ለመኖር ሳይሆን ለመሞት የተወለደው ሕጻን|ስሜ ታደሰ | Sime Tadesse

ልደቱ የጸጋው ምንነት የተገለጠበት ሕያው መንገድ ​-የውድቀት ታሪኬ ተስተያይ ማካካሻ አልነበረውም:አይን አጥፍቼ አይኔ በመጥፋቱ: ጥርስ አውልቄ ጥርሴ በመውለቁ:ገድዬ በመገደሌ ብቻ እግዚአብሔር ተተካካይ እፎይታ አላገኘም--አልረካም:: በትዩዩ በሌላ ገጹ:- -የውድቀት ታሪኬን አንግቤ ግና በተስፋ መፍትሔ አግኝ ብዬ በብዙ ጸሎት እና ትጋት ከእርሱ እንዳልተለየሁ መቁጠሬ: በዘላቂነት በፍጹም ደግነትና ያለኝን በማካፈል የኖርኩበት የሕይወት ዘይቤዬን:ዋስትና እንዳለኝ አድርጌ መቁጠሬ: ----ቅዱስ ቃሉን በማጥናት መትጋቴና ማስተማሬ እና መሰል እንቅስቃሴዎችን ሳልታክት ማድረጌ ሁሉ ያስገብዘኝ ይሆናል እንጂ ያስገኙልኛል ያልኩለትን እርግጠኝነት ከእግዝአብሔር ምሬዋለሁ የሚያስብል ቃል አላስወጣውም:: አላስገኘኝም:: ይህ ብቻ አይደለም በትዩዩ:- -የውድቀት ታሪኬ በእውቀት በልጽጌ በመዝለቅ የጨቀየች ማንነቴን በመረዳት እየነጻሁ አድርጌ መቁጠሬ: ለሁሉ ነገር ሀላፊነቱን ከተጠያቂነት ጋር መውሰድ እንዳለብኝ አምኜ መኖሬ እፎይታንና ምስጋናን ከእግዚአብሔር አሁንም አላመጣም:: ይህም ሁሉ ያለመሳካቱ እና የእሙባይ ካብ ሆኖ የመቅረቱ መሰረታዊ ምክንያት የኢየሱስ ክርስቶስ የመወለድን አስፈላጊነት አለመረዳት ያመጣው ጣጣ መሆኑን ዛሬ እኔም ሁላችንም ልብ እንድንለው ፈለጉኝ:: የእግዚአብሔር ቃል :- "..ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤." ሮሜ 3:23 የሚለው የመርዶ አዋጅ ከራሱ ከእግዚአብሔር መፍትሔን ካላመጣ በቀር ሰው ሁሉ በከንቱ ለዘላለም ሞቱ እየሰራ ይኖራል:: የሰው ልጅ ይህን ጉድለት ሊሞላ እርማትም ሊሰጥ የሚችል መስሎት ዳከረ እንጂ መፍትሔ ሰጪ አንድም ሰው ከሰው መካከል አልተገኘም:: ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ግልጥ ነው:-ቃሉ -በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ (ኤፌ 2:1) ያለበትን እውነታ ባለመረዳት ምላሽ የሰጠን የመሰለን ግን የትኛውም ምላሽ ተቀባይነት አጥቶ ውሀ እንደበላው ያልተረዳን ምስኪኖች እንደነበርን እያረዳው ላበስራችሁ ዛሬ በፊታችሁ ተገኝቻለሁ:: ከሁለት ሺህ አመት በፊት ዮሐንስ ከእግዚአብሔር በተላከ መልዐኩ ተጠየቀ::ለጥያቄው መልስ ለማግኘት ዮሐንስ ዋተተ:-ከእርሱ ዘንድ ምንም መልስ አልነበረምና --ወደ ሦስት ያልተገመቱ ክልልሎች በመሔድ ጠየቀ አሁንም የመልስ ፍንጭ የመፍትሔ ዘለላ አልነበረም በዚህ ግዜ ትንሰቅስቆ አለቀሰ:: --ለካስ የሰው ልጅ ፈውስ በሌለው ደዌ ተመቷል:: --ለካስ ጥረቱ ድካሙ በአጭር ቀርቷል:: እግዚአብሔር ይህን ግዜ በመጠቀም የጸጋ ምንነት እና ታላቅነቱ የእግዚአብሔር ፍቅርና ሕያውነቱ አሁን ሊተረጎም ተገልጦም ሊበሰር ሊሰበክም ሰዐቱ ሆነ:: ኩነቱ እንዲህ ይነበባል:- 2 ብርቱም መልአክ፡— መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው? ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ። 3 በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም። 4 መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ። 5 ከሽማግሌዎቹም አንዱ፡— አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፡ አለኝ። 6 በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፥ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ነበሩት እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው። 7 መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው። 8 መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ። 9-10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። 11 አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥ 12 በታላቅም ድምፅ፡— የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል፡ አሉ። 13 በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፡— በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ። ወገኖቼ ከሁሉ ሀጢያትን ሰርተዋል ...ቀጥሎ የመጣው ብስራት 24 በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።(ሮሜ :3:24) የሚል መሆኑን ይህም በመወለድ እውን መሆኑን አስተውሉ:: ይህን እውነታ አጽኚው ሌላው ቃል:- "...ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ (ኤፌ 2:4-5) በማለት ታላቁን የጸጋ ምንነት አጸናልን::ይህም ደግሞ:- "... ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ....ልጁን ላከ፤..."(ገላትያ 4:4) የጸጋው ታላቅነት ይገለጥ ዘንድ ኢየሱስ ተወለደ ይህም ይሆን ዘንድ በሰው አቅም ልናስተውለው የማንችለው ትንግርት ሆነልን ::እንግዲህ የጸጋን ምንነት ገላጭ የሆኑ አምስት መገለጫዎችን አንስቼ ልጠቅልል:- ==አንዱ(1):- እግዝአብሔር ወልድ ሰው ሆነ:: 6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ 7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ 8 በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። 9 በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ 10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ 11 መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ጸጋ እኔን ለማኖር የስላሴ ሁለተኛው እግዝአብሔር ወልድ ስው ሆኖ መገኘቱና መወለድ ነው::ይህ ደግሞ ወደ ሁለተኛው ነጥቤ ያጓጉዘኛል:: ==ሁለት(2):- ድንግል ከሆነችው ሴት ካለወንድ ተጸነሰ:: --ሉቃስ1:27-31 ተባለች እርሷም እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች ሆነም:: ==ሦስት(3):- የሚወለደው ለእርሱ ሳይሆን ለእኛ ለሐጢያተኞች ምትክ ለመሆን ነው:: 4 በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። 5 እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።(ኢሳይያስ 53:4-5 ==አራት(4):- በመወለዱ ሰው በመሆኑ ድካሞቼን ሁሉ ተጋራ ይልቁኑ በስጋ ሞቶ በአካል በመነሳት ለድነቴ ምክንያት የሆነውን የጸጋን ታላቅነት እግዚአብሔር በእኔ ላይ ገለጠው:: 30-31 ነገር ግን፡— የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።(1ኛ ቆሮ 1:30-31) ይህ የተገለጠላቸው ደግሞ -9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤(ሮሜ 10:9) ተባለላቸው:: አምስት(5):- የውድቀትን ጥልቅነት የተረዱ የጸጋው ታላቅነት እስከ እቅፋቸው ሲመጣ ምርጫቸው ምስጋና እና ለመሔድ መድፈር ነው ከዓለም ለመውጣት ለመሞት:: 25 እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል ሰው ነበረ፥ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቅ ነበር፤ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፥ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ። 26 በጌታም የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር። 28 እርሱ ደግሞ ተቀብሎ አቀፈው እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ፡— 29 ጌታ ሆይ፥ አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፤ 30-31 ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤ 32 ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው። 34-35 ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም፡— እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል፡ አላት። ኢየሱስ እኔን ሊያተርፍ በመፍቀዱ ሊሞትልኝ ተወለደልኝ:: ታህሳስ 29 2018 አመተ ምህረት

🔴ከማዕበሉ ለመዳን ትክክለኛውን መንገድ ተከተል |Kes Tigistu Moges| #gospel #kingdomsound
▶︎

🔴ከማዕበሉ ለመዳን ትክክለኛውን መንገድ ተከተል |Kes Tigistu Moges| #gospel #kingdomsound

መንፈስ ቅዱስን መታዘዝ፡ ከሰማርያ ከተማ እስከ በረሃው መንገድ (ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ) || የተለወጡ ለዋጮች
▶︎

መንፈስ ቅዱስን መታዘዝ፡ ከሰማርያ ከተማ እስከ በረሃው መንገድ (ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ) || የተለወጡ ለዋጮች

መጋቢ ታሪኩ ቴዎድሮስ በሐዋርያትና በነቢያት ጉዳይ ዝምታውን ሰበረ‼️ | Nikodimos Show - Tigist Ejigu
▶︎

መጋቢ ታሪኩ ቴዎድሮስ በሐዋርያትና በነቢያት ጉዳይ ዝምታውን ሰበረ‼️ | Nikodimos Show - Tigist Ejigu

“ለበጎ ስራ የተዘጋጀ ሰው አራት ማንነቶች” ክፍል አንድ// ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ
▶︎

“ለበጎ ስራ የተዘጋጀ ሰው አራት ማንነቶች” ክፍል አንድ// ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ

ያዝንላችዋል‼️//ቲፕ ከፓ/ር ቸሬ//
▶︎

ያዝንላችዋል‼️//ቲፕ ከፓ/ር ቸሬ//

የ ህይወታችን አላማ ማወቅ#habesha #motivation #inspiration #kingdomsound
▶︎

የ ህይወታችን አላማ ማወቅ#habesha #motivation #inspiration #kingdomsound

በእግዚአብሔር_ፊት_ንፁህ_ልብና_ሚስጥረኞች_ሆናችሁ_ቅረቡ_በአገልጋይ_ጥላሁን_ፀጋዬ//prophet_tilahun_tsegaye(best_Bible_teaching)
▶︎

በእግዚአብሔር_ፊት_ንፁህ_ልብና_ሚስጥረኞች_ሆናችሁ_ቅረቡ_በአገልጋይ_ጥላሁን_ፀጋዬ//prophet_tilahun_tsegaye(best_Bible_teaching)

እግዚአብሔር አዋቂ ነው | ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ | ክፍል 2 | Dr. Mamusha Fenta #2024 | Halwot Emmanuel United Church
▶︎

እግዚአብሔር አዋቂ ነው | ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ | ክፍል 2 | Dr. Mamusha Fenta #2024 | Halwot Emmanuel United Church

🛑፮ ማህበራዊ ህይወት ከዲ/ን እዩኤል ሀብታሙ ጋር / Social life with D.n Eyuel Habtamu
▶︎

🛑፮ ማህበራዊ ህይወት ከዲ/ን እዩኤል ሀብታሙ ጋር / Social life with D.n Eyuel Habtamu

የሙስሊም ማሕበረሰብን ለመድረስ ሼህ ዘካሪያ ጅብሪል ያቀበሉት የእምነት አካሔድ|| ክፍል 21 |ስሜ ታደሰ | Sime Tadesse
▶︎

የሙስሊም ማሕበረሰብን ለመድረስ ሼህ ዘካሪያ ጅብሪል ያቀበሉት የእምነት አካሔድ|| ክፍል 21 |ስሜ ታደሰ | Sime Tadesse

ልሳንን በምን ተካነው ክፍል ሁለት 2
▶︎

ልሳንን በምን ተካነው ክፍል ሁለት 2

ቄስ ትዕግስቱ| Reverend Tigistu| kes Tigistu ምሳሌያዊ ሰው
▶︎

ቄስ ትዕግስቱ| Reverend Tigistu| kes Tigistu ምሳሌያዊ ሰው

የተሳሳተውን የወንጌል ስርጭት አካሔዳችንን እናርም!! || ክፍል  17 |ስሜ ታደሰ | Sime Tadesse
▶︎

የተሳሳተውን የወንጌል ስርጭት አካሔዳችንን እናርም!! || ክፍል 17 |ስሜ ታደሰ | Sime Tadesse

🔴ቃሉ ከወደክበት ያነሳሃል |"The Word of God has power."| KesTigistu #wordofgod #jesus #kingdomsound #tigistu
▶︎

🔴ቃሉ ከወደክበት ያነሳሃል |"The Word of God has power."| KesTigistu #wordofgod #jesus #kingdomsound #tigistu

እንደዚህ ፀልዩ የህወታችሁን ለዉጥ ታዩታላችሁ! |Apostle Tamrat Tarekegn|
▶︎

እንደዚህ ፀልዩ የህወታችሁን ለዉጥ ታዩታላችሁ! |Apostle Tamrat Tarekegn|

በፈተና_ጊዜ_ይንንን_አስቡ_አገልጋይ_ጥላሁን_ፀጋዬ||prophet_tilahun_tsegaye
▶︎

በፈተና_ጊዜ_ይንንን_አስቡ_አገልጋይ_ጥላሁን_ፀጋዬ||prophet_tilahun_tsegaye

በሰኔ 21 ይህንን አድርጉ !! ተአምረኛዋ የእመቤታችን ስዕል !! ውዳሴዋን ደግሞ የሚያድር ማነው !?ልሳነ ክርስቶስ መምህር ጳውሎስ መ/ሥላሴ
▶︎

በሰኔ 21 ይህንን አድርጉ !! ተአምረኛዋ የእመቤታችን ስዕል !! ውዳሴዋን ደግሞ የሚያድር ማነው !?ልሳነ ክርስቶስ መምህር ጳውሎስ መ/ሥላሴ

እጣ ፈንታ ወይም የ40 ቀን እድል....!!! | Predestination Is Wrong! | Diakon Henok Haile
▶︎

እጣ ፈንታ ወይም የ40 ቀን እድል....!!! | Predestination Is Wrong! | Diakon Henok Haile

የተስፋው ቃል ሲዘገይ የእግዚአብሔር መልስ!! ቄስ ትግስቱ ሞገስ kes Tigistu Moges
▶︎

የተስፋው ቃል ሲዘገይ የእግዚአብሔር መልስ!! ቄስ ትግስቱ ሞገስ kes Tigistu Moges

ከቤተልሄም ምንጭ ውሃ ማን ባጠጣኝ | ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ | Dr. Mamusha Fenta #2026 | Halwot Emmanuel United
▶︎

ከቤተልሄም ምንጭ ውሃ ማን ባጠጣኝ | ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ | Dr. Mamusha Fenta #2026 | Halwot Emmanuel United