ቅዱስ አግናጢዎስ ምጥው ለአንበሳ በአናብስት የተበላ ሰማዕት ሐዋርያነ አበው/
ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ቅዱስ አግናጥዮስ የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ በነበረበት ወቅት ቤተ ክርስቲያን ከዓላውያን የሮማ ነገሥታት ከፍተኛ መከራና ስቃይ ይደርስባት ነበር:: በድምጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ከነበረው የመከራ ማዕበል በጾም እና በጸሎት፣ በብዙ መንፈሳዊ ተጋድሎ፥ በተለይም ምእመናን መከራውን ተሰቅቀው ከሃይማኖት እንዳይወጡ ተግቶ በማስተማር እንደ መልካም ካፒቴን ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን መርቶ አሻግሯል:: ቅዱስ አግናጥዮስ ከትሕትናው የተነሣ ስለ ራሱ ሕይወት እውነተኛ የክርስቶስ ፍቅር ላይ ገና አልደረስኩም፤ እውነተኛ የደቀ መዝሙርነት ፍጽምና ላይ አልደረስኩም እያለ ያዝን ነበር:: በመሆኑም ሰማዕትነት የበለጠ ወደ እግዚአብሔር እንደሚያቀርብ በማመን ለሰማዕትነት ክብር እንዲበቃ በእጅጉ ይመኝ ነበር:: በሮማ መንግሥታት ዙፋን ላይ የተተካው ንጉሥ ትርያዳን በጦርነት ድል ቢቀናው ልቡ በትዕቢት ተነፍቶ፥ “ለድል ባበቁት” አማልክት ተመክቶ በግዛቱ ያሉ ክርስቲያኖች በሙሉ ለጣዖታት እንዲገዙ አዘዘ:: ለሥራ ጉዳይ ወደ አንጾኪያ ጎራ ባለበት ጊዜም የክርስቲያኖች መሪ ቅዱስ አግናጥዮስ ተጠርቶ ወደ እርሱ እንዲቀርብ ተደረገ:: ንጉሡም:- “ትእዛዛችንን የምታፈርስ ሌሎችንም በአሰቃቂ ሁኔታ ይገደሉ ዘንድ እንዲሁ የምታስተምር ‘ክፉ ሰይጣን’ አንተ ማን ነህ?” ሲል ጠየቀው:: ቅዱስ አግናጥዮስ እንዲህ ሲል መለሰለት:-“ማንም ለባሴ- እግዚአብሔርን ሰይጣን ሊለው አይገባም፤ ክፉዎች አጋንንት ከእግዚአብሔር አገልጋዮች የራቁ ናቸውና:: ነገር ግን እኔ የእነዚህ ክፉ መናፍስት ጠላት ስለሆንኩ፥ ከሰማዩ ንጉሥ ከክርስቶስ የተነሣ ክፉ አሠራራቸውን ስለማጠፋ ከእነርሱ የተነሣ ክፉ ብትለኝ እስማማለሁ”:: ንጉሡ “ለባሴ-እግዚአብሔር ማን ነው?” ብሎ ሲጠይቅ ቅዱስ አግናጥዮስ “በልቡ ክርስቶስ ያለው” ሲል መለሰለት:: ቀጥሎም ንጉሡ “ታዲያ እኛስ የፈለግነው በጦርነት ጊዜ እርዳታቸው እግጅ ደስ የሚያሰኘን እና በኅሊናችን ያሉ አማልክት በአንተም እንዲኖሩ አይደል?” ሲለው በድፍረት እንዲህ አለው፥ “የአሕዛብ ሰይጣናትን አማልክት በማለትህ ተሳስተሃል:: ሰማይና ምድርን፥ በውስጣቸው ያሉትንም ሁሉ የፈጠረ አንድ እግዚአብሔር፤ በመንግሥቱ በደስታ እኖር ዘንድ ተስፋ የማደርገው የአብ አንድያ ልጅ አንድ ኢየሱስ ክርስቶስ አለና”:: ንጉሡ:- “በጴንጤናዊው ጲላጦስ የተሰቀለውን ማለትህ ነው?” አግናጥዮስ:- “ማለቴ ኀጢአቴን ከአስገኝዋ ጋር የሰቀለውን፤ እርሱን በልባቸው ለተሸከሙት [ለክርስቲያኖች] ሰይጣንን ከነማታለያው ከእግራቸው በታች የቀጠቀጠውን ማለቴ ነው” አለው:: በመጨረሻም ትርያዳን በመዘባበት “ታዲያ የተሰቀለውን እርሱን በውስጥህ ተሸክመሃላ!?” ሲለው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‘በወንጌል አላፍርምና’ [እንደ ሰው ሰውኛ ሽንፈት የሚመስል ነገር ግን የእግዚአብሔር ኀይል የሆነ ነገረ መስቀሉን - ክርስቶስ ታመመ: ሞተ: ተሰቀለ ብዬ ማስተማርን አላፍርም] እንዳለ እርሱም በልበ ሙሉነት “አዎን እውነት ነው፤ ‘በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ’ ተብሎ ተጽፏልና” አለው (2ቆሮ. 6፥16):: ከዚህ በኋላ ንጉሡ ከአንጾኪያ ወደ ሮም ተወስዶ በዚያ በስታድየም በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ለአናብስት ተጥሎ እንዲበላ ትእዛዝ አስተላለፈ:: ሰማዕትነት ጥንቱንም የሚመኘው ነበርና ቅዱስ አግናጥዮስ ይህንን ፍርድ ሲሰማ በደስታ እንዲህ ሲል ጮኸ:- “ኦ ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ! በፍጹም ፍቅርህ አክብረኸኛልና ልክ እንደ ሐዋርያህ ጳውሎስ እጆቼ በብረት ሰንሰለት እንዲታሰሩ አድርገሃለና”:: እጆቹን በደስታ ለሰንሰለት ካስረከበ በኋላ በጨካኝ ወታደሮች እየተዳፋ ጉዞ ወደ ሮም ሆነ:: ሰርምኔስ እንደ ደረሰ ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ እግር ሥር አብሮት የተማረውን አሁን የሰርምኔስ ጳጳስ የሆነው የሚወደው ጓደኛው ፖሊካርፕስን አግኝቶ ብዙ መንፈሳዊ ስጦታዎች ተለዋወጡ፤ የአብያተ ክርስቲያናትን አደራም ሰጠው:: በጉዞው ወቅት ብዙ ከተሞችን እያቆራረጠ ሲሄድ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናት እርሱን ለማግኘት ከየአካባቢው አብያተ ክርስቲያናት ይጎርፉ ነበር:: ለእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት መላእክታትን የጻፈውም በዚሁ ጉዞ ላይ ሆኖ ነው:: ሰዎች ሁሉ በየመንገዱ እየተከተሉ እርሱን ለማግኘት ሲሽቀዳደሙ እና ፍቅራቸውን ሲገልጹ ተመልክቶ ምናልባት ይህ ፍቅራቸው የተከፈተለትን የሰማዕትነት በር እንዳይዘጋበት ሰግቶ ለሮም ክርስቲያኖች እንዳይከለክሉት ጻፈላቸው:: በአድርያቲክ ባሕር በመርከብ ሲጓዝ “ፑቲዮሊስ”ን (ሐዋ. 28፥13-14) ሲያይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በተመሳሳይ ታስሮ ወደ ሮም የሄደበትን የጉዞ መስመር ተከትሎ ይሄድ ዘንድ ወደደ:: ነገር ግን ማዕበል ስለ ተነሣ በዚያ መሄድ አልተቻለም:: ሮም እንደ ደረሰ በዚያ ያሉት ወንድሞች እርሱን በማየታቸው ደስ ቢላቸውም ሊሞት ስለ ሆነ ደግሞ አዝነው በተቀላቀለ ስሜት ሆነው ተቀበሉት:: እርሱም ካረጋጋቸው እና ለአብያተ ክርስቲያናቱ ሁሉ ከጸለየ በኋላ በሮማ ስታድየም የሚካሄደው ፌስቲባል እየተገባደደ ስለነበር ሕዝቡ ሳይበተን ለማድረስ በወታደሮች እየተቻኮለ ወደ ትያትር ቦታው ተወሰደ:: በዚያም ለአንበሶች ተጥሎ “ለጻድቃንም ምኞታቸው ትሰጣቸዋለች” እንደ ተባለ (ምሳ. 10፥24) የክርስቶስ ሰማዕት ለመሆን በተመኘው መሠረት ምኞቱን አገኘ:: ከአንበሶች የተረፈው ተረፈ ዐጽሙም ተሰብስቦ ለአንሶኪያ ቤተክርስቲያን ተላከላት::

የቅዱስ ላሊበላ አስደናቂ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) @Meba_tv

📍መነኩሴ ከአንድ ገዳም አይወጣም‼️መነኩሴ ከተማ ከተገኘ ምራቅ ይተፋበታል// አባ ገብረኪዳን @menkermedia21

❤እግዚአብሔር አልታረቅ ያለው🔴ሀሜተኞች በመሆናችን ነው❤EOTC👉በኑኃሚን ቲዩብ‼️

ሰኔ ጎልጎታ | Samuel Asres| ሳሙኤል አስረስ | Ethiopia Orthodox Tewahido | 14 August 2023

🛑 ተወዳጅ የእመቤታቸን መዝሙሮች ስብስብ #Ethiopian Orthodox Tewahdo #Maryam_mezmur #ህዳር_ፂወን @Hosaenamedia

ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ማን ነው ? | መባዕ ቲቪ @Meba_tv

🔴 የሃጥያቶች ሁሉ እናት አዲስ ስብከት በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ || aba gebrekidan girma

የዘጠኙ ቅዱሳን ታሪክ - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ - @meba-tv - Eotc tv - ስንክሳር - ገድል

🔴ሳይቋረጥ የሚደመጡ የእመቤታችን መዝሙራት like mezemran yilma hailu yemaryam mezmurat

ክብረ ቅዱሳን // ቅዱስ አግናጢዎስ

የዮሐንስ ወንጌል ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ትረካ - The Gospel of John Full Audio Bible

መዝሙረ ዳዊት መፀለይ ጀምሩ! | ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan New Sibket 2026

የድንግል ማርያም ሞት - አስተርዮ ማርያም - መባዕ ቲቪ (Meba TV) @Meba_tv

ኢትዮጵያ ለምን ተከለከለች? || የተከለከለው የኢትዮጵያ ታሪክ || ታላላቅ ሚስጥሮች ሲጋለጡ || ደራሲ አሸናፊ ፈንቴ

ነቢዩ ኤልያስ | የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች (ከብሉይ ኪዳን)

🔴አዲስ ስብከት ‼️አትባክኑ ጊዜያችሁ ተጠቀሙ-ጊዜ የለኝም አትበሉ //ራሳችንን የምንለውጥበት ድንቅ ትምህርት //የሚያሳርፍ //ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን

የማያዳግም መልስ // ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ? // ጥያቄና መልስ ክፍል 02

የአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አስደናቂ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) @Meba_tv

ዘማሪ ገብረዮሐንስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የዘመራቸው መዝሙሮች | ቤተ ቅኔ - Beta Qene

