ በመግባቱ ነገሩ ተገልብጦ ያ ዕለት የደስታ ቀን ሆነ፤ የፉሪም በዓል ጅማሬ ሆነ። በመርዶክዮስና በሐማን መካከል የነበረው ግጭት በሁለት ሰዎች መካከል ከሚከሰት ግጭት ያለፈ ነው። ሐማን አማሌቃዊ ነው፤ አማሌቃውያን ደግሞ የእስራኤል ሕዝብ ከግብፅ ባርነት ነጻ በወጡ ጊዜ በመንገዶቻቸው ላይ ቆመው በመቋቋማቸው እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የተናገረው ነገር እና ሙሴ ስለዚህ ሕዝብ ለኢያሱ የሰጠው መመሪያ በኦሪት መጻሕፍት ተመዝግቧል። የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሳዖልም ይህን ሕዝብ እንዲያጠፋ ትእዛዝ ቢሰጠውም ሙሉ በሙሉ አልፈጸመውም። በግምት ከ500 ዓመታት በኋላ ከቢንያም ወገን በሆነው በመርዶክዮስ እግዚአብሔር አስቀድሞ የተናገረውን ወደ ፍጻሜ ለማምጣት እንደ ተነሣ ይህ ታሪክ ያሳያል። የሐማን ጥረት በእግዚአብሔር የማዳን ታሪክ ላይ የተቃጣ የጥፋት ጥረት ነው። የእግዚአብሔር ዕቅድ በማንም አይቀለበስም። ሞትን የደገሰው ሞተ፣ የተጨነቀችው ከተማ እልል አለች፣ ለማጥፋት ሲዘጋጁ ከነበሩት ውስጥ አንዳንዶች ወደ አይሁድነት ተቀየሩ፣ ሞት የተደገሰለት ሕዝብ ስጦታ ሲለዋወጥ እና በዓል ሲያከብር ዋለ፤ ነገሩ ተገለበጠ!! ይህን ቪድዮ በመመልከት የመጽሐፉን ትኩረት መረዳት ይቻላል።

AMHARIC AUDIO BIBLE-መጽሃፈ አስቴር/ Esther

በውበቷ ወገኖቿን ያዳነችው የንግስት አስቴር የመጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ ታሪክ | @gedamattv

✨ተሃድሶ! ሁሉም አማኝ ሊሰማው የሚገባ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት በወንድም ብንያም ዘላለም 2018

መጽሐፈ ዜና: ከምርኮ የተመለሱ ትሩፋንን ማበረታታት /እንዳሻው ነጋሽ/ Chronicles: encouraging postexilic community/ Endashaw

ዳሰሳ፡- አስቴር Esther

፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት //በወንድም እስራኤል ትውልድ @Beqidsina

በረኸት ሒዝኻ ኽትወጽእ ብፓስተር ዮናታን ኣብርሃም SHALOMNA TV 2026

መጽሐፈ አስቴር አስደናቂ ትምህርት በመጋቢ እሸቴ በለጠ ______Hawassa Tabor KHC 2016

ዘፍጥረት፤ ጅማሬ // እንዳሻው ነጋሽ // Genesis: Beginning // Endashaw Negash
![ነገሩ ተገለበጠ PROPHET HENOK GIRMA[JPS TV WORLD WIDE] 2020](https://i.ytimg.com/vi/KHUG_R3u0jw/hqdefault.jpg?sqp=-oaymwEjCNACELwBSFryq4qpAxUIARUAAAAAGAElAADIQj0AgKJDeAE=&rs=AOn4CLByoFv4CcqHqkbuSMQKshZsGhaFSw)
ነገሩ ተገለበጠ PROPHET HENOK GIRMA[JPS TV WORLD WIDE] 2020

ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ ስለ ምሕረቱ እግዚአብሔርን አመስግኑ መዝ 107 ፥ 15

የብሉይ ዳሰሳ | መጽሐፈ አስቴር | ትምህርት 1 | አስፋው በቀለ (ፓ/ር)

Sunday Service: 28th June 2026

የአንበሶቹን አፍ የዘጋ የእምነት ኃይል ነብዩ ዳንኤል#biblestories #history

መጽሐፍ ቅዱስ ትረካ : መጽሃፈ አስቴር(ምዕራፍ 1-10) | Bible Audio : Aster(Chapter 1-10)

መጽሐፈ አስቴር ጥናት - ክፍል አንድ /01/ | Pastor Ali Omer

የንጉሥ ዳዊት ሙሉ ታሪክ: መንፈሳዊ ፊልም በአማርኛ / Story Of King David

🔴ሀጢአት መስራት አቁሙ! | STOP SINNING! - PROPHET TILAHUN TSEGAYE #jesus #protestantreformation #habesha

መጽሐፈ አስቴር አጭር ገለጻ | የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መግቢያ

