ኢየሱስ አባቴ ብሎ መጥራቱ ልክ ነው ወይስ አይደለም? ኢትዮጵያዊው በኬንያ ዶክተር ዛኪር ናይክን አስጨነቀው

የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇    / @dhugaanniboqachiisa   መልካም ዜና የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን። ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡- “በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።” መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡- “ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥... እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15) ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል። ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።” — (ኢሳይያስ 53፥10) ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና። {የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29) እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው። 1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል። 2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ። አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇 http://t.me/BibleAndMe Additional: - [email protected]

የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የምስጋና መዝሙሮች | Abune Gebremenfes Kidus | New Ethiopian Orthodox  Mezmur
▶︎

የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የምስጋና መዝሙሮች | Abune Gebremenfes Kidus | New Ethiopian Orthodox Mezmur

ትንሽ ግፉ በዛ ...  የሸይኻችን ሰዓት | ኸሚስ ምሽት - ክፍል 272 Khemis Mishit #Khemis_Mishit
▶︎

ትንሽ ግፉ በዛ ... የሸይኻችን ሰዓት | ኸሚስ ምሽት - ክፍል 272 Khemis Mishit #Khemis_Mishit

‘መሀመድ የ6 ዓመት ልጅ ማግባቱ ለህሊናዬ እስካሁን እረፍት አይሰጠኝም' ||Mohammed abebaw(መሐመድ አበባው) || #Meskelmedia#2025
▶︎

‘መሀመድ የ6 ዓመት ልጅ ማግባቱ ለህሊናዬ እስካሁን እረፍት አይሰጠኝም' ||Mohammed abebaw(መሐመድ አበባው) || #Meskelmedia#2025

የዓለማችን አስገራሚ የ ኒውክለር ምሽጎች
▶︎

የዓለማችን አስገራሚ የ ኒውክለር ምሽጎች

አደገኛው አስተምሮ ኢየሱስና ሉሲፈር ወንድማማች ናቸው /Pastor Asfaw Bekele /
▶︎

አደገኛው አስተምሮ ኢየሱስና ሉሲፈር ወንድማማች ናቸው /Pastor Asfaw Bekele /

የአህመድ ሙሐመድ ያሁኑ #ገብረስላሴ የክርስትና ጉዞ!
▶︎

የአህመድ ሙሐመድ ያሁኑ #ገብረስላሴ የክርስትና ጉዞ!

"ከአይሁድ፣ ከዕብራውያን እና ከእስራኤላውያን ጀርባ ያለውን ሚስጥር ይወቁ! | መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው  አይተውት የማያውቁት ልዩነት! #እስካሁን ተሳስተናል?
▶︎

"ከአይሁድ፣ ከዕብራውያን እና ከእስራኤላውያን ጀርባ ያለውን ሚስጥር ይወቁ! | መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው አይተውት የማያውቁት ልዩነት! #እስካሁን ተሳስተናል?

ከታዳሚዎች ለመጣላቸው 9 ተመሳሳይ ጥያቄዎች ሁለቱም መልስ ሰጡ፣ ሙስሊሞች ከርክራችሁን አቁሙ || Shabir Ali Vs David Wood Amharic
▶︎

ከታዳሚዎች ለመጣላቸው 9 ተመሳሳይ ጥያቄዎች ሁለቱም መልስ ሰጡ፣ ሙስሊሞች ከርክራችሁን አቁሙ || Shabir Ali Vs David Wood Amharic

የ12ቱ ነገደ እስራኤል ሙሉ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​ @Meba_tv
▶︎

የ12ቱ ነገደ እስራኤል ሙሉ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​ @Meba_tv

Ethio Frist24 //የፕሬዚዳንቶቹ ሚስጥራዊ ስብሰባ፣ ከምርጫው በኋላ በኢትዮጵያ ምን እየተከናወነ ነው?
▶︎

Ethio Frist24 //የፕሬዚዳንቶቹ ሚስጥራዊ ስብሰባ፣ ከምርጫው በኋላ በኢትዮጵያ ምን እየተከናወነ ነው?

SURAH AL KAHF سورة الكهف | BEAUTIFUL CALMING RECITATION TO SOOTHE YOUR HEART | Habibullah TV
▶︎

SURAH AL KAHF سورة الكهف | BEAUTIFUL CALMING RECITATION TO SOOTHE YOUR HEART | Habibullah TV

አለም አቀፉ ዳኢ ዶክተር ዛኪር ናይክ ስለ አሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራንፕ  ተጠይቆ የሰጠው አስደናቂ ምላሽ  ተርጉመን አቅርበንላችሃል ዳና መልቲሚዲያ
▶︎

አለም አቀፉ ዳኢ ዶክተር ዛኪር ናይክ ስለ አሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራንፕ ተጠይቆ የሰጠው አስደናቂ ምላሽ ተርጉመን አቅርበንላችሃል ዳና መልቲሚዲያ

የእስልምናው አጣብቂኝ ሙሉ ክርክር || The Islamic Dilemma Full Debate || የክርክር ስርአት እንዲማር ለሁሱ ላኩለት
▶︎

የእስልምናው አጣብቂኝ ሙሉ ክርክር || The Islamic Dilemma Full Debate || የክርክር ስርአት እንዲማር ለሁሱ ላኩለት

ለምን ሃይማኖት ያስፈልገናል? ክ.2 | Ask Dr Zakir Naik Amharic P.2
▶︎

ለምን ሃይማኖት ያስፈልገናል? ክ.2 | Ask Dr Zakir Naik Amharic P.2

ሰሚራ ከእስልምና ወድ ክርስትና ለምን መጣች? ምስክርነት
▶︎

ሰሚራ ከእስልምና ወድ ክርስትና ለምን መጣች? ምስክርነት

ለምን የራሱን ፖለቲከኞችን ያሸብራል?  “ትርጉም የለሽ ምርጫ” የኦፌኮ መግለጫ,  ያንዣበበው የከተማ ውስጥ አደጋ
▶︎

ለምን የራሱን ፖለቲከኞችን ያሸብራል? “ትርጉም የለሽ ምርጫ” የኦፌኮ መግለጫ, ያንዣበበው የከተማ ውስጥ አደጋ

ያየኸውን አስጠንቅቀህ ንገራቸው አለኝ  ይህ በጣም አስደንጋጭም አስገራሚም ምስክርነት ነው። እባካችሁ እንዳያልፋችሁ   .
▶︎

ያየኸውን አስጠንቅቀህ ንገራቸው አለኝ ይህ በጣም አስደንጋጭም አስገራሚም ምስክርነት ነው። እባካችሁ እንዳያልፋችሁ .

መጽሐፍ ቅዱስ 66 ወይስ 81 | አቡ Vs ሀንኤል | ክርስቲያን Vs ፕሮቴስታንት | ቴቄል ትዩብ
▶︎

መጽሐፍ ቅዱስ 66 ወይስ 81 | አቡ Vs ሀንኤል | ክርስቲያን Vs ፕሮቴስታንት | ቴቄል ትዩብ

ሙስሊሞች ለምን ዉሻ ጠሉ?  ዉሻ ለምን ነጃሳ ሆነ? ጥቁር ዉሻ ለምን እንዲገደል ተደረገ? አስደንጋጭ መልስ በእፎይ
▶︎

ሙስሊሞች ለምን ዉሻ ጠሉ? ዉሻ ለምን ነጃሳ ሆነ? ጥቁር ዉሻ ለምን እንዲገደል ተደረገ? አስደንጋጭ መልስ በእፎይ

እውነታን መካድ የማይችለው ሙስሊም የኢየሱስን አምላክነት በአደባባይ አመነ || Sam Shamoun Amharic
▶︎

እውነታን መካድ የማይችለው ሙስሊም የኢየሱስን አምላክነት በአደባባይ አመነ || Sam Shamoun Amharic