ለእጆቻችን ፋጥነት በገና ትምህርት ክፍል 12 Begena lesson part 12

ልበ_አምላክ_ቅዱስ_ዳዊት 🤲#ሀብተ_ፈውስ፦ በገናን እየደረደረና መዝሙር እየዘመረ ድውይን ህሙምን መፈወስና የመንፈስን ጭንቀት ማስወገድ።በዚህ በተሰጠው ሀብተ ፈውስ በገና በመምታትና መዝሙር በመዘመር ጊዜና ሰዓት እያየ በርኩስ መንፈስ ይሰቃይ የነበረ ሳኦልን ይፈውሰው እንደነበር ሁሉ ዛሬም ቢሆን በርኩስ መንፈስ ተይዘው የሚሰቃዩትን ሲፈውሳቸው ይታያል። (መዝሙረ ዳዊት አንድምታ መቅድም ) 👉ቅዱስ ዳዊት በተሰጠው ሰማያዊ ጸጋ እና ሃብት መዝሙሮችን አዘጋጅቷል። ኁልቁ መዝሙሩ ፻፶ ነው። ፻፶ ውንም መዝሙር በ ፲ አርእስት በአራት ለይኩን ፣በአምስትኛ ለይበሉ ከአምስት ከፍሎታል። ምክንያቱም ለጊዜው #በአምስቱ_መጻህፍተ_ሙሴ ምሳሌ ነው ፍጻሜው ግን ከጊዜው ሳይደርስ እንደ ደረሰ ሆኖ በትንቢት ለተናገራቸው #አምስቱ_አዕማደ_ምሥጢር ምሳሌ ሆኖ ለመቆየት ነው። 👉ቅዱስ ዳዊት ፪፻፹፰ መዘምራን ካህናት ነበሩት፤ እነዚህ ፪፻፹፰ መዘምራን በ ፬ አለቆች ይመሩ ነበር፤ የአለቆቹም ስም እንደሚከተለው ነው። 👉#አሳፍ (መዝ ፡ ፹፯፣ቊ፡፵፱ ፡ቊ፡፹፩) 👉#ቆሬ (መዝ ፡ ፹፯፣ቊ፡፵፰) 👉#ኤማን 👉#ኤዶትም 👉መዝሙር ሰማንያ ስምንት (፹፰) ከላይ የተጠቀሱት ፪፻፹፰ ቱ መዘምራን በየአለቆቻቸው ከ ፬ ተከፍለው አንዱ ወገን በበገና፣ አንዱ ወገን በመሰንቆ ፣ አንዱ ወገን በከበሮ፣ አንዱ ወገን በቃጭል፣ አሥራ ሁለት አሥራ ሁለት እየሆኑ በሃያ አራቱ ጊዜያት በደብተራ ኦሪት እየተሰበሰቡ በንባብ የሚሆነውን ምስጋና በንባብ፤ በዜማ የሚዘመረውን በዜማ ይዘምሩ ነበር፤ ዳዊትም ከአደባባይ በማይውልበት፣ ነገር በማይሰማበት ጊዜ እየተገኘ ከእነርሱ ጋር በበገና ይዘምር እንደ ነበር ተጽፏል። (፩ኛ ዜና መዋዕል ፡ ም፡ ፮ ቊ: ፴፩ ፵፬) (፪ኛዜና መዋዕል ፡ ም፡ ፳፱፣ ቊ፡ ፳፭- ፴፩)(ነሕምያ ፡ ም፡ ፲፪፣ ቊ፡ ፳፰- ፵፯) 👉ለእኛም ለኢትዮጵያ ሰዎች በቀዳማዊ ምኒልክ ጊዜ ታቦተ ጽዮንና መጻሕፍተ ነቢያት ሲመጡ መዝሙረ ዳዊቱ መጥቶልናል፣ነገር ግን ንባቡ ብቻ መጥቶልናል እንጅ መዘምራኑ ይዘምሩት እንደነበረው ሆኖ የመዝሙሩ ግጥም የዜማው ጣዕም ከበገናው ተስማምቶ አልመጣንልም። ምክንያቱም ቅዱስ ዳዊት የደረሰው በቋንቋው በዕብራይስጥ ነበረ። ለእኛ ግን የመጣልን ከዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ ተመልሶ ስለ ሆነ አንድ ንግግር ከአንድ ልሳን ወደ አንድ ልሳን ሲመለስ ንባቡ ተመዛዝኖ ቤቱ ተመጣጥኖ ሊገኝ የማይቻል በመሆኑ ይመስላል።ስለዚህም እስከ አጼ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት በበገና መደርደሩ በዜማ ስልት ከከበሮና ከጽናጽል መተባበሩ ቀርቶ በንባቡ ብቻ የሚጸለይ ጸሎት ሆኖ ኖረ ሊባል ይችላል።(መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ) #begena #ermiasbegena #church #በገና #በገና_መዝሙር #artwork #bass #creative #handmade #ኤማንበገና #emanbegena #ermiashaylay #kebronbegena #begena #በገና #church

how to play begena in 10 minutes
▶︎

how to play begena in 10 minutes

"ከቶ አይቀርም ሞቱ " የበገና ዝማሬ እንዴት እንደርድር ?
▶︎

"ከቶ አይቀርም ሞቱ " የበገና ዝማሬ እንዴት እንደርድር ?

በገና                                                                     Begena Finger exercises
▶︎

በገና Begena Finger exercises

የታመነ ነው የተፈራ የስላሴ መዝሙር በዘማሪ ዲ/ን ብስራት ጨብሲ
▶︎

የታመነ ነው የተፈራ የስላሴ መዝሙር በዘማሪ ዲ/ን ብስራት ጨብሲ

ስርዓተ ቅዳሴ እስከ ምልክቱ
▶︎

ስርዓተ ቅዳሴ እስከ ምልክቱ

ስርዓተ ቅዳሴ በምልክት
▶︎

ስርዓተ ቅዳሴ በምልክት

የበገና አስተሳሰር                                             በገና ትምህርት ክፍል 13 Begena lesson part 13
▶︎

የበገና አስተሳሰር በገና ትምህርት ክፍል 13 Begena lesson part 13

Ethiopian ortodox mezmur begena abel tesfayeየበገና መማርያ ክፍል 1 begena tutor part 1 how to learn begena
▶︎

Ethiopian ortodox mezmur begena abel tesfayeየበገና መማርያ ክፍል 1 begena tutor part 1 how to learn begena

ካንሰር፣  አልዛይመር ፣ ዲሜንሺያ ያለባቸው ህመምተኞች ጋር እየሄድኩ ነፍሳቸው ሰላም እንድታገኝ በገና እደረድራለው  ኤርምያስ በገና  | Seifu on EBS
▶︎

ካንሰር፣ አልዛይመር ፣ ዲሜንሺያ ያለባቸው ህመምተኞች ጋር እየሄድኩ ነፍሳቸው ሰላም እንድታገኝ በገና እደረድራለው ኤርምያስ በገና | Seifu on EBS

ድርብ ድርደራ ምንድንነው?
▶︎

ድርብ ድርደራ ምንድንነው?

ብልህ ሴት ይህን ታረጋለች! | ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan New Sibket 2026
▶︎

ብልህ ሴት ይህን ታረጋለች! | ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan New Sibket 2026

🔴ተወራርጃለሁ|| hanos begena
▶︎

🔴ተወራርጃለሁ|| hanos begena

የበገና ትምህርት፡ ክፍል - 11: ሰላም ለማርያም
▶︎

የበገና ትምህርት፡ ክፍል - 11: ሰላም ለማርያም

ወንድሜ ጠፍቶኝ ስሄድ                                                መጋቤ ስብሀት አለሙ አጋ መዝሙር
▶︎

ወንድሜ ጠፍቶኝ ስሄድ መጋቤ ስብሀት አለሙ አጋ መዝሙር

በገና እንዴት ይቃኛል? በገና ድምጽ የማያወጣልን ምን ሲሆን ነው? | How does the harp sound? How do I tune my harp?
▶︎

በገና እንዴት ይቃኛል? በገና ድምጽ የማያወጣልን ምን ሲሆን ነው? | How does the harp sound? How do I tune my harp?

|ካንሰርን ያክማል  | ከHARVARD  ድረስ መተው ሪሰርች ሰርታዋል አብረውኝ| በገና  MEDITAION  ላይ ይወስዳል | ብልጥ ሰው ልጁን በገና ያሰማል
▶︎

|ካንሰርን ያክማል | ከHARVARD ድረስ መተው ሪሰርች ሰርታዋል አብረውኝ| በገና MEDITAION ላይ ይወስዳል | ብልጥ ሰው ልጁን በገና ያሰማል

🔴ስሜ ተለዉጦ /  ዳን በገና  |  Semay Teleweto by Dan Begena
▶︎

🔴ስሜ ተለዉጦ / ዳን በገና | Semay Teleweto by Dan Begena

Begena/ tunning with in 10 second /#tuningbegena
▶︎

Begena/ tunning with in 10 second /#tuningbegena

ሥርዓተ ቅዳሴ - ክፍል 1
▶︎

ሥርዓተ ቅዳሴ - ክፍል 1

"አየሁኝ በህልሜ" የበገና ዝማሬ እንዴት እንደርድር ?
▶︎

"አየሁኝ በህልሜ" የበገና ዝማሬ እንዴት እንደርድር ?